ሣጥን 13ሀ
የተለያዩ ቤተ መቅደሶች፣ የተለያዩ ትምህርቶች
ሕዝቅኤል በራእይ ያየው ቤተ መቅደስ፦
ሕዝቅኤል በባቢሎን ለነበሩ አይሁዳውያን ግዞተኞች ስለዚህ ቤተ መቅደስ ተናግሯል
ብዙ መሥዋዕቶች የሚቀርቡበት መሠዊያ አለው
ይሖዋ ለንጹሕ አምልኮ ያወጣውን መሥፈርት ጎላ አድርጎ ይገልጻል
ትኩረታችን በ1919 በጀመረው መንፈሳዊ ተሃድሶ ላይ እንዲያርፍ ያደርጋል
ታላቁ መንፈሳዊ ቤተ መቅደስ፦
ጳውሎስ ለዕብራውያን ክርስቲያኖች በጻፈው ደብዳቤ ላይ አብራርቶታል
አንድ መሥዋዕት ብቻ “ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ” የቀረበበት መሠዊያ አለው (ዕብ. 10:10)
የማደሪያ ድንኳኑና ሌሎቹ ቤተ መቅደሶች ጥላ የሆኑለትን መንፈሳዊ እውነታ ማለትም ይሖዋ በክርስቶስ ቤዛዊ መሥዋዕት አማካኝነት ለንጹሕ አምልኮ ያደረገውን ዝግጅት ያመለክታል
ትኩረታችን ክርስቶስ ታላቅ ሊቀ ካህናት በመሆን ከ29 እስከ 33 ዓ.ም. ባከናወነው ሥራ ላይ እንዲያርፍ ያደርጋል