የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • lfb ትምህርት 9 ገጽ 28-ገጽ 29 አን. 1
  • በመጨረሻ ልጅ ወለዱ!

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • በመጨረሻ ልጅ ወለዱ!
  • ከመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች ምን ትማራለህ?
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • አምላክ “ልዕልት” ብሎ ጠርቷታል
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (ለሕዝብ የሚሰራጭ)—2017
  • አብርሃም እና ሣራ—እምነታቸውን መኮረጅ ትችላለህ!
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2004
  • “አንቺ በጣም ውብ ሴት ነሽ”
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (ለሕዝብ የሚሰራጭ)—2017
  • አብርሃም ማን ነበር?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2012
ለተጨማሪ መረጃ
ከመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች ምን ትማራለህ?
lfb ትምህርት 9 ገጽ 28-ገጽ 29 አን. 1
መላእክቱ አብርሃምን ሲያነጋግሩት ሣራ ድንኳን ውስጥ ሆና ስትሰማ

ትምህርት 9

በመጨረሻ ልጅ ወለዱ!

አብርሃምና ሣራ ተጋብተው ለረጅም ጊዜ ኖረዋል። በዑር የነበራቸውን ምቹ ቤት ትተው በድንኳን እየኖሩ ነበር። ሆኖም ሣራ በይሖዋ ትታመን ስለነበር አላጉረመረመችም።

ሣራ ልጅ ማግኘት በጣም ትፈልግ ስለነበር አብርሃምን ‘አገልጋዬ አጋር ልጅ ብትወልድ ልጁ እንደ ራሴ ልጅ ይሆናል’ አለችው። ከጊዜ በኋላ አጋር ወንድ ልጅ ወለደች። የልጁ ስም እስማኤል ይባላል።

ሣራ እርጉዝ ሆና

ከብዙ ዓመታት በኋላ ማለትም አብርሃም 99 ዓመት፣ ሣራ ደግሞ 89 ዓመት ሲሆናቸው ሦስት እንግዶች ወደ እነአብርሃም ቤት መጡ። አብርሃም እንግዶቹን ዛፍ ሥር እንዲያርፉና ምግብ እንዲበሉ ጠየቃቸው። እነዚህ እንግዶች እነማን እንደሆኑ ታውቃለህ? መላእክት ነበሩ! እነሱም አብርሃምን ‘በሚቀጥለው ዓመት በዚህ ጊዜ ሚስትህ ወንድ ልጅ ትወልዳለች’ አሉት። ሣራ ድንኳኑ ውስጥ ሆና የሚሉትን ትሰማ ነበር። ይህን ስትሰማ ‘አሁን እንዲህ ካረጀሁ በኋላ ልጅ መውለድ እችላለሁ?’ ብላ በማሰብ ሳቀች።

በቀጣዩ ዓመት ልክ የይሖዋ መልአክ እንደተናገረው ሣራ ወንድ ልጅ ወለደች። አብርሃም ልጁን ይስሐቅ ብሎ ስም አወጣለት፤ ይስሐቅ ማለት “ሳቅ” ማለት ነው።

ይስሐቅ አምስት ዓመት አካባቢ ሲሆነው ሣራ፣ እስማኤል በይስሐቅ ላይ ሲያሾፍበት አየች። ልጇን ለመጠበቅ ስትል አጋርንና እስማኤልን እንዲያባርራቸው አብርሃምን ጠየቀችው። አብርሃም መጀመሪያ ላይ እንደዚህ ማድረግ አልፈለገም ነበር። ሆኖም ይሖዋ ለይስሐቅ ጥበቃ ማድረግ ስለፈለገ አብርሃምን እንዲህ አለው፦ ‘ሣራ የምትልህን ስማ። እስማኤልን እኔ እንከባከበዋለሁ። የገባሁልህ ቃል የሚፈጸመው ግን በይስሐቅ በኩል ነው።’

አጋርና እስማኤል ሲሄዱ ሣራና ይስሐቅ ቆመው እየተመለከቷቸው ነው

“ሣራም የተስፋን ቃል የሰጠው እሱ ታማኝ እንደሆነ አድርጋ ስላሰበች . . . ዘር ለመፀነስ በእምነት ኃይል አገኘች።”—ዕብራውያን 11:11

ጥያቄ፦ ሣራ መላእክቱ ለአብርሃም ምን ብለው ሲነግሩት ሰማች? ይሖዋ ለይስሐቅ ጥበቃ ያደረገለት እንዴት ነው?

ዘፍጥረት 16:1-4, 15, 16፤ 17:25-27፤ 18:1-15፤ 21:1-14፤ ዕብራውያን 11:11

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ