መዝሙር 124
በእንግድነት ተቀበሏቸው
በወረቀት የሚታተመው
1. እንግዳ ተቀባይ ነው ይሖዋ ’ምላክ፤
ለሁሉም ያስባል፣ ማዳላት አያውቅ።
ዝናብና ፀሐይ ለሁሉም ይሰጣል፤
ልብንም
በደስታ ይሞላል።
ለተቸገረ ሰው ጥሩዎች ስንሆን፣
ይሖዋ አምላክን እንመስለዋለን።
ለሌሎች ልባዊ ደግነት ካሳየን፣
ካምላክ ወሮታ ’ናገኛለን።
2. የተቸገረን አይተን መርዳታችን፣
ይችላል ውጤቱ ያማረ ሊሆን።
ባናውቃቸው እንኳ እንቀበላቸው፤
በችግር ጊዜ እንርዳቸው።
ልክ እንደ ሊዲያ ‘ቤቴ ኑ’ እንበል፤
ቤታችን ’ሚመጣ ሰው
እፎይ ይበል።
ይሖዋ እንደሱ ደጎች የሆኑትን፣
የትም ቢሆኑ ያያቸዋል።
(በተጨማሪም ሥራ 16:14, 15ን፣ ሮም 12:13ን፣ 1 ጢሞ. 3:2ን፣ ዕብ. 13:2ን እና 1 ጴጥ. 4:9ን ተመልከት።)