የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w97 5/1 ገጽ 6
  • ‘ሐቀኛ ሰዎች ያስፈልጉናል’

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ‘ሐቀኛ ሰዎች ያስፈልጉናል’
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1997
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • በሁሉም ነገር ሐቀኞች ሁኑ
    ከአምላክ ፍቅር ሳትወጡ ኑሩ
  • በሁሉም ነገር ሐቀኛ ሁን
    ለዘላለም በደስታ ኑር!—አሳታፊ የመጽሐፍ ቅዱስ መማሪያ
  • በሁሉም ነገር ሐቀኛ ሁን
    ‘ከአምላክ ፍቅር አትውጡ’
  • ሐቀኛ መሆን ይክሳል
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2006
ለተጨማሪ መረጃ
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1997
w97 5/1 ገጽ 6

‘ሐቀኛ ሰዎች ያስፈልጉናል’

በዛሬው ዓለም ውስጥ ሐቀኝነት እየጠፋ ሄዷል። ይሁን እንጂ ሐቀኝነት ክርስቲያኖች ሊኖራቸው የሚገባ መሠረታዊ ባሕርይ ነው። ጳውሎስ ‘በነገር ሁሉ በሐቀኝነት ልንመላለስ’ እንወዳለን ሲል ጽፏል። (ዕብራውያን 13:​18 NW) ከይሖዋ ምሥክሮች አንዷ የሆነችውን በኢጣሊያ ፋኤንዛ ከተማ የምትኖረው ቬልማም ያደረገችው ይኸንኑ ነበር።

ኢል ሬስቶ ዴል ካርሊኖ የተባለው ጋዜጣ በምትኖርበት ከተማ ውስጥ ከሚገኝ አንድ የገበያ አዳራሽ ውጭ ብዙ ገንዘብ የያዘ የገንዘብ ቦርሳ ባገኘች ጊዜ ለባለንብረቱ ይመለስ ዘንድ “ያለ ምንም ማመንታት” ለፖሊስ ወስዳ እንዳስረከበች ገልጿል።

የከተማው ከንቲባ ይህን ሲሰሙ ወዲያው ለቬልማ አጭር የምስጋና ደብዳቤ ላኩላት። እንዲህ ሲሉ ጽፈዋል:- “ለፈጸምሽው ሰናይ ምግባር በከተማችን ነዋሪዎች ስም ላመሰግንሽ እወዳለሁ። ስመ ጥሯ ከተማችን ፋኤንዛ ጥሩና ሐቀኛ ሰዎችን ትፈልጋለች።”

የምናከናውነው መልካም ድርጊት ለሰዎች የሚታይ ሆነም አልሆነ ሁልጊዜ ሐቀኞች ለመሆን መጣር ይኖርብናል። ቅዱሳን ጽሑፎች እንደሚያሳስቡን “በጌታ ፊት ብቻ ያይደለ ነገር ግን በሰው ፊት ደግሞ መልካም የሆነውን” ለማድረግ እንጥራለን።—2 ቆሮንቶስ 8:21

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ