መዝሙር 126
በፍቅር ተነሳስተን ያከናወንነው ሥራ
በወረቀት የሚታተመው
1. አበቃኸን ለዚህ ቀን፤
ልዑሉ አምላክ ተመስገን።
ያሳየኸን ሞገስ፣ ክብርህም፣
ቃል አይገልጸውም
አይተህ ድካማችንን፣
ባርከኸዋል ሥራችንን።
ላንተ የሠራነው ይህ ሕንፃ፣
ያሳያል ይህን።
(አዝማች)
ይሖዋ ሆይ ላንተ ቤት መሥራት፣
ነው ለኛ እጅግ ታላቅ መብት።
ዕድሜያችንን በሙሉ አንተን ’ናገልግልህ፤
በሥራችን እናክብርህ።
2. ሁላችን ደስ ብሎናል፤
ዝምድናችንም ጠንክሯል።
ይህ ትዝታ ከቶ አይጠፋም፤
እስከ ዘላለም!
በአንድነት ለመሥራት
ሆኖናል መንፈስህ ረዳት።
ስምህን ከፍ ከፍ አ’ርገናል
ተደስተናል።
(አዝማች)
ይሖዋ ሆይ ላንተ ቤት መሥራት፣
ነው ለኛ እጅግ ታላቅ መብት።
ዕድሜያችንን በሙሉ አንተን ’ናገልግልህ፤
በሥራችን እናክብርህ።
(በተጨማሪም መዝ. 116:1፤ 147:1ን እና ሮም 15:6ን ተመልከት።)