የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w91 4/15 ገጽ 26-27
  • “የጌታ ቀን”

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • “የጌታ ቀን”
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1991
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • “ኢየሱስ ክርስቶስ ጌታ ነው” እንዴትና መቼ?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1994
  • የራእይ መጽሐፍ የያዘው መልእክት ምንድን ነው?
    የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው
  • የራእይን መጽሐፍ በማንበብ ተደሰቱ
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1999
  • ዮሐንስ ክብር የተቀዳጀውን ኢየሱስን ተመለከተ
    ራእይ—ታላቁ መደምደሚያው ደርሷል!
ለተጨማሪ መረጃ
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1991
w91 4/15 ገጽ 26-27

“የጌታ ቀን”

“በጌታ ቀን በመንፈስ ነበርሁ።” (ራእይ 1:10) በመጽሐፍ ቅዱሱ የራእይ መጽሐፍ የመጀመሪያ ምዕራፍ ውስጥ ከላይ የተጠቀሰውን የተናገረው በዕድሜ የሸመገለው ሐዋርያው ዮሐንስ ነበር። እርሱ የተናገረው ይህ ቃል ቀጥሎ ሊገልጻቸው ያሉት አስደናቂ ራእዮች የሚፈጸሙበትን ጊዜ ለማወቅ ይረዳናል።

ይሁን እንጂ ራእይ 1:10 ከላይ እንደተገለጸው ሆኖ መተርጎሙን ሁሉም ሰዎች አይስማሙም። ለምሳሌ ያህል ጆርግ ዚንክ የተባለው የጀርመን የመጽሐፍ ቅዱስ ተርጓሚ “በመንፈስ ቅዱስ ተሞልቼ ነበር​—ቀኑም እሁድ ነበር” ሲል ተርጉሞታል። ሆኖም አብዛኞቹ የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉሞች ቴይ ኪሪአኪ ሄሜራይ የሚለውን ሐረግ “የጌታ ቀን” ሲሉ ተርጉመውታል። ሆኖም ብዙዎቹ በግርጌ ማስታወሻቸው ላይ እሁድን እንደሚያመለክት ይገልጻሉ። ይህ ትክክል ነውን?

የካቶሊክ የማጣቀሻ መጽሐፍ የሆነው የጀርመኑ ሄርደርስ ባይብል ኮመንታር እንደሚከተለው በማለት ከዚህ በስተጀርባ ያለውን ምክንያት ያብራራል፦ “እዚህ ላይ [በራእይ 1:10 ላይ] የተጠቀሰው ‘የጌታ ቀን’ በመባል የሚታወቀው የመጨረሻው የፍርድ ቀን ሳይሆን በሣምንት ውስጥ ያለ አንድ የተወሰነ ቀን ነው። የጥንት ክርስቲያኖች ከመጀመሪያው መቶ ዘመን እኩሌታ ጀምሮ የሣምንቱን የመጀመሪያ ቀን እንደ ዋነኛ የቤተ ክርስቲያን አገልግሎት መፈጸሚያ ቀን አድርገው ማክበር ጀመሩ። (ሥራ 20:7፤ 1 ቆሮ. 16:2)” ነገር ግን በዚህ የማጣቀሻ ጽሑፍ ላይ የተጠቀሱት ሁለት ጥቅሶች የመጀመሪያው መቶ ዘመን ክርስቲያኖች የሣምንቱን የመጀመሪያ ቀን “እንደ ዋነኛ የቤተ ክርስቲያን አገልግሎት መፈጸሚያ ቀን” አድርገው ይመለከቱት እንደነበረ በምንም መንገድ አያረጋግጡም።

የመጀመሪያው ጥቅስ ማለትም ሥራ 20:7 የሚገልጸው ጳውሎስና የጉዞ ጓደኞቹ ከጢሮአዳ ክርስቲያኖች ጋር ከሣምንቱ በመጀመሪያው ቀን ለምግብ እንደተሰበሰቡ ነው። ጳውሎስ በሚቀጥለው ቀን ሊሄድ ስለነበረ ለተወሰነ ጊዜ እንደገና ስለማያያቸው ከእነርሱ ጋር ረጅም ጊዜ ወስዶ ለመነጋገር በአጋጣሚው ተጠቀመ።

ሁለተኛው ጥቅስ ማለትም 1 ቆሮንቶስ 16:2 ደግሞ በይሁዳ ለነበሩት ችግረኛ ወንድሞች መዋጮ ለማድረግ “በየሣምንቱ በፊተኛው ቀን” እንደቀናቸው ገንዘብ እንዲያስቀምጡ የሚያበረታታ ነበር። ምሁሩ አዶልፍ ዴሲማን ይህ ቀን የደሞዝ ክፍያ ቀን ነው የሚል ሐሳብ አቅርበዋል። ያም ሆነ ይህ በሣምንቱ ውስጥ በእጅ ላይ ያለ ገንዘብ ሊያልቅ ስለሚችል ጳውሎስ በዚህ ቀን ገንዘብ ስለ ማስቀመጥ ሐሳብ መስጠቱ ምክንያታዊ ነው።

ሐዋርያት በኖሩበት ዘመን ክርስቲያኖች በአሁኑ ጊዜ እሁድ ተብሎ የሚጠራውን ቀን ለዘወትር ስብሰባዎቻቸው ወይም አምልኮታቸው እንደተለየ የክርስቲያን ሰንበት ዓይነት አድርገው ይመለከቱት እንደነበር በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የተገለጸ ምንም ነገር የለም። እሁድ በዚህ መልክ መታየት የጀመረውና “የጌታ ቀን” የሚል ስያሜ ያገኘው ከሐዋርያት ሞት በኋላ ነው። ይህም ለውጥ በክርስቶስና በሐዋርያቱ የተተነበየው ክህደት ክፍል ነው።​—ማቴዎስ 13:36-43፤ ሥራ 20:29, 30፤ 1 ዮሐንስ 2:18

ታዲያ “የጌታ ቀን” ምንድን ነው? በራእይ 1:10 ዙሪያ ያለው ሐሳብ ቀኑ ጌታ የተባለው የኢየሱስ ቀን እንደሆነ ያመለክታል። የአምላክ ቃል የሰውን ልጅ የፍርድ ጊዜና ገነት እንደገና የምትመለስበትን ጊዜ ‘የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ቀን’ በማለት ይገልጸዋል።​—1 ቆሮንቶስ 1:8፤ 15:24-26፤ ፊልጵስዩስ 1:6, 10፤ 2:16

ሐንስ ብሩንስ ከተጨማሪ ማብራሪያ ጋር በተረጎሙት አዲስ ኪዳን ትርጉም ውስጥ እንደሚከተለው በማለት የተናገሩት ትክክል ነበር፦ “አንዳንዶች እርሱ [ዮሐንስ] የተናገረው ስለ እሁድ ነው ይላሉ፤ ይሁን እንጂ በኋላ የሚመጡት መግለጫዎች በሙሉ እንደሚያመለክቱት እርሱ የጠቀሰው ምሳሌያዊውን የጌታ ቀን እንደሆነ መረዳት ይቻላል።” ደብልዩ ኢ ቫይን “‘የጌታ ቀን’ . . . በዓለም ላይ ፍርዱን የሚገልጽበት ቀን ነው” ብለዋል። የፍሪዝ ራይንከር ሌክስኮን ኦፍ ዘ ባይብል “የጌታ ቀን” በግልጽ የሚያመለክተው “የፍርድ ቀንን” እንደሆነ ይናገራል።

“የጌታ ቀን” ስለሚለው አገላለጽ ትክክለኛ ግንዛቤ ማግኘታችን መላውን የራእይ መጽሐፍ ለመረዳት ያስችለናል። ከዚህም በላይ ይህ ቀን ቀደም ሲል እንደጀመረ ማስረጃ አለ። እንግዲያው ‘የትንቢቱን ቃል መስማታችንና በውስጡ የተጻፉትን መጠበቃችን’ ምንኛ አስፈላጊ ነው!​—ራእይ 1:3, 19

[በገጽ 27 ላይ የሚገኝ ሥዕል]

“ራእይ​—ታላቁ መደምደሚያው ደርሷል” በተባለው መጽሐፍ ውስጥ በራእይ መጽሐፍ ውስጥ ላሉት ጥቅሶች ሁሉ ግልጽና ትኩስ የሆነ ማብራሪያ ቀርቧል። መጽሐፍ ቅዱስን ለማጥናት የሚረዳውን ይህን አስደናቂ መጽሐፍ ከይሖዋ ምሥክሮች ማግኘት ይቻላል

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ