የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w91 9/1 ገጽ 30-31
  • የወንድ ተግባር

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የወንድ ተግባር
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1991
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ልጆች የሚያስፈልጋቸውን ትኩረት መስጠት
    ንቁ!—2005
  • ለቤተሰባችሁ መዳን ጠንክራችሁ ሥሩ
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1994
  • ልጆችን በአምላክ ተግሣጽ ማሳደግ
    ንቁ!—2004
  • አምላክን በአንድነት የሚያገለግሉ ብዙ ልጆች ያሏቸው ቤተሰቦች
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1999
ለተጨማሪ መረጃ
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1991
w91 9/1 ገጽ 30-31

የወንድ ተግባር

“ሮፓ፣ ዛፓቶ፣ ካዛ፣ ይ ኮሚዳ!” እነዚህ ቃላት አንድ ወንድ ለቤተሰቡ እንዲያቀርባቸው የሚጠበቁበትን አራት መሠረታዊ ነገሮች ማለትም ልብስ፣ ጫማ፣ መጠለያንና ምግብን ከሚዘረዝር ከአንድ የቆየ የስፓኒሽ ዘፈን የተወሰዱ ናቸው። ኃላፊነት የሚሰማቸው አብዛኞቹ ወንዶች ይህንን ሸክም በኩራት ሊሸከሙት ይሞክራሉ።

ይሁን እንጂ አንተ ቤተሰብ ያለህ ሰው ከሆንክ ለቤተሰብህ ከላይ ከተጠቀሱት ይበልጥ አስፈላጊ የሆኑትን መንፈሳዊ ነገሮች ታሟላለህን? ወይም እንደ ብዙዎቹ ወንዶች በቤት ውስጥ የሃይማኖታዊውን ጉዳይ መከታተሉ የወንዶች ሥራ አይደለም ብለህ ታስባለህን? እንዲያውም በአንዳንድ ባሕሎች ወንዶች ልጆቻቸውን ስለ አምላክና ስለ መጽሐፍ ቅዱስ ለማስተማር ጊዜ እንዲመድቡ አይጠበቅባቸውም።

የአምላክ ቃል በተለይ ለአባወራው በቤተሰቡ ውስጥ ለአምላክ ፍቅርን የመቅረጽና ለመለኮታዊ የአቋም ደረጃዎችም ጥልቅ አድናቆትን የመገንባትን ኃላፊነት ይሰጠዋል። ለምሳሌም ያህል በኤፌሶን 6:4 ላይ የሚገኘው ጥቅስ ክርስቲያን ወንዶችን እንደሚከተለው በማለት አጥብቆ ይመክራቸዋል፦ “እናንተም አባቶች ሆይ፣ ልጆቻችሁን [በይሖዋ (አዓት)] ምክርና በተግሣጽ አሳድጉአቸው እንጂ አታስቆጡአቸው።”

ይሁን እንጂ እነዚህን ቃላት የሚያውቁ አንዳንዶች ጥቅሱ በተለይ የሚያተኩረው በተለይ አባወራ በሆነው አባት ላይ መሆኑን ሙሉ በሙሉ አይረዱት ይሆናል። ለምሳሌ ያህል የስፓኒሽና የፖርቹጋል ቋንቋ ተናጋሪ የሆኑ ግለሰቦች በኤፌሶን 6:4 ላይ የሚገኙትን እነዚህን ቃላት ለአባትና ለእናትም እንደተነገሩ አድርገው ሊረዱአቸው ይችላሉ። በእነዚህ ቋንቋዎች “አባቶች” እና “ወላጆች” የሚሉትን ቃላት ለመግለጽ የሚጠቀሙት በአንድ ቃል ነው። ይሁን እንጂ በኤፌሶን ምዕራፍ 6 ቁጥር 1 ላይ ሐዋርያው ጳውሎስ አባትንም ሆነ እናትን ለመጥቀስ “ወላጆች” የሚል ትርጉም ካለው ከጎኒውስ የወጣውን ጎኒውሲን የሚለውን የግሪክኛ ቃል ተጠቅሟል። በቁጥር 4 ላይ ግን የገባው የግሪክ ቃል “አባት” የሚል ትርጉም ያለው ፓቴሬስ ነው። አዎን፣ በኤፌሶን 6:4 ላይ ጳውሎስ የተናገራቸውን ቃላት በቀጥታ የጻፈው በቤተሰቡ ውስጥ ላለው የቤቱ ኃላፊ ወንድ ነው።

በእርግጥ በቤተሰቡ ውስጥ የመሪነቱን ቦታ የያዘ ወንድ ከሌለ ሴትየዋ ይህን ኃላፊነት መውሰድ ያስፈልጋታል። በይሖዋ እርዳታ ብዙ እናቶች ልጆቻቸውን በተሳካ ሁኔታ በይሖዋ ምክርና ተግሣጽ ለማሳደግ ያደረጉት ጥረት ተሳክቶላቸዋል። ይሁን እንጂ አንድ ክርስቲያን ወንድ ካለ የመሪነቱን ቦታ እርሱ መውሰድ ይኖርበታል። ይህን ኃላፊነት የሚዘነጋ ከሆነ ለቀረው ቤተሰብ ጥሩ የሆነ የመንፈሳዊ ምግብ ፕሮግራም ለማዘጋጀት በጣም አስቸጋሪ ይሆናል። እንደዚህ ያለው ሰው ስለ ቸልተኝነቱ በይሖዋ ተጠያቂ ይሆናል።

አምላክ ስለዚህ ነገር ያለው ስሜት በክርስቲያን ጉባኤ ውስጥ ለሚያገለግሉት የበላይ ተመልካቾችንና ለዲያቆናት በተሰጡት ብቃቶች ላይ በግልጽ የሚታይ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ ይህን ቦታ ለመያዝ የተመረጠው ሰው፦ “ልጆቹን በጭምትነት ሁሉ እየገዛ የራሱን ቤት በመልካም የሚያስተዳድር ሰው ግን የራሱን ቤት እንዲያስተዳድር ባያውቅ፣ የእግዚአብሔርን ቤተክርስቲያን እንዴት ይጠብቃታል?”ይላል።​—1 ጢሞቴዎስ 3:4, 5, 12፣ ቲቶ 1:6

አባወራ የሆነው ወንድ ደስታዎችንና የግል ምቾቶችን ስለ ልጆቹ መንፈሳዊ ደኅንነት ሲል መሥዋዕት ለማድረግ ፈቃደኛ መሆን ይኖርበታል። ዘወትር ከልጆቹ ጋር የተወሰነ መጠን ያለው ጊዜ አብሮ ለማሳለፍ አንዳንድ ጊዜ ለሌሎች ሥራዎች ከወሰነው ጊዜ ላይ መቀነስ ይኖርበት ይሆናል። (ዘዳግም 6:6, 7) ሆኖም ይህን ከአምላክ የተቀበለውን ሥራ ለሌሎች አይለቅም። ለልጆቹ ያለው ፍቅርና አሳቢነት ልብስ፣ ጫማና ምግብ ከማቅረብ የበለጠ አልፎ የሚሄድ ነው።

ልጆችን “በይሖዋ ምክርና በተግሣጽ” ማሳደግ ትግል የሚጠይቅ ሥራ ነው። በአንደኛ ደረጃ ኃላፊነቱ የወደቀው በወንዱ ላይ የሆነውም ለዚህ ነው። አንድ ክርስቲያን አባት ተግባሩን በሚገባ ሲያከናውን አምላክን የሚፈሩ ልጆቹን ከይሖዋ እንደተሰጠ በረከት አድርጎ ሊመለከታቸው ይችላል። ከመዝሙራዊው ጋር “በኃያል እጅ እንዳሉ ፍላጾች፣ የጎልማስነት ልጆች እንዲሁ ናቸው። ከእነርሱ ዘንድ ምኞቱን የሚፈጽም ብፁዕ ሰው ነው” ሊል ይችላል።​—መዝሙር 127:4, 5

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ