የክፍል 7 ማስተዋወቂያ
ይህ ክፍል የንጉሥ ሳኦልንና የንጉሥ ዳዊትን የሕይወት ታሪክ የያዘ ሲሆን ወደ 80 በሚጠጉ ዓመታት ውስጥ የተከናወኑ ነገሮችን ያወሳል። ሳኦል መጀመሪያ ላይ ትሑትና አምላክን የሚፈራ ሰው ነበር፤ ከጊዜ በኋላ ግን የአምላክን መመሪያ ለመቀበል ፈቃደኛ ሳይሆን ቀርቷል። በዚህም የተነሳ ይሖዋ ሳኦልን ተወው፤ ከዚያም ዳዊትን የእስራኤል ንጉሥ አድርጎ እንዲቀባው ሳሙኤልን አዘዘው። ሳኦል በቅናት ተነሳስቶ ዳዊትን ለመግደል በተደጋጋሚ ቢሞክርም ዳዊት ለመበቀል አልሞከረም። የሳኦል ልጅ ዮናታን፣ ይሖዋ የመረጠው ዳዊትን እንደሆነ ስለተገነዘበ ለዳዊት ታማኝ ሆኗል። ዳዊት ከባድ ኃጢአት የሠራባቸው ጊዜያት ቢኖሩም ምንጊዜም የይሖዋን ተግሣጽ ለመቀበል ፈቃደኛ ነበር። ወላጅ ከሆንክ፣ ልጅህ የይሖዋን ዝግጅቶች መደገፍ ያለውን ጥቅም እንዲገነዘብ እርዳው።