የ50 ዓመት ዕድሜ ያለውና አሁንም በተሳካ ሁኔታ በመሥራት ላይ የሚገኘው የጊልያድ ትምህርት ቤት
የካቲት 1, 1943 የጊልያድ ትምህርት ቤት ሲከፈት ለመጀመሪያዎቹ ተማሪዎች ኤን ኤች ኖር “ስለ መንግሥቱ በስፋት ምስክርነት ያልተሰጠባቸው ብዙ ሥፍራዎች አሉ” ሲል ገለጸላቸው። ቀጥሎም:- “በመስኩ ላይ ብዙ ሠራተኞች ቢኖሩ ኖሮ በመቶና በሺህ የሚቆጠሩ ሰዎችን መርዳት ይቻል ነበር። በጌታ ፀጋ ወደፊት ብዙ ሠራተኞች ይኖሩናል” አለ።
በመስኩ ላይ ብዙ ሠራተኞች ነበሩ። ወደፊት ደግሞ በሚልዮን የሚቆጠሩ ያስፈልጋሉ። በ1943 የመንግሥቱ አስፋፊዎች ቁጥር በ54 አገሮች ውስጥ 129,070 የነበረው በ1992 በ229 አገሮች ውስጥ ወደ 4,472,787 ከፍ ብሏል። ይህን ጭማሪ ላስገኘው ምስክርነት የጊልያድ ትምህርት ቤት ከፍተኛ አስተዋፅኦ አበርክቷል። 50 ዓመታት ካለፉ በኋላም ሚሲዮናውያንን እያሰለጠነ በዓለም መስክ ላይ ሠራተኛ ወደሚያስፈልግባቸው አካባቢዎች በመላክ ቁልፍ የሆነ ሚና መጫወቱን ቀጥሏል።
በኒው ጀርሲ ውስጥ በጀርሲ ሲቲ የክልል ስብሰባ አዳራሽ መጋቢት 7, 1993 የአሜሪካ ቤቴል ቤተሰቦችና ጥሪ የተደረገላቸውን እንግዶች ጨምሮ በጠቅላላው 4,798 ሆነው ለ94ኛው ክፍል ተማሪዎች የምረቃ ሥነ ሥርዓት ተሰብስበው ነበር። ከዚህም በተጨማሪ ይህ ልዩ የሆነው ምረቃ ጊልያድ ያሳለፋቸውን 50 ዓመታት ወደ ኋላ መለስ ብሎ ለመመልከት አጋጣሚ ይሰጣል። ስለ ፕሮግራሙ በመጠኑ ማወቅ ትፈልጋለህን?
ከመክፈቻው መዝሙር በኋላ የአስተዳደር አካል አባል የሆነው ጆርጅ ዲ ጋንገስ ልብ የሚነካ ጸሎት አደረገ። ቀጥሎም ከሊቀመንበሩ ከካሪይ ደብልዩ ባርበር የመክፈቻ ንግግር በኋላ ተመራቂዎቹና በስብሰባው ላይ የተገኙት ሁሉ በተከታታይ የቀረቡ አጫጭር ንግግሮችን አደመጡ።
“ብቻችሁን አይደላችሁም” የሚል አጠቃላይ መልዕክት በመያዝ ንግግሩን በመጀመሪያ ያቀረበው ሮበርት ደብልዩ ዋለን ነበር። ሞቅ ባለ ድምፅ ወደፊት በሕይወታችሁ ውስጥ አንዳንድ ነገሮች ይገጥሟችሁና አሁን ብቻዬን ነኝ፣ ከቤተሰቦቼና ከጓደኞቼ በጣም ርቄያለሁ የሚል ስሜት ይመጣባችኋል። ታዲያ “ብቻችሁን አይደላችሁም” ሊባል የሚቻለው እንዴት ነው? ሲያብራራም ‘እያንዳንዳችሁ ከይሖዋ አምላክ ጋር የማያቋርጥ የሐሳብ ግኑኝነት ማድረግ ስለምትችሉ ነው።’ ለጸሎት መብታቸው ከፍተኛ ዋጋ እንዲሰጡና በየቀኑም እንዲጠቀሙበት ተመራቂዎቹን አጥብቆ አሳሰባቸው። ከዚያም እንደ ኢየሱስ “ብቻዬን አይደለሁም” ብለው ለመናገር ይችላሉ። (ዮሐንስ 16:32) እነዚህ ቃላት ለተመራቂዎቹ በጣም የሚያበረታቱ ነበሩ!
ቀጥሎም የአስተዳደር አካል የሆነው ሌይማን ኤ ስዊንግል “ተስፋችሁን አጥብቃችሁ ያዙ” በሚለው አጠቃላይ መልዕክት ሥር (በመጋቢት 7 የዕለት ጥቅስ ላይ የተመሠረተ) በሁለቱ ባሕሪያት ማለትም በጽናትና በተስፋ አስፈላጊነት ላይ ንግግር አደረገ። ‘ስድብ፣ ተቃውሞ፣ ጥላቻ፣ እሥር፣ ሞትም እንኳን ሳይቀር ክርስቲያኖች ለምን መጽናት እንደሚያስፈልጋቸው የሚያስገነዝቡ ነገሮች ናቸው’ አለ። ‘ታማኝ የሆኑ የይሖዋ ምስክሮች በሚያስፈልጋቸው ጊዜ ከወትሮው ለየት ያለ ኃይል እንዲሰጣቸው በማንኛውም ጊዜ ይሖዋን መጠየቀ ይችላሉ። ይህ በተለይ ለእናንተ ለተመራቂዎች በጣም የሚያጽናና ነው።’ ስለ ተስፋስ ምን ሊባል ይቻላል? ‘ተስፋ በጣም አስፈላጊ የሆነ ነገር ነው።’ ‘የራስ ቁር ያደረገ ሰው ራሱን ከአደጋ እንደሚከላከልለት ሁሉ የመዳንም ተስፋ አንድን ክርስቲያን በታማኝነቱ እንዲጸና የማሰብ ችሎታውን በመጠበቅ ይከላከልለታል’ በማለት ገለጸ። — 1 ተሰሎንቄ 5:8
ተከታዩ ተናጋሪ ራልፍ ኢ ዋልስ ማራኪ የሆነ አጠቃላይ መልዕክት መርጦ ነበር። “ደህንነት ወደምናገኝበት ሰፊ ሥፍራ እንዴት ልናመልጥ እንችላለን? ይህ “ሰፊ ስፍራ” ምንድን ነው? (መዝሙር 18:19) “የአዕምሮ ሰላምና የልብ መረጋጋት የሚያስገኝ የነፃነት ሁኔታ ነው” በማለት ተናጋሪው ገለጸ። ነፃ መሆን የምንፈልገው ከምንድን ነው? ‘ከራሳችሁ ድክመቶችና ሰይጣን ከሚያባብሳቸው ከእናንተ ውጪ ካሉት ነገሮች ነው’ ሲል ጨምሮ አብራራ። (መዝሙር 118:5) ደህንነት ወደሚገኝበት ወደዚያ ሰፊ ስፍራ ልናመልጥ የምንችለው እንዴት ነው? ‘በምናደርጋቸው ነገሮች ሁሉ የይሖዋን ሥርዓቶች በመፈለግና ይሰማናል ብለን በማመን የሚያስጭንቀንን ሁሉ በምልጃ ለይሖዋ በማቅረብ ነው።’
“ወደ ፊት ምን ይጠብቀናል?” የሚለው አጠቃላይ መልዕክት የተመረጠው ደግሞ በዶን ኤ ኣዳምስ ነበር። አዲሶቹ ሚስዮናውያን ከፊታቸው ምን ይጠብቃቸዋል? ከሁኔታዎች ጋር ራሳቸውን የሚያለማምዱበት ጊዜ ይጠብቃቸዋል በማለት ገለጸ። “በተጨማሪም ከፊታችሁ ብዙ በረከቶች ይጠብቋችኋል።” ሁለት አዲስ ሚሲዮናውያን ወደ ምድብ ቦታቸው ከሄዱ በኋላ የጻፉትን ምሳሌ በማድረግ ተናገረ። “በአገልግሎት ካሳለፋችኋቸው ቀኖች ሁሉ ይበልጥ አስደሳች የሆነውን ቀን አስቡ። ሚሲዮናዊ ከሆናችሁ በኋላ እያንዳንዱ ቀን እንደዚያ አስደሳች ቀን ነው። ጽሑፎቻችን በእጆቻችን ብዙም አይቆዩም። ሰዎች እንድናስጠናቸው ያለማቋረጥ ይጠይቁናል።” ተናጋሪው ለተመራቂዎቹ ቤተሰቦችና ጓደኞች እንዲህ ሲል አንዳንድ ሐሳቦች አስተላለፈ:- ‘ለተመራቂዎቹ የምትጭነቁበት ምክንያት የለም። የማበረታቻ ደብዳቤ በመጻፍ ልትረዷቸው ትችላላችሁ።’ — ምሳሌ 25:25
ቀጥሎም የትምህርት ቤቱ አስተማሪዎች ንግግር አደረጉ። ጃክ ዲ ሬድፎርድ የመረጠው አጠቃላይ መልዕክት “ከማንም ሰው ምንም ነገር አትጠብቁ” የሚል ነበር። ተመራቂዎቹ ከሚያጋጥሟቸው ፈታኝ ሁኔታዎች አንዱ ከሰዎች ጋር ተግባብቶ መኖር ነው በማለት ገለጸ። ምን ሊረዳችሁ ይችላል? “ስህተቶቻቸውን እለፉላቸው። ከሌሎቹ ሰዎች ብዙ ነገር አትጠብቁ።” ይገባኛል የምትሉት ሁሉ ይሟላልኛል ብላችሁ ሁልጊዜ አትጠብቁ። ለሌሎች ሰዎች አለፍጽምና ቦታ ስጡት። እንዲህ ዓይነቱ ደግነት ከሰዎች ጋር ተግባብታችሁ እንድትኖሩ ይረዳችኋል። ከሌሎች ሰዎች ጋር ተግባብታችሁ መኖራችሁ የብስለታችሁ መለኪያ ነው።” (ምሳሌ 17:9) ተመራቂዎቹ ይህንን የጥበብ ምክር በሥራ ላይ ማዋላቸው በውጭ አገር ሚሲዮናዊ ሆነው በሚያገለግሉበት ጊዜ በእርግጥ በተሳካ መንገድ አካባቢያቸውን እንዲለምዱ ይረዳቸዋል።
“ይህ መዝገብ በሸክላ ዕቃ ውስጥ አለን” በማለት 2 ቆሮንቶስ 4:7 ይናገራል። የጊልያድ ትምህርት ቤት ሬጂስትራር የሆነው ዩሊሰስ ቪ ግላስ “ታማኝነታቸውን ባረጋገጡ ወንድሞቻችሁ ላይ ትምክህት ይኑራችሁ” የሚል አጠቃላይ መልእክት ባለው ንግግር በጥቅሱ ላይ ሃሳብ ሰጠ። ‘የሸክላ ዕቃዎቹ’ ምንድን ናቸው? “ፍጹማን ያልሆነውን እኛን የሚያመለክቱ መሆን አለባቸው” ሲል አሳሰበ። “መዝገቡስ” ምንድን ነው? “ክርስቲያናዊ አገልግሎታችን ነው” በማለት ገለጸ። (2 ቆሮንቶስ 4:1) በዚህ መዝገብ ወይም ውድ ኃብት ምን ሊደረግበት ይገባል? “ይሖዋ በአደራ የሰጠን ይህ ውድ ኃብት ተሰውሮ የሚቀመጥ አይደለም። ስለዚህ እናንተ ውድ እጩ ሚሲዮናውያን ይህንን ውድ ኃብት በምትሄዱበት ስፍራ ሁሉ ለሌሎች በማካፈል እነሱም ለሌሎች ብዙ ሰዎች እንዴት ሊያካፍሉ እንደሚችሉ አስተምሯቸው።”
የጊልያድ ትምህርት ቤት ሥራውን ሲጀምር የመጀመሪያው ሬጂስትራር ሆኖ ያገለገለው አልበርት ዲ ሽሮደር መድረኩ ላይ በወጣ ጊዜ የጥንቱ ትዝታ የተቀሰቀሰበት ሰዓት ነበር። የንግግሩ አጠቃላይ መልዕክት “የግማሽ መቶ ዘመን የቲኦክራቲካዊ ስልጠና” የሚል ነበር። “ይሖዋ ውጤታማ ስልጠናን እንዴት መስጠት እንዳለበት ያውቃል፤ ይህንንም ፈጽሞታል” በማለት ገለጸ። ይህንን የፈጸመው እንዴት ነው? ወንድም ሽሮደር ከ50 ዓመት በፊት በተቋቋሙት ሁለት ትምህርት ቤቶች ማለትም በቲኦክራቲካዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤትና በጊልያድ ትምህርት ቤት አማካኝነት የተሰጠውን ስልጠና ጠቅሶ ተናገረ። የአዲሲቱ ዓለም ትርጉም ትክክለኛ እውቀትን በመስጠት ረገድ ጠቃሚ መሣሪያ ሆኖ መቆየቱን አመልክቷል። “ማኀበሩ የይሖዋን ዓላማ ትክክለኛ እውቀት ለእናንተ መስጠቱን እንደሚቀጥል በመተማመን ወደ ተመደባችሁባቸው አገሮች ልትሄዱ ትችላላችሁ” ሲል አረጋገጠላቸው።
የፔንሲልቫንያው የመጽሐፍ ቅዱስ፣ የመጠበቂያ ግንብና የትራክት ማኀበር ፕሬዘዳንት ሚልተን ጂ ሔንሼል “ከአሸናፊዎች የሚበልጡ” በሚል አጠቃላይ መልዕክት ንግግር አቀረበ። ወንድም ሔንሼል አጠቃላይ መልዕክቱን የወሰደው “በዚህ ሁሉ ግን በወደደን በእርሱ ከአሸናፊዎች እንበልጣለን” ከሚለው ከ1943 የዓመት ጥቅስ ነው። (ሮሜ 8:37) በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወቅት በብዙ አገሮች ውስጥ ያሉ ወንድሞቻችን ስደት ላይ ስለነበሩ ይህ የዓመት ጥቅስ ለወቅቱ የሚስማማ ነበረ በማለት ገለጸ። ወንድም ሔንሼል የዓመቱ ጥቅስ ከተብራራበት መጠበቂያ ግንብ በመጥቀስ እንዲህ ሲል ገለጸ:- “ይህ መጠበቂያ ግንብ [የጥር 15, 1943] በየካቲት ወር በመጀመሪያዎቹ የጊልያድ ተማሪዎች ተጠንቶ ነበር። ከፊታቸው ይጠብቃቸው ለነበረው ነገር አዘጋጅቷቸዋል።” አብዛኛዎቹ ተመራቂዎች ባለፉት 50 ዓመታት አሸናፊዎች እንደሆኑ አስመስክረዋል በማለት ገለጸ። ስለ94ኛው ክፍል ተማሪዎች ምን ሊባል ይቻላል? “ወደ ይሖዋ ተጠግታችሁ ኑሩ፣ ከፍቅሩ አትራቁ፣ እንደዚህ ካደረጋችሁ አሸናፊነታችሁ ይረጋገጣል።”
ጠዋት ከቀረቡት ንግግሮች በኋላ ሊቀመንበሩ ከልዩ ልዩ አገሮች የተላኩትን አንዳንድ ሰላምታዎች አነበበላቸው። ከዚያም 24ቱ ባልና ሚስት በጉጉት ሲጠባበቁት የነበረው ዲፕሎማ የሚሰጥበት ሰዓት ደረሰ። የጊልያድ ተማሪዎች የነበሩት አሁን በይፋ የጊልያድ ምሩቃን ሆነዋል! የመጡት ከ5 አገሮች ሲሆን ምድብ ሥራቸው ግን ሆንግ ኮንግ፣ ታይዋን ሞዛምቢክና ምሥራቅ አውሮፓን ጨምሮ ወደ 17 አገሮች ይወስዳቸዋል።
ከእረፍቱ ቀጥሎ የከሰዓት በኋላው ፕሮግራም በሮበርት ኤል በትለር መጠበቂያ ግንብን በአጭሩ በማብራራት ተጀመረ። ከዚያም ተመራቂዎቹ በኒው ዮርክ ዎልኪል አካባቢ ሲሰብኩ ያጋጠሟቸውን አስደናቂ ተሞክሮዎች ተናገሩ። ፕሮግራሙ ወደ ጊልያድ እንዲመጡ ካደረጋቸው ነገሮቸ አንዱን ማለትም ለመስክ አገልግሎቱ ያላቸውን ጥልቅ ፍቅር አንጸባርቋል።
ከተማሪዎቹ ፕሮግራም ቀጥሎ ከተሰብሳቢዎቹ መካከል ብዙዎቹ 50ኛውን ዓመት የጊልያድ ትምህርት ቤት መታሰቢያ በማድረግ አንድ ልዩ ዝግጅት ይኖር ይሆን በማለት በጉጉት ይጠባበቁ ነበር። ልዩ የሆነው ፕሮግራም ተዘጋጅቶ ስለነበር ተደስተዋል። “የጊልያድ ትምህርት ቤት ያሳለፋቸውን 50 ዓመታት ወደ ኋላ ዞር ብሎ መመልከት” የሚለውን ሳጥን ተመልከት።
ከ50 ዓመታት በፊት ወንድም ኖር እምነት ያለውና የወደፊቱን ጊዜ አርቆ መመልከት የሚችል ሰው መሆኑን አሳይቷል። የጊልያድ ትምህርት ቤት የተሳካ ውጤት ላይ እንደሚደርስ የነበረው እርግጠኛነት ለመጀመሪያዎቹ ተማሪዎች የመግቢያ ንግግር ባደረገ ጊዜ እንደሚከተለው በማለት በጠቀሳቸው ነጥቦች ታይቷል:- “እንደ ስሙ ‘የምስክሮች ክምር’ በመሆን ከዚህ ቦታ ተነስቶ ለሁሉም የዓለም ክፍሎች የሚዳረሰው ይህ ምስክርነት ፍጹም ለማይጠፋው ለአምላካችን ክብር እንደ መታሰቢያ ሐውልት ሆኖ ይቆማል ብለን እናምናለን። እናንተም የተሾማችሁ እንደመሆናችሁ መጠን ሙሉ እምነታችሁን በልዑሉ ላይ በማድረግ በአስፈላጊው ጊዜ ሁሉ እንደሚመራችሁና እንደሚደግፋችሁ ታውቃላችሁ። የበረከት አምላክ መሆኑንም ትገነዘባላችሁ።a
የ94ኛው ክፍል ተመራቂዎች ከእነሱ በፊት የነበሩትን ከ6,500 በላይ የሚሆኑትን ተመራቂዎች አርዓያ የመከተል መብት አግኝተዋል። ለይሖዋ አምላክ ክብር የሚሆን ‘የምስክር ክምር’ እንዲቆለል በማድረግ የበኩላቸውን ድርሻ በማበርከት ትምክህታቸውን በልዑሉ ላይ ያድርጉ።
[የግርጌ ማስታወሻ]
a በዕብራይስጥ ቋንቋ ጊልያድ ማለት ‘የምስክር ክምር’ ማለት ነው። (ዘፍጥረት 31:47, 48)
[በገጽ 1 ላይ የሚገኝ ሣጥን25]
የክፍሉ ስታትስቲክስ
የተማሪዎቹ ጠቅላላ ቁጥር:- 48
የተወከሉት አገሮች ቁጥር:- 5
የተመደቡባቸው አገሮች ቁጥር:- 17
አማካይ ዕድሜ:- 32
በእውነት ውስጥ የቆዩባቸው አማካይ ዓመታት:- 15.3
በሙሉ ጊዜ አገልግሎት የቆዩባቸው አማካይ ዓመታት:- 9.6
[በገጽ 26, 27 ላይ የሚገኝ ሣጥን]
የጊልያድ ትምህርት ቤት ያሳለፋቸውን 50 ዓመታት ወደ ኋላ ዞር ብሎ መመልከት
ጊልያድ ያሳለፈውን ታሪክ ወደ ኋላ ዞር ብሎ ለመመልከት እንዲቻል በውስጡ የኖሩት ማለትም ከቀደምት ምሩቃኑ፣ ከአስተማሪዎቹና፣ ትምህርት ቤቱ እንዲደራጅ የረዱት ካሳለፉት ተሞክሮ ሌላ ምን ጥሩ መንገድ ይኖራል? “የጊልያድ ትምህርት ቤት ያሳለፋቸውን 50 ዓመታት ወደ ኋላ ዞር ብሎ መመልከት” የሚለው ክፍል በቲዮዶር ጃራዝ ሲቀርብ ተሰብሳቢዎቹ በጣም ተደስተው ነበር።
ትምህርት ቤቱ እንዲቋቋም የረዱት ሁኔታዎች ምን ነበሩ? ወንድም ሽሮደር እንደገለጸው እሱና ሌሎች ሁለት አስተማሪዎች ትምህርት ቤቱን እንዲያደራጁ 4 ወር ብቻ ተሰጣቸው። “እኛ ግን ሰኞ የካቲት 1, 1943 ትምህርት ቤቱን ለማስመረቅ ዝግጁዎች ነበርን” በማለት ገለጸ።
ከትምህርት ቤቱ ተመርቀው ከወጡት ለመጀመሪያዎቹ ሚሲዮናውያንስ ሁኔታው እንዴት ነበር? ወንድም ሔንሼል ይህን በማስታወስ ሲናገር “በማኀበሩ የዕቃ መላኪያ ክፍል በነበሩት ሳጥኖች ሊወስዱ የፈለጉትን ዕቃ ሁሉ እንዲታሸግላቸው አደረግን። የታሸጉት ሳጥኖች ሲደርሷቸው በጥንቃቄ በመክፈት ንብረታቸውን ወሰዱ። ከዚያም ሳጥኖቹን የቤት ቁሳቁስ ለመሥራት ተጠቀሙባቸው።” ከጊዜ በኋላ ግን ማኀበሩ የተሟላ ዕቃ ያለው የሚሲዮናውያን መኖሪያ ቤት እንዳዘጋጀ ጠቀሰ።
ቀጥሎ በፕሮግራሙ ላይ አሁን በአሜሪካ የቤቴል ቤተሰብ አባል የሆኑት ቀደምት የጊልያድ ትምህርት ቤት ተመራቂዎች ከነበሩት መካከል አንዳንዶቹ ትውስታቸውን፣ ስሜቶቻቸውንና ተሞክሮዎቻቸውን ተናገሩ። የሰጧቸው ሐሳቦች የተሰበሰቡትን ሁሉ ልባቸውን በጣም ነክቷቸዋል።
“የጊልያድን ትምህርት ቤት የመጀመሪያውን ክፍል እንድካፈል ግብዣው ከደረሰኝ በኋላ እናቴ ካንሰር እንደያዛት አወቅሁ። ይሁን እንጂ ከ16 ዓመቷ ጀምራ በአቅኚነት ስላገለገለች ግብዣውን እንድቀበል አጥብቃ መከረችኝ። በዚህም ምክንያት ደስታና ሐዘን በተቀላቀለበት ስሜት በይሖዋ ላይ እምነት በመጣል ወደ ደቡብ ላንሲንግ ተጓዝኩ። በጊልያድ ትምህርት ቤት በተሰጠን ሥልጠና በጣም ተደሰትኩ፤ ከልቤም አደነቅኩት። እናቴ እኔ ከተመረቅሁ ከጥቂት ጊዜ በኋላ ምድራዊ ሕይወቷን ጨረሰች።” — ሻርሎት ሽሮደር በሜክሲኮና በኤል ሳልቫዶር ያገለገለች
“እኖርበት በነበረው አገር ይሖዋ ይንከባከበኝ ስለነበር የትም ብሄድ ምድር የእሱ ስለሆነች እንደሚንከባከበኝ አውቅ ነበር። በዚህ ምክንያት የመጀመሪያውን ክፍል ግብዣ በደስታ ተቀበልኩ።” — ጁሊያ ዋይልድማን በሜክሲኮና በኤል ሳልቫዶር ያገለገለች
“በጣም አስደሳች ነበር! በያንዳንዱ በር ላይ ሰዎችን ማነጋገር እንችል ነበር። በመጀመሪያው ወር ላይ 107 መጽሐፎች አበርክቼ 19 የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች መራሁ። በሁለተኛው ወር ላይ 28 የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች ነበሩኝ። እርግጥ ነው፣ ሙቀት፣ ርጥበት አዘል አየርና ትኋንን መላመድ ነበረብን። ይሁን እንጂ እዚያ መገኘቴ አስደሳች መብት ነበር። ሁልጊዜ እያስታወስኩት የምደሰትበት ነገር ነው።” — ሜሪ አዳምስ የሁለተኛው ክፍል ምሩቅ በኩባ ተመድባ ትሠራበት የነበረውን ሥራ በተመለከተ
በአላስካ ውስጥ መወጣት የነበረብን ትልቁ እንቅፋት የአየሩ ሁኔታ ነበር። በሰሜን በኩል እጅግ በጣም ከመቀዝቀዙ የተነሣ የቅዝቃዜው መጠን ከዜሮ በታች 60 ዲግሪ ፋራናይት እና ከዚያም በታች ይደርስ ነበር። የሕንድ መንደሮችና በደቡብ ምሥራቅ አላስካ ርቀው የሚገኙ ቦታዎች በጀልባ ወይም በአይሮፕላን በመሄድ እንሰብክላቸው ነበር።” — ጆን ኤርቺቲ የ3ኛው ክፍል ምሩቅ
“ለእኔ ጊልያድ ይሖዋ በምድራዊ ድርጅቱ በኩል በመንፈሳዊ እንድንጎለብትና አስደናቂውን የሕይወት ጎዳና እንድንቀምስ ጥሪ ያደረገበት መንገድ ነው።” — ማይልድረድ ባር የ11ኛው ክፍል በአየርላንድ ያገለገለች ምሩቅ
ቀጥሎም አስደሳች የሆኑ ቃለ ምልልሶች ተደረገላቸው። — ከሉቺሊ ሔንሼል (በቬንዚዌላ ያገለገለች የ14ኛው ክፍል ምሩቅ) ከማርጋሬት ክላይን (የ20ኛው ክፍል ምሩቅ በቦሊቪያ ያገለገለች) ከሉቺሊ ኮልትራፕ (በፔሩ ያገለገለች የ24ኛው ክፍል ምሩቅ) ከሎራይን ዋለን (በብራዚል ያገለገለ የ27ኛው ክፍል ምሩቅ) ዊልያምና ሳንድራ ማልንፋት (የ34ኛው ክፍል ምሩቅ በሞሮኮ ያገለገሉ) ከጌርት ሎሽ (የ41ኛው ክፍል በኦስትሪያ ያገለገለ ምሩቅ) እና ዴቪድ ስፒሌን (የ42ኛው ክፍል በሴኔጋል ያገለገለ ምሩቅ)
አስተማሪዎች ሆነው በትምህርት ቤቱ ያገለገሉትስ ምን ይላሉ? ቁጥራቸው በርካታ ለሆኑት ቃለ ምልልስ ተደረለጎላቸዋል። እነሱም:- ራስል ኩርዛን፣ ካርል አደምስ፣ ሃሮልድ ጃክሰን፣ ፍሬድ ራስክ፣ ሃሪ ፔሎያን፣ ጃክ ሬድፎርድና ዩሊሰስ ግላስ ናቸው። ያገኙት መብት እስካሁን ድረስ ሕይወታቸውን እንዴት እንደነካው ገለጹ።
በጊልያድ የሰለጠኑ ሚሲዮናውያን ውጤታማ መሆናቸውን የሚያሳየው አስደናቂ ማስረጃ በጃፓን ውስጥ ባገለገለው በሎይድ ባሬ ቀረበ። 15 ሚሲዮናውያን በ1949 ሲላኩ በጃፓን ውስጥ በአጠቃላይ 10 የማይሞሉ አስፋፊዎች ብቻ ነበሩ። ይሁን እንጂ ከ44 ዓመታት በኋላ ከ175,000 በላይ የመንግሥቱ አዋጅ ነጋሪዎች በዚሁ አገር ይገኛሉ። ቀጥሎም ሮበርት ዋለን በፓናማ ለ45 ዓመታት ያህል ስታገለግል የቆየችና ወደ 125 የሚያክሉ ሰዎች ራሳቸውን ለአምላክ እንዲወስኑና እንዲጠመቁ የረዳች የአንዲት ሚሲዮናዊ እህት ተሞክሮን ጨምሮ አንዳንድ ሚሲዮናውያን ሌሎችን ሰዎች ወደ እውነት በማምጣት ረገድ ያገኙትን የተሳካ ውጤት ተናገረ።
በተሰብሳቢዎች መካከል የነበሩት የጊልያድ ምሩቃን የሆኑ ሁሉ ወደ መድረኩ እንዲመጡ ሲጋበዙ አጠቃላይ የፕሮግራሙ መደምደሚያ ሰዓት ደረሰ። በእውነትም ልብን የሚነካ ወቅት ነበር። ጥሪ የተደረገላቸው ምሩቃን እንዲሁም በቤቴል ቤተሰብ ውስጥ ያሉ 89 የሚያክሉ ወንድሞችና እህቶችን ጨምሮ መድረኩንና ወደ መድረኩ የሚወስደውን መተላለፊያ መንገድ ሞልተውት ቆሙ። ቀጥሎም ለብዙ ዓመታት ሲያገለግሉ የነበሩ የትምህርት ቤቱ አስተማሪዎችና የ94ኛው ክፍል ተመራቂዎች ጋር በመሆን በአጠቃላይ በመድረኩ ላይ የተገኙት ወደ 160 የሚጠጉ ነበሩ።
“የጊልያድ ትምህርት ቤት ሚሲዮናውያንን አሰልጥኖ ወደ ውጭ አገር በመላክ ተሳክቶለታልን?” በማለት ወንድም ጃራዝ ጠየቀ። “አዎ፣ ባለፉት 50 ዓመታት የተገኙት ማስረጃዎች አዎን የሚል የሚያስተጋባ መልስ ይሰጣሉ!
[በገጽ 25 ላይ የሚገኝ ሥዕል]
የመጠበቂያ ግንብ የመጽሐፍ ቅዱስ የጊልያድ ትምህርት ቤት ተመራቂዎች የ94ኛው ክፍል
ከዚህ በታች ባለው ዝርዝር ተርታዎች ቁጥር የተሰጣቸው ከፊት ወደ ኋላ ሲሆን የስም ዝርዝሮቹ ደግሞ በእያንዳንዱ ተርታ ከግራ ወደ ቀኝ በዝርዝር ተጽፈዋል።
(1) ዲላ ጋርዛ ሲ፤ ቦርግ ኢ አሪጋ፤ ሹህ ኢ፤ ፐርቨስ ዲ፤ ፎስቤሪ ኤ፤ ዲልጋዶ ኤ፤ ድሬሽር ኤል፤ (2) ስኮት ቪ፤ ፍሪድሉንድ ኤል፤ ኬቱላ ኤስ፤ ኮፕላንድ ዲ፤ አሪጋ ጄ፤ ቲዲ ጄ፤ ኦልሶን ኢ፤ ዋይድግረን፤ (3) ዲልጋዶ ኤፍ፤ ኪጋን ኤስ፤ ሊዮነን ኤ፤ ፊኒጋን ኢ፤ ፎስቤሪ ኤፍ፤ ሆልብሩክ ጄ፤ ቤርጉላንድ ኤ፤ ጆነስ ፒ፤ (4) ዋልሰን ቢ፤ ፈራየስ ሲ፤ ሹህ ቢ፤ ሆልብሩክ ጄ፤ ፐርቨስ ጄ፤ ፊኒጋን ኤስ፤ ጆነስ ኤ፤ ኪቺያ ኤም፤ (5) ስኮት ጂ፤ ኮፕላንድ ዲ፤ ድሬሸር ቢ፤ ዲ ላ ጋርዛ አር፤ ሊዮነን አይ፤ ኪጋን ዲ፤ ዋትሰን ቲ፤ ኬቱላ ኤም፤ (6) ዋይድግረን ጄ፤ ቦርግ ኤስ፤ ኩቺያ ኤል፤ ቤርጉላንድ ኤ፤ ኦልሰን ቢ፤ ፍራያስ ጄ፤ ፍሪድሉንድ ቲ፤ ታይድ ፒ።