መዝሙር 80
ጥሩነት
በወረቀት የሚታተመው
1. የይሖዋ ጥሩነት ነው፣ ደስተኛ የሚያደርገን።
ጥሩነቱ ወደር የለው፤ እሱ ነው አባታችን።
ለኛ ከሚገባን በላይ፣ ሞገሱን ያሳየናል።
በደስታ እናገልግለው፤ አምልኮ ይገባዋል።
2. በአምሳሉ ስለሠራን እንችላለን ማዳበር፣
ባሕርያቱን በጠቅላላ፣ ጥሩነቱንም ጭምር።
እንደ አምላክ ጥሩ እንሁን፤ እናሳይ ባሕርያቱን።
ፍሬውን ማፍራት እንድንችል መንፈሱን እንለምን።
3. ለክርስቲያን ባልንጀሮች በ’ምነት ለሚዛመዱን፣
ልዩ ፍቅር ቢኖረንም፣ ለሁሉም መልካም እንሁን።
ምሥራቹን ስንናገር፣ ተስፋውን ስናካፍል፣
መቼም ቢሆን አናዳላ፤ ጥሩነት እንዲሟላ።
(በተጨማሪም መዝ. 103:10ን፣ ማር. 10:18ን፣ ገላ. 5:22ን እና ኤፌ. 5:9ን ተመልከት።)