የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w91 9/1 ገጽ 9
  • የመንግሥቱ አዋጅ ነጋሪዎች ሪፖርት

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የመንግሥቱ አዋጅ ነጋሪዎች ሪፖርት
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1991
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • “እንዲህ ያለ ፍቅር በማየታችን ልባችን በጣም ተነክቷል”
    ንቁ!—2017
  • ቲኦክራሲያዊ ዜናዎች
    የመንግሥት አገልግሎታችን—1994
  • ከአምላክና ከእናቴ ጋር ሰላም መፍጠር
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2015
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1991
w91 9/1 ገጽ 9

የመንግሥቱ አዋጅ ነጋሪዎች ሪፖርት

በካትማንዱ አመኑ

አንዲት አርቲስት በ1980 በፈረንሳይ ውስጥ በብሪታኒ እውነትን መፈለግ ጀመረች። ከጴንጤቆስጤዎች ጋር ውይይቶችን አድርጋለች፣ የምሥራቅ ሃይማኖቶችንም አጥንታለች፣ ሆኖም ምንም ልትረካ አልቻለችም። ከዚያ ቆይቶ ከአንድ የይሖዋ ምስክር ጋር መወያየት ጀምራ ወዲያውኑ አቆመች። ከአንድ ከሌላ አርቲስት ጋር ተገናኘችና ከእርሱ ጋር መሥራትና መኖር ጀመረች።

ይህ ከሆነ ከጥቂት ጊዜ በኋላ እነዚህ ያልተጋቡ ወንድና ሴት ኔፓልን ለመጎብኘት ወሰኑ። በዚህችም አገር ውበትና ሰላም በጣም ተደነቁ፣ ነገር ግን በእነርሱ የምዕራባውያን አመለካከት ትክክለኛ መስሎ ባልታያቸው ሰውን በጎሣ በሚያበላልጠው እምነት ቅር ተሰኙ።

ወደ ፈረንሳይ ሲመለሱም ሴትየዋ ለጓደኛዋ አብረው መጽሐፍ ቅዱስ እንዲያጠኑ አሳብ አቀረበች፣ ያላሰበችው ነገር ቢሆንም ለማጥናት ተስማማ። ከሁለት ዓመት በፊት ያወያዩዋት ከነበሩት የይሖዋ ምስክሮች ጋር ተገናኙ። በመጀመሪያ በመጽሐፍ ቅዱስ ብቻ ይጠቀሙ ነበር። ውሎ አድሮ ግን ወደ ዘላለም ሕይወት የሚመራ እውነት በተሰኘውና በምድር ላይ በገነት ለዘላለም መኖር ትችላለህ በተሰኙት መጻሕፍት ለመጠቀም ተስማሙ። በአንድ ዓመት ውስጥ አደንዛዥ ዕፅ መውሰዳቸውን አቆሙ።

ኔፓልን እንደገና ለሁለት ወራት ከጎበኙ በኋል ጥናታቸውን ወደቀጠሉበት ወደ ፈረንሳይ ተመለሱ። ሲጋራ ማጨሳቸውን፣ ወደ መጠጥ ቤቶችና ወደየምሽት ዳንስ ቤቶች መሄዳቸውን አቁመው በይሖዋ ምስክሮች ስብሰባዎች ላይ መገኘት ጀምሩ። ሆኖም ለዘላለም መኖር የተባለውን መጽሐፍ አጥንተው ከጨረሱ በኋላ ጥናታቸውን ለማቆም ወሰኑ።

እንደገና ወደ ኔፓል ሄደው ከሂማላያ ተራሮች ግርጌ በአንድ ትንሽ ቤት ውስጥ መኖር ጀመሩ። አንድ ቀን ሙሉ ልብስና ክራባት ያደረገ አንድ ሽማግሌ ሰው በራቸውን አንኳኳ። ሴትየዋ እቤት ውስጥ ብቻዋን ነበረች። ስዕላቸውን ለማየት የመጣ የስዕል ደላላ መስሏት ነበር። በፈረንሳይ ውስጥ ሲያስጠናቸው የነበረው ሰው ምትክ ሆኖ የመጣ የይሖዋ ምስክር ነበር፣ ይህም ምንም ያላሰበችው ነበር። ጥቂት ቆየት ብሎ ጓደኛዋ ወደ ቤቱ ተመለሰ። ለሁለት ሰዓትም ውይይት ተደረገ።

ከጥቂት ቀናት በኋላም ወንድየውና ሴቲቱ በካትማንዱ በሚገኘው የይሖዋ ምስክሮች ስብሰባ ላይ ተገኙ። በተሰብሳቢዎቹም ንፁህ አለባበስ በጣም ተደነቁ። በፈረንሳይ በነበሩበት ጊዜ በስብሰባዎች ላይ ያዩትን ያንኑን ዓይነት ወንድማዊ ፍቅርና ደስታ እዚህም ተመለከቱ። በተጨማሪም የመጡት ከተለያዩ ጎሣዎች ቢሆንም በዚያ የነበሩት የኔፓል ሰዎች ያላቸውን አንድነት ተመለከቱ። አሁን የይሖዋ ድርጅት ይህ ነው ብለው አመኑ።

ከአንድ ወር በኋላ ወደ ፈረንሳይ ተመለሱና ወዲያውኑ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናታቸውንና በስብሰባዎች ላይ መገኘታቸውን ቀጥሉ። ተጋቡ፣ በምሥክርነቱም ሥራ መካፈል ጀመሩ፤ በመጨረሻም ተጠመቁ። ባልየው አሁን ዲያቆን ሆኖ ሲያገለግል ሚስቲቱ ደግሞ አዘውትራ በረዳት አቅኚነት አገልግሎት ትካፈላለች። በእርግጥም ትክክለኛ የልብ ሁኔታ ያላቸው ሰዎች እንዲያድጉና አምላኪዎቹ እንዲሆኑ የይሖዋ መንፈስ ይረዳቸዋል።​—ራእይ 7:15-17

[በገጽ 9 ላይ የሚገኝ ሣጥን/ካርታ]

ኔፓል

የሕዝብ ብዛት - 17,712,221

የ1990 ከፍተኛ የአስፋፊዎች ቁጥር - 63

ሬሾ፣ 1 አስፋፊ ለ- 281,146

አማካይ አቅኚዎች - 10

የጉባኤዎች ቁጥር - 1

አማካይ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች- 107

የመታሰቢያው በዓል ተሰብሳቢዎች - 220

[ካርታ]

(መልክ ባለው መንገድ የተቀናበረውን ለማየት ጽሑፉን ተመልከት)

ኔፓል

ሕንድ

[በገጽ 9 ላይ የሚገኝ ሥዕል]

Market scene in Kathmandu, Nepal

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ