የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w97 6/1 ገጽ 5-6
  • በጌታ ስም የሚደረግ ምሥጢራዊ እንቅስቃሴ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • በጌታ ስም የሚደረግ ምሥጢራዊ እንቅስቃሴ
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1997
  • ንዑስ ርዕሶች
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ምሥጢራዊ የሆነ ሃይማኖታዊ እንቅስቃሴ የሚያስከትለው አደጋ
  • በምሥጢር መንቀሳቀስ ለምን አስፈለገ?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1997
  • የርዕስ ማውጫ
    ንቁ!—2018
  • ክርስቲያኖች ሊሰውሩት የማይገባ ምሥጢር!
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1997
  • ለሌሎች መናገር የምትችለው ሚስጥር
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2010
ለተጨማሪ መረጃ
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1997
w97 6/1 ገጽ 5-6

በጌታ ስም የሚደረግ ምሥጢራዊ እንቅስቃሴ

አሥራ ሁለት ሰዎችን የገደለውና በብዙ ሺህ በሚቆጠሩ ሰዎች ላይ ደግሞ የጤና መታወክ ያስከተለው መጋቢት 1995 በጃፓን ቶኪዮ በአንድ የምድር ውስጥ የባቡር መተላለፊያ የደረሰው የመርዘኛ ጋዝ ጥቃት አንድ ምሥጢር እንዲጋለጥ አስተዋጽዖ አድርጓል። ኦም ሽንሪኪዮ (የላቀ እውነት) በመባል የሚታወቅ አንድ ሃይማኖታዊ ቡድን ስውር ዓላማውን ለማሳካት የተጠቀመበትን የሳሪን ጋዝ ቀደም ብሎ በድብቅ አከማችቶ ነበር።

ከአንድ ወር በኋላ ደግሞ በዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ በኦክላሆማ ሲቲ ቦምብ ፈንድቶ አንድ የፌደራል ሕንፃ በማፈራረስ 167 ሰዎችን ለሕልፈተ ሕይወት ዳርጓል። ይህ ጥቃት ልክ ከሁለት ዓመት በፊት በመንግሥትና በዋኮ ቴክሳስ በሚገኝ ብራንች ዴቪዲያን በሚባል ሃይማኖታዊ ቡድን መካከል ተፈጥሮ ከነበረው የከረረ አለመግባባት ጋር በተወሰነ ደረጃ ግንኙነት እንዳለው አንዳንድ ማስረጃዎች ይጠቁማሉ። በዚያ ወቅት 80 የሚያክሉ የሃይማኖታዊ ቡድኑ አባላት ሞተዋል። የቦምቡ ፍንዳታ ለአብዛኞቹ ሰዎች ምሥጢር የነበረ አንድ ነገር እንዲገለጥ አድርጓል:- በዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ በደርዘን የሚቆጠሩ የወታደራዊ ሚልሺያ ቡድኖች በመንቀሳቀስ ላይ እንዳሉና ቢያንስ የተወሰኑት ፀረ መንግሥት እርምጃ ለመውሰድ በምሥጢር በማቀድ ላይ እንዳሉ ተጠርጥረዋል።

ከዚያም 1995 ሊገባደድ አካባቢ በፈረንሳይ በግረኖብል አቅራቢያ በሚገኝ አንድ ጫካ ውስጥ የ16 ሰዎች የተቃጠለ አስከሬን ተገኘ። እነዚህ ሰዎች ኦርደር ኦቭ ዘ ሶላር ቴምፕል በመባል የሚታወቅ የአንድ አነስተኛ ሃይማኖታዊ ቡድን አባላት የነበሩ ሲሆን በጥቅምት 1994 የዚህ ሃይማኖታዊ ቡድን አባላት የነበሩ 53 ሰዎች ወይ ራሳቸውን ገድለዋል አሊያም በሌሎች በግፍ ተገድለዋል ተብሎ እንደሚገመት በስዊዘርላንድና በካናዳ ዜና ማሰራጫዎች ተነግሮ ነበር። ይህ አሳዛኝ የሆነ አደጋ ከደረሰ በኋላም ቢሆን ሃይማኖታዊ ቡድኑ የሚያደርገውን እንቅስቃሴ አላቆመም። የዚህ ሃይማኖታዊ ቡድን ፍላጎትና ዓላማ አሁንም ምሥጢር እንደሆነ ነው።

ምሥጢራዊ የሆነ ሃይማኖታዊ እንቅስቃሴ የሚያስከትለው አደጋ

ከእነዚህ ሁሉ ክስተቶች አንፃር ሲታይ ብዙ ሰዎች ሃይማኖታዊ ቡድኖችን በጥርጣሬ ዓይን ቢመለከቱ የሚያስገርም ነውን? ማንም ሰው ቢሆን እንዳሰበው ሆኖ የማያገኘውንና እሱ የማይስማማባቸውን ዓላማዎች የሚያራምድን ሃይማኖታዊም ሆነ ሃይማኖታዊ ያልሆነ በምሥጢር የሚንቀሳቀስ ድርጅት ለመደገፍ እንደማይፈልግ የታወቀ ነው። ሆኖም አጠያያቂ ሁኔታ ባላቸው ምሥጢራዊ ድርጅቶች ወጥመድ ውስጥ ከመግባት ለመራቅ ሰዎች ምን ሊያደርጉ ይችላሉ?

በምሥጢር የሚንቀሳቀስ ድርጅት አባል ለመሆን የሚያስብ ማንኛውም ሰው በቅድሚያ የድርጅቱን ትክክለኛ ዓላማ በሚገባ ቢያረጋግጥ ጥበብ እንደሚሆን ግልጽ ነው። ከጓደኞች ወይም ከምናውቃቸው ሰዎች ግፊት መጠንቀቅ ያስፈልጋል፤ ይህ ውሳኔ በስሜታዊነት ሳይሆን በማስረጃዎች ላይ ተመስርቶ መደረግ ይኖርበታል። ወደፊት ሊያጋጥም የሚችለውን ማንኛውም መጥፎ ሁኔታ የሚቀበለው ራሱ ግለሰቡ እንጂ ሌሎች ሰዎች አለመሆናቸውን አስታውስ።

መጥፎ ዓላማ ካላቸው አደገኛ ቡድኖች ለመራቅ የሚረዳ ከሁሉ የተሻለ አስተማማኝ መንገድ የመጽሐፍ ቅዱስን መሠረታዊ ሥርዓቶች መከተል ነው። (ኢሳይያስ 30:​21) ይህም ከፖለቲካ ገለልተኛ መሆንን፣ ለሌሎች፣ ጠላት ለሆኑ ሰዎችም እንኳ ሳይቀር ፍቅር ማሳየትን፣ ‘ከሥጋ ሥራዎች’ መራቅንና የአምላክ መንፈስ ፍሬዎችን መኮትኮትን ይጨምራል። ከዚህም በላይ ደግሞ ኢየሱስ የዓለም ክፍል እንዳልነበረ ሁሉ እውነተኛ ክርስቲያኖችም የዚህ ዓለም ክፍል መሆን የለባቸውም፤ ይህም በምሥጢር በሚንቀሳቀሱ ዓለማዊ ድርጅቶች ውስጥ ተሳትፎ ከማድረግ መራቅን ይጨምራል።​— ገላትያ 5:​19-23፤ ዮሐንስ 17:​14, 16፤ 18:​36፤ ሮሜ 12:​17-21፤ ያዕቆብ 4:​4

የይሖዋ ምሥክሮች እምነታቸውን በቁም ነገር የሚመለከቱና በግልጽ በሚታይ መንገድ እምነታቸው ከሚጠይቅባቸው ብቃት ጋር ተስማምተው ለመኖር ጥረት የሚያደርጉ እውነተኛ የመጽሐፍ ቅዱስ ተማሪዎች ናቸው። በዓለም ዙሪያ የሚታወቁት ‘ሰላምን የሚፈልግና የሚከተል’ ሃይማኖታዊ ቡድን እንደሆኑ ተደርገው ነው። (1 ጴጥሮስ 3:​11) የይሖዋ ምሥክሮች—የአምላክ መንግሥት አዋጅ ነጋሪዎች የተባለው (የእንግሊዝኛ) መጽሐፋቸው እንዲህ ሲል በትክክል ይገልጻል:- “የይሖዋ ምሥክሮች በምንም ዓይነት በምሥጢር የሚንቀሳቀስ ቡድን አባላት አይደሉም። በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ የተመሠረተው እምነታቸው ማንም ሰው አግኝቶ ሊያነባቸው በሚችሉ ጽሑፎች ላይ በሚገባ ተብራርቷል። በተጨማሪም ሰዎች በስብሰባዎቻቸው ላይ በመገኘት ምን እንደሚካሄድ እንዲያዩና እንዲሰሙ ለመጋበዝ ልዩ ጥረት ያደርጋሉ።”

እውነተኛ ሃይማኖት በምሥጢር እንደማይንቀሳቀስ የታወቀ ነው። እውነተኛውን አምላክ የሚያመልኩ ሰዎች የይሖዋ ምሥክሮች እንደ መሆናቸው መጠን ማንነታቸውን እንዳይሰውሩ ወይም የቆሙለትን ዓላማ በግልጽ እንዲያሳውቁ ታዘዋል። ጥንት የነበሩት የኢየሱስ ደቀ መዛሙርት በትምህርታቸው ኢየሩሳሌምን ሞልተዋት ነበር። እምነታቸውና የሚያከናውኑት ሥራ በይፋ የሚታወቅ ነበር። ዛሬ ያሉ የይሖዋ ምሥክሮች ሁኔታም ተመሳሳይ ነው። ክርስቲያኖች በሚያከናውኑት ድፍረት የሚጠይቅ ይፋ ምሥክርነት የተነሳ አምባገነን የሆኑ ገዢዎች አለአግባብ የአምልኮ ነፃነት በሚከለክሏቸው ጊዜ ‘ከሰው ይልቅ አምላክን እንደ ገዢያቸው አድርገው’ በመታዘዝ ሥራቸውን በጥንቃቄና በድፍረት ማከናወን እንዳለባቸው ግልጽ ነው።​— ሥራ 5:​27-29፤ 8:​1፤ 12:​1-14፤ ማቴዎስ 10:​16, 26, 27

የይሖዋ ምሥክሮች በምሥጢር የሚንቀሳቀስ ሃይማኖታዊ ቡድን ወይም ኑፋቄ አባላት ሳይሆኑ አይቀሩም ብለህ የምታስብ ከሆነ እንዲህ ብለህ ልታስብ የቻልከው ስለ እነሱ በሚገባ ስለማታውቅ ሊሆን ይችላል። በመጀመሪያው መቶ ዘመን የነበሩ የአብዛኞቹ ሰዎች ሁኔታም ከዚህ ጋር ተመሳሳይ መሆን አለበት።

ሥራ ምዕራፍ 28 ሐዋርያው ጳውሎስ ‘ከአይሁድ ታላላቆች’ ጋር በሮም ስላደረገው ስብሰባ ይነግረናል። እነሱም “ይህን አንተ የምትከተለውን የሃይማኖት ክፍል በየቦታው ሰዎች እንደሚቃወሙት እናውቃለን፤ ስለዚህ የአንተ አሳብ ምን እንደሆነ መስማት እንፈልጋለን” አሉት። (ሥራ 28:​16-22 የ1980 ትርጉም ) ጳውሎስም ‘ስለ እግዚአብሔር መንግሥት በሚገባ እየመሰከረ አብራራላቸው’፤ “እኩሌቶቹም የተናገረውን አመኑ።” (ሥራ 28:​23, 24) በእርግጥም ስለ እውነተኛው ክርስትና ሐቁን ማወቃቸው ዘላቂ ጥቅም ያስገኝላቸው ነበር።

የይሖዋ ምሥክሮች በግልጽና በይፋ ለሚከናወነው የአምላክ አገልግሎት ያደሩ ስለሆኑ ማወቅ ለሚፈልግ ማንኛውም ሰው ሥራቸውንና እምነታቸውን በተመለከተ ቁልጭ ያለውን ሐቅ ለማስረዳት ፈቃደኞች ናቸው። ስለ እምነታቸው ትክክለኛውን ነገር ለማወቅ ለምን አንተ ራስህ ቀረብ ብለህ አትመረምርም?

[በገጽ 6 ላይ የሚገኝ ሥዕል]

የይሖዋ ምሥክሮች ስለ ማንነታቸውና ስለሚሠሩት ሥራ ለሌሎች ለማስረዳት ፈቃደኞች ናቸው

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ