የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • yc ትምህርት 13 ገጽ 28-29
  • ጢሞቴዎስ ሰዎችን ለመርዳት ይፈልግ ነበር

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ጢሞቴዎስ ሰዎችን ለመርዳት ይፈልግ ነበር
  • ልጆቻችሁን አስተምሩ
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ጢሞቴዎስ—አምላክን ለማገልገል ዝግጁና ፈቃደኛ ነበር
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2008
  • ጳውሎስና ጢሞቴዎስ
    ከመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች ምን ትማራለህ?
  • ጢሞቴዎስ ‘በእምነት እውነተኛ ልጅ የሆነ’
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1999
  • ‘በጌታ ልጄ የሆነው የምወደውና ታማኝ የሆነው ጢሞቴዎስ’
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2015
ለተጨማሪ መረጃ
ልጆቻችሁን አስተምሩ
yc ትምህርት 13 ገጽ 28-29
ትንሹን ጢሞቴዎስ እናቱ ኤውንቄና አያቱ ሎይድ ሲያስተምሩት

ትምህርት 13

ጢሞቴዎስ ሰዎችን ለመርዳት ይፈልግ ነበር

ጢሞቴዎስ ሌሎችን መርዳት የሚያስደስተው ወጣት ነበር። ሰዎችን ለመርዳት ሲል ወደ ብዙ ቦታዎች ሄዷል። ሌሎችን ይረዳ ስለነበር ሕይወቱ በጣም አስደሳች ነበር። ስለ ጢሞቴዎስ ታሪክ መስማት ትፈልጋለህ?—

የጢሞቴዎስ እናትና አያት ስለ ይሖዋ አስተምረውታል

ጢሞቴዎስ ያደገው በልስጥራ ነው። አያቱ ሎይድና እናቱ ኤውንቄ፣ ጢሞቴዎስን ስለ ይሖዋ ያስተማሩት ገና ከትንሽነቱ ጀምሮ ነው። ጢሞቴዎስ እያደገ ሲሄድ እሱም ሌሎችን ስለ ይሖዋ ማስተማር ጀመረ።

ጢሞቴዎስ ገና ወጣት እያለ፣ ጳውሎስ ከእሱ ጋር ወደ ሌሎች ቦታዎች እየሄደ እንዲሰብክ ጠየቀው። ጢሞቴዎስም ‘እሺ!’ አለ። ወደ ተለያዩ ቦታዎች በመሄድ ሌሎችን ለመርዳት ፈቃደኛ ነበር።

ጢሞቴዎስ፣ መቄዶንያ ውስጥ ወደምትገኝ ተሰሎንቄ የተባለች ከተማ ከጳውሎስ ጋር ተጓዘ። እዚያ ለመድረስ ረጅም መንገድ በእግራቸው መሄድና ከዚያም በጀልባ መጓዝ ነበረባቸው። በመጨረሻም ተሰሎንቄ ሲደርሱ ብዙ ሰዎችን ስለ ይሖዋ አስተማሩ። ይሁን እንጂ አንዳንድ ሰዎች በጣም ስለተናደዱ ሊደበድቧቸው ሞከሩ። በዚህ ጊዜ ጳውሎስና ጢሞቴዎስ ይህችን ከተማ ትተው በሌሎች ቦታዎች ለመስበክ ሄዱ።

ጢሞቴዎስ ከሐዋርያው ጳውሎስ ጋር በጀልባ ሲጓዝ

ጢሞቴዎስ አስደሳች ሕይወት ነበረው

ከተወሰኑ ወራት በኋላ ጳውሎስ፣ ወደ ተሰሎንቄ ተመልሶ በዚያ የነበሩትን ወንድሞች እንዲጠይቃቸው ጢሞቴዎስን ላከው። ጢሞቴዎስ ወደዚያች አደገኛ ከተማ ተመልሶ ለመሄድ ድፍረት ጠይቆበታል! ያም ቢሆን ጢሞቴዎስ በዚያ ያሉት ወንድሞች ሁኔታ ስላሳሰበው ተመልሶ ሄደ። ከዚያም ለጳውሎስ ጥሩ ዜና ይዞለት ተመለሰ። በተሰሎንቄ ያሉት ወንድሞች በጥሩ ሁኔታ ላይ ነበሩ!

ጢሞቴዎስ ለብዙ ዓመታት ከጳውሎስ ጋር አብሮ አገልግሏል። በአንድ ወቅት ጳውሎስ ጉባኤዎችን ለመርዳት ሊልከው የሚችለው ከሁሉ የተሻለው ሰው ጢሞቴዎስ እንደሆነ ጽፎ ነበር። ጢሞቴዎስ ይሖዋንና ሰዎችን ይወድ ነበር።

አንተስ ሰዎችን ትወዳለህ? ስለ ይሖዋ እንዲማሩ መርዳትስ ትፈልጋለህ?— ከሆነ ሕይወትህ ልክ እንደ ጢሞቴዎስ በጣም አስደሳች ሊሆን ይችላል!

የሚከተሉትን ጥቅሶች አንብቡ

  • 2 ጢሞቴዎስ 1:5፤ 3:15

  • የሐዋርያት ሥራ 16:1-5፤ 17:1-10

  • 1 ተሰሎንቄ 3:2-7

  • ፊልጵስዩስ 2:19-22

ጥያቄዎች፦

  • ጢሞቴዎስ ያደገው የት ነበር?

  • ጢሞቴዎስ፣ ከጳውሎስ ጋር ለመሄድ ፈቃደኛ ነበር? ፈቃደኛ የሆነው ለምን ነበር?

  • ጢሞቴዎስ ወደ ተሰሎንቄ ተመልሶ የሄደው ለምንድን ነው?

  • እንደ ጢሞቴዎስ አስደሳች ሕይወት እንዲኖርህ ምን ማድረግ ትችላለህ?

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ