መዝሙር 133
በወጣትነታችሁ ይሖዋን አምልኩ
በወረቀት የሚታተመው
1. ላምላክ ያደርን ወጣቶች በሙሉ
ዋጋ አለን፣ ውድ ነን በፊቱ።
አምላካችን እጅግ ይወደናል፤
በረከቶቹም ይከተሉናል።
2. ወላጆቻችን ያስቡልናል፤
ሁሌ ልናከብራቸው ይገባል።
በሰው ፊት ሞገስ ያስገኝልናል፤
በአምላክም ዘንድ ያስወድደናል።
3. ይሖዋን እናስብ ወጣት ሳለን፤
ለእውነትም አድናቆት ይኑረን።
ምርጣችንን ለአምላክ እንስጠው፤
በሕይወታችን እናስደስተው።