የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w92 11/1 ገጽ 8-9
  • ወደ ሴሎ መሄድ—ጥሩና ባለጌ ልጆች

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ወደ ሴሎ መሄድ—ጥሩና ባለጌ ልጆች
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1992
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ‘በይሖዋ ፊት አደገ’
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2010
  • ‘በይሖዋ ፊት እያደገ ሄደ’
    በእምነታቸው ምሰሏቸው
  • ሳሙኤል እውነተኛውን አምልኮ አስፋፍቷል
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2007
  • አምላክን ያገለገለ አንድ ትንሽ ልጅ
    የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች መማሪያ መጽሐፌ
ለተጨማሪ መረጃ
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1992
w92 11/1 ገጽ 8-9

የተስፋይቱ ምድር ገጽታዎች

ወደ ሴሎ መሄድ—ጥሩና ባለጌ ልጆች

የተስፋይቱ ምድር ከተሞች፣ መንደሮች ወይም አካባቢዎች ስታስቡ አንዳንድ ታዋቂ የሆኑ ወንዶችና ሴቶች ወደ አእምሮአችሁ ይመጣሉን? ምናልባት ትዝ ይሉአችሁ ይሆናል፤ ምክንያቱም ብዙዎቹ የመጽሐፍ ቅዱስ ዘገባዎች ትልልቅ ሰዎችን ስለሚጨምሩ ነው። ነገር ግን በዚያ ጊዜ ስለነበሩት ልጆችስ? በእነዚህ ገጽታዎች ውስጥ ይታዩአችኋልን?

ከላይ ያለው ሥዕል ለክርስቲያኖች መልካም ምሳሌዎች የሆኑ አንዳንዶችንና የማስጠንቀቂያ ምሳሌዎች የሆኑ ሌሎች ወጣቶችን በሚያጠቃልሉ ታሪኮች ላይ እንድናተኩር ይረዳናል። መሐል ላይ ያለው ከፍ ያለ ኮረብታ የጥንቷ ሴሎ የነበረችበት ቦታ እንደሆነ ግልጽ ነው።a

እስራኤላውያን ተስፋይቱ ምድር ሲገቡ የአምላክን መገናኛ ድንኳን ለመጀመሪያ ጊዜ የተከሉት በኢያሪኮ አጠገብ በጌልጌላ እንደነበር ሳታስታውሱ አትቀሩም። (ኢያሱ 4:19) ይሁን እንጂ ምድሪቱ ስትከፋፈል የእስራኤላውያን አምልኮ ማዕከል የሆነው ቅዱሱ ድንኳን ወደዚህ ወደ ሴሎ ተዛወረ። (ኢያሱ 18:1) ይህም በተራራማው በኤፍሬም አገር ከኢየሩሳሌም በስተ ሰሜን 30 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የሚገኝ ነበር። ከመላው እስራኤል ወደ ሴሎ የሚመጡ ወንዶችና ሴቶች በጣም ብዙ ሕዝብ በመሆን የመገናኛው ድንኳን ተተክሎበት ሊሆን ከሚችልበት ቦታ በስተ ደቡብ ባለው ሸለቆ ውስጥ ይሰበሰቡ ነበር። (ኢያሱ 22:12) ልጆች ወደዚህ ቦታ ሲመጡ በአእምሮአችሁ ልትሥሏቸው ትችላላችሁን?

አንዳንዶች ይመጡ ነበር። የማይረሳ ታዋቂ ምሳሌ አድርገን የምንወስደው ወጣቱን ሳሙኤልን ነው። ወላጆቹ ሕልቃናና ሐና በምዕራብ በኩል ባሉት ኮረብቶች ላይ በምትገኝ አነስተኛ ከተማ ውስጥ ይኖሩ ነበር። በየዓመቱ ወደዚህ ቦታ ይመጡ ነበር። በዚህ ጊዜ ምናልባት የሕልቃና ሌላ ሚስት የወለደቻቸውን አንዳንዶቹን ልጆችም ይዘዋቸው ይመጡ ኖረው ይሆናል። በመጨረሻም ይሖዋ ሳሙኤል የተባለ ወንድ ልጅ እንድትወልድ በማድረግ ሐናን ባረካት። ከጊዜ በኋላ ወላጆቹ በሴሎ እየኖረ በመገናኛው ድንኳን ውስጥ ከሊቀ ካህኑ ከኤሊ ጋር ያገለግል ዘንድ ወደዚህ አመጡት።—1 ሳሙኤል 1:1 እስከ 2:11

ልጁ በአምላክ ቤት ውስጥ የሚሠራው የዘወትር ሥራ ነበረው። እንዲሁም በአቅራቢያው ባሉ ኮረብቶች ላይ በእግሩ የመንሸራሸር ብዙ አጋጣሚዎችም አግኝቶ መሆን አለበት። (1 ሳሙኤል 3:1, 15) ገጽ 9 ላይ ባለው ሥዕል ውስጥ እንደሚታየው አንዳንዶቹ እርከን የተበጀላቸውና በወይራ ዛፍ የተሞሉ ነበሩ። ትንሹን የድንጋይ ማማ ተመልከቱት። ብቻቸውን የሆኑ ገበሬዎች ወይም እረኞች እንዲህ ካለው ማማ ላይ ሆነው ለመጠበቅ ይችሉ ነበር። ይሁን እንጂ ወጣቱ ሳሙኤልም ለማየት እዚያ ላይ ሊወጣ እንደሚችል ልትገምቱ ትችላላችሁ። (ከ2 ዜና 20:24 ጋር አወዳድር) አውሬዎች መምጣት አለመምጣታቸውን ለማየት የሚያስችል አመቺ ቦታ ነበር።

ከአሁኑ ይልቅ በዚያን ጊዜ ብዙ ዛፎችና የዱር አራዊት የሚዘዋወሩባቸው ጫካዎችም ጭምር ነበሩ። (ኢያሱ 17:15, 18) ይህንንም ኤልሳዕ ዋነኛ የአምላክ ነቢይ በነበረበት ጊዜ ከተፈጸመው አንድ ሁኔታ ለማየት እንችላለን። ኤልሳዕ ከኢያሪኮ ወደ ቤቴል በመጓዝ ላይ ነበር፤ ስለዚህ ከሴሎ በስተደቡብ 16 ኪሎ ሜትሮች ርቆ በሚገኝ አካባቢ ነበር። የወርቅ ጥጃ አምልኮ ማዕከል ከነበረችው ከቤቴል ሰዎች ምን ዓይነት አቀባበል ያገኝ ይሆን? (1 ነገሥት 12:27-33፤ 2 ነገሥት 10:29) በዚያ ከተማ ያሉት ትልልቆቹ ሰዎች ለይሖዋ ነቢይ ጥላቻ ሳይኖርባቸው አይቀርም። ይህም አመለካከት በልጆቻቸው ላይ የተጋባባቸው ይመስላል።

ሁለተኛ ነገሥት 2:23, 24 አንድ የወጣቶች ቡድን የአምላክን ነቢይ “አንተ መላጣ፣ ውጣ፤ አንተ መላጣ፣ ውጣ” እያሉ እንዳፌዙበት ይነግረናል። ኤልሳዕም በምላሹ “በእግዚአብሔርም [በይሖዋም አዓት] ስም ረገማቸው፤ ከዱርም ሁለት [ሴት አዓት] ድቦች ወጥተው ከብላቴኖች አርባ ሁለቱን ሰባበሩአቸው።” እንዲህ ያሉት የሶሪያ ቡናማ ድቦች በሚደናገጡበት ወይም ግልገሎቻቸው ጥቃት የተቃጣባቸው በመሰላቸው ጊዜ በኃይለኛ ቁጣ ሊቦጫጭቁ ይችላሉ። (2 ሳሙኤል 17:8፤ ምሳሌ 17:12፤ 28:15) አምላክ እነዚህን ድቦች ተወካዮቹን ባዋረዱት፣ በዚህም አድራጎት ይሖዋን በናቁት ላይ መለኮታዊ ፍትሕ ለማስፈጸም ተጠቅሞባቸዋል።

በሴሎ ኮረብቶች አካባቢ አንድ ልጅ እንዲህ ዓይነቱ የዱር አውሬ ሊያጋጥመው መቻሉ የሳሙኤል ወላጆች በመገናኛው ድንኳን እንዲያገለግል እርሱን ወደዚህ በማምጣታቸው የነበራቸውን እምነት ይበልጥ እንድናደንቅ ይረዳናል።

ቀደም ሲልም ሌላው እውነተኛ አምላኪ መስፍኑ ዮፍታሔ ተመሳሳይ የሆነ እምነትና አምላካዊ ፍቅር አሳይቶ ነበር። የሚኖረው ከዮርዳኖስ በስተምሥራቅ በኩል በኮረብታማው አገር በገለዓድ ነበር። ለይሖዋ ቅንዓት ስለነበረው ጠላት የነበሩትን አሞናውያን ለማጥፋት ሲል እሱን ሊገናኘው በመጀመሪያ ከቤቱ የሚወጣውን ሰው ለይሖዋ መሥዋዕት እንደሚያደርግ ተሳለ። በመጀመሪያ የወጣችውም ድንግል ልጁ ሆና ተገኘች። ስለዚህ አንድ ልጁን ለዓመታት በታማኝነት እያገለገለች ወደኖረችበት በሴሎ ወደሚገኘው ወደ አምላክ መቅደስ አመጣት።—መሳፍንት 11:30-40

በእርግጥም ሳሙኤልና የዮፍታሔ ሴት ልጅ በሴሎ አካባቢ ያሳዩት የታማኝነት አምላካዊ ፍቅር በዚሁ ቦታ በይሖዋ ነቢይ ላይ ካላገጡት እነዚያ 42 ዓመፀኛ ወጣቶች ካሳዩት አፍራሽ የሆነ ምሳሌነት ጋር ሲነፃፀር በጣም የተለየ ነው።—ከ1 ቆሮንቶስ 10:6, 11 ጋር አወዳድር።

[የግርጌ ማስታወሻ]

a ሥዕሉን በትልቁ ለማየት የ1992⁠ን የይሖዋ ምስክሮች የቀን መቁጠሪያ ተመልከት።

[በገጽ 8 ላይ የሚገኘው ሥዕል ምንጭ]

Pictorial Archive (Near Eastern History) Est.

[በገጽ 9 ላይ የሚገኘው ሥዕል ምንጭ]

Pictorial Archive (Near Eastern History) Est.

[በገጽ 9 ላይ የሚገኘው ሥዕል ምንጭ]

Safari Zoo, Ramat-Gan, Tel Aviv

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ