መዝሙር 149
የድል መዝሙር
በወረቀት የሚታተመው
1. ላምላክ ዘምሩ፤ ታላቅ ስሙ ገናና ሆኗል።
የግብፅን ሠራዊት በቀይ ባሕር ውስጥ ጥሏል።
ያህን አክብሩት፤
የለም እሱን የሚተካከል።
ይሖዋ ነው ስሙ፤
ታላቅ ድል ተቀዳጅቷል።
(አዝማች)
አምላካችን ወደር የለህም፤
አንተ አትለወጥ ለዘላለም።
በቅርብ በማጥፋት ጠላቶችህን፣
ታስቀድሳለህ ስምህን።
2. ዛሬም ልዑሉን ’ሚቃወሙ ብሔራት ሁሉ፣
ኃያላን ቢሆኑም
ተዋርደው ይጠፋሉ።
ጥፋት ይመጣል፤
ከአርማጌዶን አያመልጡም።
በቅርብ ጊዜ ሁሉም
ያውቃሉ ያምላክን ስም።
(አዝማች)
አምላካችን ወደር የለህም፤
አንተ አትለወጥ ለዘላለም።
በቅርብ በማጥፋት ጠላቶችህን፣
ታስቀድሳለህ ስምህን።