የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w92 11/15 ገጽ 3
  • እንደገና የሚወለዱት እነማን ናቸው?

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • እንደገና የሚወለዱት እነማን ናቸው?
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1992
  • ንዑስ ርዕሶች
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ስሜትና አእምሮ
  • ዳግመኛ መወለድ መዳን የሚገኝበት መንገድ ነው?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2009
  • ኒቆዲሞስን በምሽት አስተማረ
    ኢየሱስ—መንገድ፣ እውነት፣ ሕይወት
  • ዳግመኛ መወለድ ሲባል ምን ማለት ነው?
    የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው
  • ኒቆዲሞስን አስተማረ
    እስከ ዛሬ ከኖሩት ሁሉ የሚበልጠው ታላቅ ሰው
ለተጨማሪ መረጃ
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1992
w92 11/15 ገጽ 3

እንደገና የሚወለዱት እነማን ናቸው?

ሁሉም ጥሩ ሰዎች ወደ ሰማይ ይሄዳሉን? ብዙ ሰዎች የሚያስቡት እንደዚህ ነው፤ ኢየሱስ ክርስቶስ ግን በዚህ አልተስማማም ነበር። በሌሊት በምስጢር ወደ እርሱ ለመጣው የአይሁድ አለቃ ለኒቆዲሞስ ኢየሱስ ሲናገር “ወደ ሰማይ የወጣ ማንም የለም” ብሎታል።—ዮሐንስ 3:13

ሆኖም አንዳንድ ሰዎች ወደ ሰማይ ለመሄድ አጋጣሚ የሚያገኙበት ጊዜ እንደሚመጣ ኢየሱስ ለኒቆዲሞስ ጠቅሶለታል። ኢየሱስ ስለ እነዚህ ሰዎች ሲናገር “ሰው ከውኃና ከመንፈስ ካልተወለደ በቀር ወደ እግዚአብሔር መንግሥት ሊገባ አይችልም። ከሥጋ የተወለደ ሥጋ ነው፣ ከመንፈስ የተወለደ መንፈስ ነው። ዳግመኛ ልትወለዱ ያስፈልጋችኋል ስላልሁህ አታድንቅ” ብሏል። ኒቆዲሞስ ግን ሰው እንዴት እንደገና ሊወለድ እንደሚችል ገርሞት ነበር።—ዮሐንስ 3:1-9

ምናልባት አንተም ኢየሱስ ምን ማለቱ እንደሆነ ገርሞህ ይሆናል። የኢየሱስ ቃላት የሚያመለክቱት በአምላክ መንፈስ ቅዱስ እንደተሞሉ የሚያስቡ ብዙ ሰዎች የሚናገሩለትን በድንገት የመለወጥ ተሞክሮን ነውን?

ስሜትና አእምሮ

አንድ ሰው እንደገና መወለዱንና አለመወለዱን የሚወስነው የመንፈስ ኃይል እንዳለው ሲሰማው ነው ብለው አንዳንድ ሰዎች ይናገራሉ። ሆኖም በተለይ ልባችንና አእምሮአችን በኃይለኛ ስሜት ከተገፋፉ ሊያሳስቱን ይችላሉ።—ኤርምያስ 17:9

ስሜት በአእምሮ ላይ ያለውን ተጽእኖ የሚያጠኑ ተመራማሪ የሆኑት ዊልያም ሳርጋንት “በስሜት ተነሳስተን አእምሮአችን ሊከዳን በሚችልበት ጊዜ የሚያድሩብንን እምነቶች ለመቀበል መጠንቀቅ” እንደሚያስፈልግ አመልክተዋል። ሳርጋንት ባሉት መሠረት የሚያነቃቃ ስብከትና የእሳታማ ሲኦል ቅጣት ማስፈራሪያዎች የሚያስከትሉት ውጤት አንዱ ምሳሌ ነው። የቀረው ምርጫ ዘላለማዊ ሥቃይ ብቻ ከሆነ ወደ ሰማይ ለመሄድ ሲል እንደገና መወለድ የማይፈልግ ማን አለ? በእንዲህ ዓይነቱ የስሜት ውጥረት ወቅት በሚኖርበት ሁኔታ “የማሰብ ችሎታ ቦታውን እንደሚለቅና የተለመደው የአንጎል ኮምፒዩተር ለጊዜው ከሥራ ውጭ ስለሚሆን አዳዲስ ሐሳቦችና እምነቶች ያለ ምንም ማመዛዘን ተቀባይነት እንደሚያገኙ” ሳርጋንት ተናግረዋል።—ዘ ማይንድ ፖሰስድ

ታዲያ ጉዳዩ እንዲህ ከሆነ አንድ ሰው እንደገና መወለድን “ያለምንም ማመዛዘን ተቀባይነት ያገኘ እምነት” መሆን አለመሆኑን ሊያውቅ የሚችለው እንዴት ነው? እውነተኛ የጥበብ መንገድ የሚሆነው የአምላክ መንፈስ ቅዱስ የመጽሐፍ ቅዱስ ጸሐፊዎችን እንዲመዘግቡ ባደረጋቸው ነገር ሁሉ መመራት ነው። ክርስቲያኖች አምላክን ‘በማሰብ ኃይላቸው’ እንዲያመልኩት ማበረታቻ ተሰጥቶአቸዋል፣ የሚያምኑት ነገር እውነት መሆኑንም ማረጋገጥ ያስፈልጋቸዋል።—ሮሜ 12:1, 2፤ 1 ተሰሎንቄ 5:21

እንደገና መወለድ ለሰው ልጆች ከተዘረጉላቸው ታላላቅ መብቶች ሁሉ የበለጠውን ታላቅ መብት ይከፍትላቸዋል። በአምላክ ዓላማ አሠራር ውስጥ በእርግጥ አስደናቂ ከሆነ የነገሮች ዕድገት ጋር የተያያዘ ነው። ይህ ሁሉ እውነት ሆኖ ሳለ “እንደገና የሚወለዱት እነማን ናቸው? እንደገና መወለድ የሚከናወነውስ እንዴት ነው? እንደገና በተወለዱት ግለሰቦች ፊት የቀረበላቸው ምን ተስፋ ነው? የሚድኑትስ እነርሱ ብቻ ናቸውን? የሚሉትን የመሰሉ ጥያቄዎች ይነሳሉ።

[በገጽ 3 ላይ የሚገኝ ሥዕል]

ኒቆዲሞስ ሰው እንዴት እንደገና ሊወለድ እንደሚችል ገርሞት ነበር

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ