የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w91 1/15 ገጽ 21
  • “ይህ ሥጋዬ ነው“

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • “ይህ ሥጋዬ ነው“
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1991
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ‘ይህን ለመታሰቢያዬ አድርጉት’
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2013
  • የጌታ እራት ለአንተ ትልቅ ትርጉም አለው
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2003
  • የጌታ እራት—አምላክን የሚያስከብር በዓል
    ትክክለኛው የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ምንድን ነው?
  • የጌታን እራት ማክበር ያለብን ለምንድን ነው?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2003
ለተጨማሪ መረጃ
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1991
w91 1/15 ገጽ 21

“ይህ ሥጋዬ ነው“

“እንካችሁ ብሉ፣ ይህ ሥጋዬ ነው።” (ማቴዎስ 26:26)

ኢየሱስ የጌታን እራት ባቋቋመበት ጊዜ ይህን ቃል ተናገረና ያልቦካ ቂጣ ለደቀመዛሙርቱ ሰጠ። ይሁን እንጂ “ይህ ሥጋዬ ነው” ሲል ምን ማለቱ ነበር?

የዚህ ጥያቄ መልስ ለሮማ ካቶሊኮች በጣም አስፈላጊ ነው ምክንያቱም የምሥጢረ ቁርባን እምነታቸው የተመሠረተው በዚህ የኢየሱስ ቃል ላይ ነው። በዚህ እምነት መሠረት ካቶሊኮች በቅዳሴ ጊዜ ኅብስቱን ሲወስዱ ኅብስቱ ተለውጦ እውነተኛ የክርስቶስ ሥጋ ይሆናል። በዚህም ምክንያት የአዲሲቱ ዓለም የቅዱሳን ጽሑፎች ትርጉም የኢየሱስን ቃል “እንካችሁ፣ ይህ ሥጋዬ ማለት ነው” ብሎ መተርጎሙን አጥብቀው ይቃወማሉ። ይህ አተረጓጎም ቂጣው የኢየሱስ ሥጋ ራሱ ሳይሆን የኢየሱስ ሥጋ ምሳሌ መሆኑን ያመለክታል። ትክክለኛውን ሐሣብ የሚያስተላልፈው ግን የትኛው አተረጓጎም ነው?

“ነው” ወይም “ማለት” ተብሎ የተተረጎመው የግሪክኛ ቃል ኤስቲን ነው። በመሠረቱ “ነው” የሚል ትርጉም ቢኖረውም “ማመልከት፣ ምሳሌ መሆን” ማለት ሊሆን ይችላል። በዚህ አገባብ ትክክል የሚሆነው የትኛው አተረጓጎም ነው?

ላ ሳግራዳ ኤስኩሪቱራ ቴክስቶ ኮሜንታሪዮ ፖር ፕሮፌሶሬስ ደ ላ ኮምፓኛ ደ ጀሱስ ኑዌቮ ቴስታሜንቶ (ቅዱስ ጽሑፉ፣ ሐሣብን ማብራሪያ በኢየሱስ ቡድን ፕሮፌሰሮች፣ አዲስ ኪዳን) የተባለው የስፓንኛ የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉም በማቴዎስ 26:26 ግርጌ ባሰፈረው ማስታወሻ ላይ ያለውን ማስተዋል ተገቢ ነው። እንዲህ ይላል፣ ‘አተረጓጎሙ ከሰዋስው አንጻር ሲታይ ያመለክታል ወይም ምሳሌ ይሆናል ወይም ቃል በቃል ነው ሊባል ይቻላል። ያመለክታል የሚል ትርጉም የተሰጠባቸው ምሳሌዎች የሚከተሉት ናቸው፦ ዘፍጥረት 41:26፤ ሕዝቅኤል 5:5፤ ዳንኤል 7:17፤ ሉቃስ 8:11፤ ማቴዎስ 13:38፤ 16:18፤ ገላትያ 4:24፤ ራእይ 1:20። ነው የሚል ትርጉም ስለመሰጠቱ ደግሞ የምሳሌነት ወይም የምልክትነት ትርጉም እንደሌለው ከሚጠቁሙት የእምነት ድንጋጌዎችና የቀድሞዋ ቤተክርስቲያን ለዚህ ሐረግ ከሰጠችው ትርጉም መረዳት ይቻላል።’

ይህ የሮማ ካቶሊክ የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉም በግልጽ እንደሚያመለክተው የኢየሱስ አነጋገር ሁለቱም ዓይነት ትርጉም ሊሰጠው ይችላል። እንዲያውም ኤስቲን የሚለው የግሪክኛ ቃል በካቶሊክ ጀሩሳሌም ባይብል ውስጥ በተለያዩ ቦታዎች “ትርጉሙም” የሚል ፍቺ ተሰጥቶታል። (ማቴዎስ 12:7) ታዲያ ለማቴዎስ 26:26 ትክክለኛ የሚሆነው አተረጓጎም የትኛው ነው? ኢየሱስ ይህን ቃል በተናገረበት ጊዜ በፍጹም ሥጋ ይኖር ስለነበረ ለተከታዮቹ የሰጣቸው ቂጣ ቃል በቃል ሥጋው ሊሆን አይችልም ነበር። ከዚህም በላይ ፍጹም የሆነው መላ ሰብዓዊ ሕይወቱ ቤዛዊ መሥዋዕት ሆኖ ተሰጥቶአል። (ቆላስይስ 1:21-23) ስለዚህ ከሁሉ የሚሻለው አተረጓጎም “ይህ ሥጋዬ ማለት ነው” የሚለው ነው። ያልቦካው ቂጣ ለሰው ልጆች በሙሉ የሚሰዋውን የኢየሱስ ሥጋ ያመለክታል።

የራስህ መጽሐፍ ቅዱስ “ይህ ሥጋዬ ነው” ብሎ ቢተረጉምም እንኳን ግራ መጋባት አይገባህም። ኢየሱስ ብዙ ጊዜ እንዲሁ ባለ የአነጋገር ዘይቤ ተጠቅሞአል። “እኔ በር ነኝ” እና “እውነተኛ የወይን ግንድ እኔ ነኝ” ባለ ጊዜ እርሱ ቃል በቃል በር ወይም የወይን ግንድ እንደሆነ የተረዳ ሰው አልነበረም። (ዮሐንስ 10:7፤ 15:1) ዘ ኒው ጀሩሳሌም ባይብል እንደሚለውም “ይህ ጽዋ አዲሱ ኪዳን ነው” ባለ ጊዜ ጽዋው ቃል በቃል አዲሱ ኪዳን ነው ብሎ የተረዳ ሰው አልነበረም። (ሉቃስ 22:20) በተመሳሳይም ቂጣው ሥጋዬ ነው ባለ ጊዜ ቂጣው ሥጋውን እንደሚወክል ወይም እንደሚያመለክት አድርገን መረዳት ይገባናል።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ