የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w95 9/15 ገጽ 30
  • የአንባብያን ጥያቄዎች

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የአንባብያን ጥያቄዎች
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1995
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ለማስተማር ሥራችሁ የማያቋርጥ ጥንቃቄ አድርጉ
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1999
  • ከኢየሱስ ታናሽ ወንድም ተማሩ
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2022
  • የአምላክን ቃል ለማስተማር በሚገባ የታጠቁ
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2002
  • እረኞች፣ ከሁሉ የላቁትን እረኞች አርዓያ ተከተሉ
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2013
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1995
w95 9/15 ገጽ 30

የአንባብያን ጥያቄዎች

ደቀ መዝሙሩ ያዕቆብ “ወንድሞቼ ሆይ፣ ከእናንተ ብዙዎቹ አስተማሪዎች አይሁኑ፣ የባሰውን ፍርድ እንድንቀበል ታውቃላችሁና” ብሎ ሲናገር ምን ማለቱ ነበር?—ያዕቆብ 3:1

ያዕቆብ ክርስቲያኖች እውነትን ለሌሎቸ ከማስተማር እንዲቆጠቡ መናገሩ እንዳልነበር እሙን ነው። በማቴዎስ 28:19, 20 ላይ ኢየሱስ ደቀ መዛሙርቱን “ያዘዝኋችሁንም ሁሉ እንዲጠብቁ እያስተማራችኋቸው ደቀ መዛሙርት አድርጓቸው” በማለት አዝዟቸዋል። ስለዚህ ሁሉም ክርስቲያኖች አስተማሪ መሆን ይኖርባቸዋል። ሐዋርያው ጳውሎስ የዕብራውያን ክርስቲያኖች አስተማሪ የመሆን ደረጃ ላይ ገና ባለመድረሳቸው ወቅሷቸዋል። “ከጊዜው የተነሣ አስተማሪዎች ልትሆኑ ሲገባችሁ፣ አንድ ሰው ስለ እግዚአብሔር ቃላት መጀመሪያ ያለውን የሕፃንነትን ትምህርት እንዲያስተምራችሁ እንደ ገና ያስፈልጋችኋልና” በማለት ጽፏል።—ዕብራውያን 5:12

ታዲያ ያዕቆብ እየተናገረ ያለው ምንን በተመለከተ ነው? በጉባኤ ውስጥ ልዩ የማስተማር መብት ስላገኙ ሰዎች አስመልክቶ እየተናገረ ነበር። በኤፌሶን 4:11 ላይ እንዲህ እናነባለን፦ “እርሱም [የጉባኤ ራስ የሆነው ኢየሱስ ክርስቶስ] አንዳንዶቹ ሐዋርያት፣ ሌሎቹም ነቢያት፣ ሌሎቹም ወንጌልን ሰባኪዎች፣ ሌሎቹም እረኞችና አስተማሪዎች እንዲሆኑ ሰጠ።” በአሁኑ ጊዜ እንዳለው ሁሉ በመጀመሪያው መቶ ዘመን ክርስቲያኖች መካከልም የማስተማር መብት ነበር። ለምሳሌ “ታማኝና ልባም ባሪያ”ን የሚወክለው የአስተዳደር አካል በዓለም ዙሪያ በሚገኙ ጉባኤዎች የሚሰጠውን ትምህርት በበላይነት የመቆጣጠር ልዩ ኃላፊነት አለው። (ማቴዎስ 24:45) ተጓዥ የበላይ ተመልካቾችም ሆኑ የጉባኤ ሽማግሌዎች ልዩ የማስተማር ኃላፊነት ተሸክመዋል።

ታዲያ ያዕቆብ ብቃት ያላቸው ክርስቲያን ወንዶች የአምላክን ከባድ ፍርድ በመፍራት የማስተማርን ቦታ መቀበል እንደሌለባቸው መናገሩ ነበርን? አልነበረም። በ1 ጢሞቴዎስ 3:1 ላይ “ማንም ኤጲስ ቆጶስነትን ቢፈልግ መልካምን ሥራ ይመኛል የሚለው ቃል የታመነ ነው” ተብሎ እንደተገለጸው ሽማግሌዎች የሚያከናውኑት ሥራ ትልቅ መብት ነው። አንድ ሰው የጉባኤ ሽማግሌ ሆኖ እንዲሾም ሊያሟላ የሚገባው አንዱ አስፈላጊ ነገር “ለማስተማር የሚበቃ” መሆን ነው። (1 ጢሞቴዎስ 3:2) ጳውሎስ በመንፈስ መሪነት የጻፋቸውን ቃላት ያዕቆብ መቃወሙ አልነበረም።

ይሁን እንጂ በመጀመሪያው መቶ ዘመን እዘአ የነበሩ አንዳንድ ሰዎች ብቃት ሳይኖራቸውና ሳይሾሙ ራሳቸውን አስተማሪ ያደረጉ ይመስላል። በዚህ ቦታ ላይ መሆን አንድ ዓይነት ዝና የሚያስገኝ ስለመሰላቸውና የግል ክብር ለማግኘት ስለተመኙ ሊሆን ይችላል። (ከማርቆስ 12:38–40 እና ከ1 ጢሞቴዎስ 5:17 ጋር አወዳድር።) ሐዋርያው ዮሐንስ ‘ዋነኛቸው ሊሆን ስለሚወደውና ከዮሐንስ ምንም ነገር በአክብሮት ለመቀበል የማይፈልገውን’ ዲዮጥራጢስን ጠቅሷል። (3 ዮሐንስ 9) አንደኛ ጢሞቴዎስ 1:7 (የ1980 ትርጉም) ‘የተናገሩትንም ሆነ እርግጠኛ ነን የሚሉበትን ሳያስተውሉ የሕግ አስተማሪዎች ለመሆን ስለሚፈልጉ’ አንዳንድ ሰዎች ይናገራል። በያዕቆብ 3:1 ላይ ያሉት ቃላት በጥንትም ሆነ በአሁኑ ጊዜ የተሳሳተ ውስጣዊ ስሜት ይዘው አስተማሪ የመሆን ምኞት ላላቸው ወንዶች ተስማሚ ናቸው። እንደነዚህ ያሉት ሰዎች መንጋውን በጣም ሊጎዱት ስለሚችሉ የባሰ ፍርድ ሊቀበሉ ይገባቸዋል።—ሮሜ 2:17–21፤ 14:12

በተጨማሪም ያዕቆብ 3:1 ብቃት ላላቸውና አስተማሪ ሆነው ለሚያገለግሉ ጥሩ ማስጠንቀቂያ ይሰጣል። ብዙ የተሰጣቸው ስለሆነ ብዙ ይፈለግባቸዋለ። (ሉቃስ 12:48) ኢየሱስ “ሰዎች ስለሚናገሩት ስለ ከንቱ ነገር ሁሉ በፍርድ ቀን መልስ ይሰጡበታል” በማለት ተናግሯል። (ማቴዎስ 12:36) በተለይም ይህ የሚናገሩት ቃላት ከፍተኛ ተሰሚነት በሚኖረው በተሾሙ ሽማግሌዎች ላይ በትክክል ይሠራል።

ሽማግሌዎች የይሖዋን በጎች ስለያዙበት መንገድ መልስ ይሰጣሉ። (ዕብራውያን 13:17) የሚናገሩት ነገር በአኗኗር ላይ ጉልህ ለውጥ ያመጣል። ስለዚህ አንድ ሽማግሌ ፈሪሳውያን ያደርጉ እንደነበረው የራሱን የግምት አስተሳሰብ እንዳያራምድ ወይም በጎቹን እንዳይጎዳ መጠንቀቅ ይኖርበታል። ኢየሱስ ያሳይ የነበረውን ዓይነት የጠለቀ ፍቅር ለማሳየት መጣጣር አለበት። ትምህርት በሚሰጥባቸው በማንኛውም አጋጣሚ ሁሉ በተለይም በፍርድ ጉዳዮች ውስጥ ገብቶ በሚሠራበት ጊዜ አስቀድሞ ሳይዘጋጅ ግምታዊ ሐሳቦችን እንዳይሰነዝር ወይም የራሱን አስተያየት እንዳይሰጥ የሚናገራቸውን ቃላት አስቀድሞ ማጤን ይኖርበታል። ሙሉ በሙሉ በይሖዋ፣ በቃሉና በድርጅቱ አማካኝነት በሚመጡ መመሪያዎች ላይ በመደገፍ እረኛው ‘የባሰውን ፍርድ ከመቀበል’ ይልቅ የአምላክን የተትረፈረፈ በረከት ሊያገኝ ይችላል።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ