የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ll ክፍል 3 ገጽ 8-9
  • በገነት ውስጥ የነበረው ሕይወት ምን ይመስል ነበር?

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • በገነት ውስጥ የነበረው ሕይወት ምን ይመስል ነበር?
  • አምላክን ስማ የዘላለም ሕይወት ታገኛለህ
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ከእኛ በላይ የሆኑ አሉ
    ከታላቁ አስተማሪ ተማር
  • መኖሪያቸውን ያጡት ለምንድን ነው?
    የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች መማሪያ መጽሐፌ
  • ሰይጣንን መስማታቸው ምን ውጤት አስከተለ?
    አምላክን ስማ የዘላለም ሕይወት ታገኛለህ
  • ክፍል 3
    አምላክን ስማ
ለተጨማሪ መረጃ
አምላክን ስማ የዘላለም ሕይወት ታገኛለህ
ll ክፍል 3 ገጽ 8-9

ክፍል 3

በገነት ውስጥ የነበረው ሕይወት ምን ይመስል ነበር?

ይሖዋ ለአዳምና ለሔዋን ብዙ ጥሩ ነገሮች ሰጥቷቸዋል። ዘፍጥረት 1:28

ይሖዋ ሔዋንን ከፈጠረ በኋላ ወደ አዳም አመጣት

ይሖዋ የመጀመሪያዋን ሴት ማለትም ሔዋንን ከፈጠረ በኋላ ሚስት እንድትሆነው ለአዳም ሰጠው።—ዘፍጥረት 2:21, 22

ይሖዋ ምንም እንከን የሌለበት ፍጹም የሆነ አእምሮና አካል ሰጥቷቸው ነበር።

አዳምና ሔዋን ገነት የሆነችውን መኖሪያቸውን ሲመለከቱ

አዳምና ሔዋን ይኖሩ የነበረው ገነት በሆነው በኤደን የአትክልት ስፍራ ሲሆን ይህ ቦታ ወንዝ፣ የፍራፍሬ ዛፎችና እንስሳት ያሉበት እጅግ የተዋበ ስፍራ ነበር።

ይሖዋ ያነጋግራቸውና ያስተምራቸው ነበር። እሱን ቢሰሙት ኖሮ በምድር ላይ በገነት ለዘላለም መኖር ይችሉ ነበር።

አምላክ ከዛፎቹ መካከል የአንደኛውን ዛፍ ፍሬ እንዳይበሉ አዟቸው ነበር። ዘፍጥረት 2:16, 17

ይሖዋ፣ አዳምና ሔዋን እንዳይበሉ የከለከላቸው ዛፍ

ይሖዋ ለአዳምና ለሔዋን በአትክልት ቦታው ካሉት ዛፎች መካከል አንዱን አሳይቶ ፍሬውን ቢበሉ እንደሚሞቱ ነገራቸው።

ክፉው መልአክ ሰይጣን ዲያብሎስ በእባብ ተጠቅሞ ሔዋንን ሲያናግራት

ከመላእክት መካከል አንዱ በአምላክ ላይ ዓመፀ። ይህ ክፉ መልአክ ሰይጣን ዲያብሎስ ነው።

ሰይጣን፣ አዳምና ሔዋን ይሖዋን እንዲታዘዙ አልፈለገም ነበር። ስለዚህ እባብን መሣሪያ አድርጎ በመጠቀም የዛፉን ፍሬ ብትበላ እንደማትሞት ይልቁንም እንደ አምላክ እንደምትሆን ለሔዋን ነገራት። እርግጥ ይህ ውሸት ነበር።—ዘፍጥረት 3:1-5

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ