የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • yc ትምህርት 12 ገጽ 26-27
  • ደፋር የሆነው የጳውሎስ እህት ልጅ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ደፋር የሆነው የጳውሎስ እህት ልጅ
  • ልጆቻችሁን አስተምሩ
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • የጳውሎስ የእህት ልጅ—የአጎቱን ሕይወት አተረፈ
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2009
  • “የማቀርበውን የመከላከያ መልስ ስሙ”
    ‘ስለ አምላክ መንግሥት በሚገባ መመሥከር’
  • አትፍራ፣ ይሖዋ ረዳትህ ነው
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2020
  • በድፍረት የተሟላ ምሥክርነት መስጠት
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2006
ለተጨማሪ መረጃ
ልጆቻችሁን አስተምሩ
yc ትምህርት 12 ገጽ 26-27
የጳውሎስ እህት ልጅ ከጦር አዛዡ ጋር ሲነጋገር

ትምህርት 12

ደፋር የሆነው የጳውሎስ እህት ልጅ

የአጎቱን ሕይወት ስላተረፈ አንድ ወጣት እስቲ እንመልከት። የዚህ ወጣት አጎት ሐዋርያው ጳውሎስ ነው። የወጣቱን ስም ባናውቅም ድፍረት የሚጠይቅ ነገር እንዳከናወነ እናውቃለን። ምን እንዳደረገ ማወቅ ትፈልጋለህ?—

ጳውሎስ በኢየሩሳሌም ታስሮ ነበር። የታሰረው ስለ ኢየሱስ በመስበኩ ነው። አንዳንድ ክፉ ሰዎች ጳውሎስን ስለጠሉት አንድ መጥፎ ነገር ለማድረግ ተመካከሩ። እንዲህ ተባባሉ፦ ‘የጦር አዛዡ፣ ጳውሎስን ከወታደሮች ጋር ወደ ፍርድ ቤት እንዲልከው እንጠይቀው። እኛም መንገድ ላይ እንደበቅና ጳውሎስ በዚያ በኩል ሲያልፍ እንገድለዋለን!’

ሐዋርያው ጳውሎስ ታስሮ እያለ ከእህቱ ልጅ ወሬ ሲሰማ

የጳውሎስ እህት ልጅ፣ አንዳንድ ሰዎች ያሰቡትን መጥፎ ነገር ለጳውሎስና ለጦር አዛዡ ነገራቸው

የጳውሎስ እህት ልጅ ይህን ሐሳባቸውን ሰማ። በዚህ ጊዜ ምን ያደርግ ይሆን? ወደ እስር ቤቱ በመሄድ ስለ ጉዳዩ ለጳውሎስ ነገረው። ጳውሎስም ወዲያውኑ ይህንን መጥፎ ሐሳባቸውን ለጦር አዛዡ እንዲናገር አሳሰበው። የጳውሎስ እህት ልጅ ጉዳዩን ለጦር አዛዡ መናገር ቀላል የሚሆንለት ይመስልሃል?— በፍጹም፣ ምክንያቱም የጦር አዛዡ ትልቅ ቦታ ያለው ሰው ነበር። የጳውሎስ እህት ልጅ ግን ደፋር ስለነበር የጦር አዛዡን አነጋገረው።

የጦር አዛዡ ምን ማድረግ እንዳለበት ያውቅ ነበር። አዛዡ፣ ጳውሎስ ጉዳት እንዳይደርስበት ለመከላከል ሲል 500 የሚያህሉ ወታደሮችን አዘጋጀ! ከዚያም በዚያው ዕለት ምሽት ጳውሎስን ወደ ቂሳርያ እንዲወስዱት አዘዛቸው። ጳውሎስ በደህና ደርሶ ይሆን?— አዎ፣ እነዚያ መጥፎ ሰዎች ጥቃት ሊያደርሱበት አልቻሉም። ያሰቡት መጥፎ ነገር ስላልተሳካ ጳውሎስ ተረፈ።

ከዚህ ታሪክ ምን ትምህርት ታገኛለህ?— አንተም እንደ ጳውሎስ እህት ልጅ ደፋር መሆን ትችላለህ። ለሌሎች ስለ ይሖዋ ስንናገር ድፍረት ያስፈልገናል። አንተስ ደፋር በመሆን ስለ ይሖዋ መናገርህን ትቀጥላለህ?— እንዲህ የምታደርግ ከሆነ የአንድ ሰው ሕይወት ልታተርፍ ትችል ይሆናል።

የሚከተሉትን ጥቅሶች አንብቡ

  • የሐዋርያት ሥራ 23:12-24

  • ማቴዎስ 24:14፤ 28:18-20

  • 1 ጢሞቴዎስ 4:16

ጥያቄዎች፦

  • አንዳንድ መጥፎ ሰዎች ጳውሎስን ምን ሊያደርጉት አስበው ነበር?

  • የጳውሎስ እህት ልጅ ምን አደረገ? ይህን ለማድረግ ደፋር መሆን ያስፈለገው ለምንድን ነው?

  • አንተስ እንደ ጳውሎስ እህት ልጅ ደፋር መሆን የምትችለው እንዴት ነው?

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ