የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • rk ክፍል 7 ገጽ 18-19
  • አምላክ በነቢያቱ በኩል የሰጠው ተስፋ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • አምላክ በነቢያቱ በኩል የሰጠው ተስፋ
  • እውነተኛ እምነት ደስታ ያስገኝልሃል
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • የመጽሐፍ ቅዱስ አጠቃላይ ስምምነት
    መጽሐፍ ቅዱስ—የአምላክ ቃል ነው ወይስ የሰው?
  • አምላክ የሰውን ዘር ለማዳን ዝግጅት አደረገ
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2013
  • የእባቡ ዘር፣ እንዴት ተጋለጠ?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1996
  • በአምላክ ትንቢታዊ ቃል ላይ እምነት ይኑራችሁ!
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2000
ለተጨማሪ መረጃ
እውነተኛ እምነት ደስታ ያስገኝልሃል
rk ክፍል 7 ገጽ 18-19

ክፍል 7

አምላክ በነቢያቱ በኩል የሰጠው ተስፋ

የጥንቶቹ ነቢያት በአምላክ ላይ እምነት እንዳላቸው አሳይተዋል። እሱ በሰጣቸው ተስፋዎች ላይ እምነት የነበራቸው ከመሆኑም ሌላ ሕይወታቸው ይህንን የሚያሳይ ነበር። እነዚህ ተስፋዎች ምንድን ናቸው?

አዳምና ሔዋን (አደምና ሐዋ) በኤደን ገነት ውስጥ ካመፁ በኋላ አምላክ፣ ‘የእባቡን’ ራስ በመጨፍለቅ ለዘላለም የሚያጠፋው “ዘር” እንደሚያስነሳ ወዲያውኑ ተስፋ ሰጠ፤ እንደሚጨፈለቅ የተገለጸው “ታላቁ ዘንዶ . . . ዲያብሎስና ሰይጣን ተብሎ የሚጠራው የጥንቱ እባብ” ነው። (ዘፍጥረት 3:​14, 15፤ ራእይ 12:​9, 12) ታዲያ ይመጣል ተብሎ ተስፋ የተደረገበት ይህ ዘር ማን ሆኖ ተገኘ?

ይሖዋ ይህንን የመጀመሪያ ትንቢት ከተናገረ ከ2,000 ዓመታት ገደማ በኋላ ለነቢዩ አብርሃም (ኢብራሂም) ይመጣል ተብሎ ተስፋ የተደረገበት ሰው ከእሳቸው ዝርያ እንደሚወለድ ቃል ገባላቸው። አምላክ ለአብርሃም እንዲህ አላቸው፦ “ቃሌን ስለሰማህ የምድር ብሔራት ሁሉ በዘርህ አማካኝነት ለራሳቸው በረከት ያገኛሉ።”​—⁠ዘፍጥረት 22:​18

በ1473 ዓ.ዓ. አምላክ ይህንን “ዘር” አስመልክቶ ለነቢዩ ሙሴ (ሙሳ) ተጨማሪ መረጃ ሰጣቸው። ሙሴ የእስራኤልን ልጆች እንዲህ አሏቸው፦ “አምላክህ ይሖዋ ከወንድሞችህ መካከል እንደ እኔ ያለ ነቢይ ያስነሳልሃል። እናንተም እሱን ማዳመጥ ይኖርባችኋል።” (ዘዳግም 18:​15) ስለዚህ ይመጣል ተብሎ ተስፋ የተደረገበት ነቢይ ልክ እንደ ሙሴ ከአብርሃም ልጆች መካከል ይወለዳል ማለት ነው።

በተጨማሪም ይህ ነቢይ ከንጉሥ ዳዊት (ዳውድ) የዘር ሐረግ የሚወለድ ሲሆን እሱ ራሱም ታላቅ ንጉሥ ይሆናል። አምላክ ለንጉሥ ዳዊት “ከአንተ በኋላ ከአብራክህ የሚወጣውን ዘርህን አስነሳለሁ፤ . . . የመንግሥቱን ዙፋን ለዘላለም አጸናለሁ” የሚል ቃል ገብቶላቸዋል። (2 ሳሙኤል 7:​12, 13) በተጨማሪም አምላክ ይህ የዳዊት ዝርያ “የሰላም መስፍን” ተብሎ እንደሚጠራ የገለጸ ሲሆን አክሎም እንዲህ ብሏል፦ “በዳዊት ዙፋንና በመንግሥቱ ላይ ይቀመጣል፤ እየተጠናከረ የሚሄደው አገዛዙም ሆነ ሰላሙ ፍጻሜ አይኖረውም። ከአሁን ጀምሮ ለዘላለም በማይናወጥ ሁኔታ ይመሠረታል፤ በፍትሕና በጽድቅም ጸንቶ ይኖራል።” (ኢሳይያስ 9:​6, 7) አዎ፣ ይህ ጻድቅ መሪ በምድር ላይ ሰላምና ፍትሕ እንዲሰፍን ያደርጋል። ታዲያ የሚመጣው መቼ ይሆን?

አብርሃም፣ ሙሴ፣ ዳዊት፣ ኢየሱስና ተስፋ የተሰጠበት ዘር የእባቡን ጭንቅላት ሲጨፈልቅ

ተስፋ የተደረገበት “ዘር” . . . የሚወለደው ከአብርሃም (ከኢብራሂም) ዘር ነው፣ እንደ ሙሴ (ሙሳ) ያለ ነቢይ ይሆናል፣ የሚመጣው ከዳዊት (ከዳውድ) የዘር ሐረግ ነው፣ የሚመጣው በ29 ዓ.ም. ነው፣ እባቡን ማለትም ሰይጣንን ይጨፈልቃል

ከጊዜ በኋላ መልአኩ ገብርኤል (ጂብሪል) ለነቢዩ ዳንኤል እንዲህ አላቸው፦ “ኢየሩሳሌምን ለማደስና መልሶ ለመገንባት ትእዛዝ ከሚወጣበት ጊዜ አንስቶ መሪ የሆነው መሲሕ እስከሚገለጥበት ጊዜ ድረስ 7 ሳምንታትና 62 ሳምንታት እንደሚሆን እወቅ፤ አስተውልም።” (ዳንኤል 9:​25) እያንዳንዳቸው የ7 ዓመት ርዝማኔ ያላቸው እነዚህ 69 ሳምንታት በድምሩ 483 ዓመታት ይሆናሉ። እነዚህ ዓመታት ከ455 ዓ.ዓ. እስከ 29 ዓ.ም. ያሉትን ጊዜያት ያመለክታሉ።a

ታዲያ መሲሑ ማለት እንደ ሙሴ ያለው ነቢይና ለረጅም ጊዜ ሲጠበቅ የቆየው “ዘር” በ29 ዓ.ም. መጥቷል? ይህን በቀጣዩ ርዕስ ላይ እንመለከታለን።

a በይሖዋ ምሥክሮች በተዘጋጀው ለዘላለም በደስታ ኑር! በተባለው መጽሐፍ ገጽ 255 ላይ የሚገኘውን ተጨማሪ ሐሳብ 2 ተመልከት።

ምን ብለህ ትመልሳለህ?

  • ይመጣል ተብሎ ተስፋ የተደረገበት የአብርሃም (የኢብራሂም) “ዘር” ሰይጣንን ምን ያደርገዋል?

  • አምላክ በሙሴ (በሙሳ) በኩል ምን ተስፋ ሰጥቷል?

  • ዳዊት (ዳውድ) ስለ ‘ዘሩ’ ምን ማወቅ ችለዋል?

  • መልአኩ ገብርኤል (ጂብሪል) ለነቢዩ ዳንኤል ምን ነገራቸው?

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ