የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • jy ምዕ. 24 ገጽ 62-ገጽ 63 አን. 7
  • በገሊላ በስፋት ሰበከ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • በገሊላ በስፋት ሰበከ
  • ኢየሱስ—መንገድ፣ እውነት፣ ሕይወት
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ኢየሱስ ወደ ምድር የመጣበት ምክንያት
    እስከ ዛሬ ከኖሩት ሁሉ የሚበልጠው ታላቅ ሰው
  • ሀ7-ሐ የኢየሱስ ምድራዊ ሕይወት አበይት ክንውኖች—ኢየሱስ በገሊላ ያከናወነው ታላቅ አገልግሎት (ክፍል 1)
    አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ
  • ለይሖዋ አምልኮ ያሳየው ቅንዓት
    እስከ ዛሬ ከኖሩት ሁሉ የሚበልጠው ታላቅ ሰው
  • መሲሑ ትንቢቶች እንዲፈጸሙ አድርጓል
    ክርስቲያናዊ ሕይወታችንና አገልግሎታችን​—የስብሰባው አስተዋጽኦ (2016)
ለተጨማሪ መረጃ
ኢየሱስ—መንገድ፣ እውነት፣ ሕይወት
jy ምዕ. 24 ገጽ 62-ገጽ 63 አን. 7
ጴጥሮስ፣ እንድርያስ፣ ያዕቆብና ዮሐንስ ኢየሱስን አገኙት

ምዕራፍ 24

በገሊላ በስፋት ሰበከ

ማቴዎስ 4:23-25 ማርቆስ 1:35-39 ሉቃስ 4:42, 43

  • ኢየሱስ ከአራት ደቀ መዛሙርቱ ጋር ገሊላን ዞረ

  • ስብከቱም ሆነ ያከናወናቸው ሥራዎች በስፋት ታወቁ

ኢየሱስ በቅፍርናሆም ከአራት ደቀ መዛሙርቱ ጋር የዋለው በሥራ ተወጥሮ ነው። አመሻሹ ላይ የቅፍርናሆም ሰዎች የታመሙ ሰዎችን እንዲፈውስ አመጡለት። ኢየሱስ ብቻውን ለመሆን ጊዜ አላገኘም።

በሚቀጥለው ቀን ገና ጎህ ሳይቀድ ኢየሱስ ብቻውን ወደ ውጭ ወጣ። ወደ አባቱ ለመጸለይ ጭር ወዳለ አካባቢ ሄደ። ሆኖም በዚህ ሁኔታ ብዙም አልቆየም። “ስምዖንና ከእሱ ጋር የነበሩት” ኢየሱስን ሲያጡት እሱን ፍለጋ ወጡ። ኢየሱስ ያረፈው ጴጥሮስ ቤት በመሆኑ እሱን ለመፈለግ ጴጥሮስ ቅድሚያውን ወስዶ ሊሆን ይችላል።—ማርቆስ 1:36፤ ሉቃስ 4:38

ኢየሱስን ሲያገኙት ጴጥሮስ “ሰው ሁሉ እየፈለገህ ነው” አለው። (ማርቆስ 1:37) የቅፍርናሆም ሰዎች ኢየሱስ እነሱ ጋ እንዲቆይ ቢፈልጉ የሚያስገርም አይደለም። ያደረገላቸውን ነገር ከልብ ስላደነቁ ‘እንዳይሄድባቸው ለመኑት።’ (ሉቃስ 4:42) ይሁንና ኢየሱስ ወደ ምድር የመጣበት ዋነኛ ዓላማ እንዲህ ዓይነት ተአምራዊ ፈውስ መፈጸም ነው? ደግሞስ ሥራውን ማከናወን ያለበት እዚህ አካባቢ ብቻ ነው? እሱ ስለዚህ ጉዳይ ምን አለ?

ኢየሱስ በአቅራቢያው ወደምትገኝ ከተማ እያመለከተ ከጴጥሮስ፣ እንድርያስ፣ ያዕቆብና ዮሐንስ ጋር ሲያወራ

ኢየሱስ ለደቀ መዛሙርቱ እንዲህ ሲል መለሰላቸው፦ “በዚያም እንድሰብክ በአቅራቢያ ወዳሉት ከተሞች እንሂድ፤ የመጣሁት ለዚሁ ነውና።” ኢየሱስ አብሯቸው እንዲቆይ ለጠየቁት ሰዎች ደግሞ “ለሌሎች ከተሞችም የአምላክን መንግሥት ምሥራች ማወጅ አለብኝ፤ ምክንያቱም የተላክሁት ለዚህ ዓላማ ነው” አላቸው።—ማርቆስ 1:38፤ ሉቃስ 4:43

አዎ፣ ኢየሱስ ወደ ምድር የመጣበት ትልቁ ዓላማ ስለ አምላክ መንግሥት ለመስበክ ነው። ይህ መንግሥት የአባቱን ስም የሚያስቀድስ ከመሆኑም ሌላ የሰው ልጆችን ችግሮች ለዘለቄታው ያስወግዳል። ኢየሱስ ተአምራዊ ፈውስ ማከናወኑ በአምላክ የተላከ መሆኑን ያረጋግጣል። ከዚህ ጋር በሚመሳሰል መልኩ ከበርካታ ዘመናት በፊት ሙሴም ከአምላክ የተላከ ለመሆኑ ማስረጃ እንዲሆን ሲል አስደናቂ ነገሮችን አድርጓል።—ዘፀአት 4:1-9, 30, 31

ኢየሱስ በሌሎች ከተሞች ለመስበክ ቅፍርናሆምን ለቆ ሲወጣ አራቱ ደቀ መዛሙርቱም አብረውት ተጓዙ። አራቱ ደቀ መዛሙርት፣ ጴጥሮስና ወንድሙ እንድርያስ እንዲሁም ዮሐንስና ወንድሙ ያዕቆብ ናቸው። ኢየሱስ ከእሱ ጋር እየተጓዙ የሚያገለግሉ የመጀመሪያዎቹ የሥራ ባልደረቦቹ እንዲሆኑ ከአንድ ሳምንት በፊት ጥሪ አቅርቦላቸው ነበር።

ኢየሱስ ከእነዚህ አራት ደቀ መዛሙርቱ ጋር ሆኖ በገሊላ እየተዘዋወረ ያከናወነው ስብከት እጅግ የተሳካ ነበር! እንዲያውም ስላከናወናቸው ነገሮች በሰፊው ተወራ። “ስለ እሱም የተወራው ወሬ በመላዋ ሶርያ” እንዲሁም ዲካፖሊስ ተብሎ በሚጠራው አሥሩ ከተሞች የሚገኙበት ክልል እና ከዮርዳኖስ ወንዝ ማዶ ባሉት አካባቢዎች ሁሉ ተዳረሰ። (ማቴዎስ 4:24, 25) ከእነዚህ አካባቢዎች እንዲሁም ከይሁዳ የመጡ እጅግ ብዙ ሰዎች ኢየሱስንና ደቀ መዛሙርቱን ተከተሏቸው። ብዙዎች የታመሙ ሰዎችን ወደ እሱ አመጡ። ኢየሱስም ቢሆን አላሳፈራቸውም፤ የታመሙትን ፈወሰ፣ ጋኔን የያዛቸውን ሰዎችም ርኩስ መንፈሱን አስወጣላቸው።

  • ኢየሱስ በቅፍርናሆም ቀኑን ሙሉ በሥራ ተጠምዶ ካሳለፈ በኋላ በነጋታው ማለዳ ላይ ምን ተፈጸመ?

  • ኢየሱስ ወደ ምድር የተላከው ለምንድን ነው? የፈጸማቸው ተአምራት ዓላማስ ምንድን ነው?

  • ኢየሱስ በገሊላ እየተዘዋወረ ሲሰብክ እነማን አብረውት ነበሩ? ላከናወናቸው ነገሮች ሰዎች ምን ምላሽ ሰጥተዋል?

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ