የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w97 6/1 ገጽ 28
  • የአንባብያን ጥያቄዎች

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የአንባብያን ጥያቄዎች
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1997
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ነቅቶ መጠበቅ የሚያስፈልግበት ጊዜ
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1995
  • ‘ከክፉ ትውልድ’ መዳን
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1995
  • የክርስቶስ መገኘት ለአንተ ምን ትርጉም አለው?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2008
  • የአንባብያን ጥያቄዎች
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1995
ለተጨማሪ መረጃ
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1997
w97 6/1 ገጽ 28

የአንባብያን ጥያቄዎች

ማቴዎስ 24:​34 ላይ እንደምናነበው በኅዳር 1, 1995 የወጣው “መጠበቂያ ግንብ” ኢየሱስ “ይህ ትውልድ” በማለት በተናገረው ላይ ትኩረት አድርጎ ነበር። ታዲያ ይህ ትምህርት የአምላክ መንግሥት በ1914 በሰማይ መቋቋሙን በተመለከተ ጥርጣሬ እንዳለ የሚያመለክት ነውን?

በዚህ መጠበቂያ ግንብ ላይ የቀረበው ማብራሪያ ስለ 1914 ባለን መሠረታዊ ትምህርት ላይ ያስከተለው ምንም ዓይነት ለውጥ የለም። ኢየሱስ በመንግሥታዊ ሥልጣኑ መገኘቱን የሚያሳዩ ምልክቶችን ዘርዝሯል። እነዚህ ምልክቶች ከ1914 ጀምሮ በመፈጸም ላይ መሆናቸውን የሚያሳይ በቂ ማስረጃ አለን። እንደ ጦርነት፣ ረሃብ፣ ቸነፈር፣ የምድር መናወጥና እነዚህን የመሰሉ ሌሎች ማስረጃዎች ኢየሱስ ከ1914 ጀምሮ የአምላክ መንግሥት ንጉሥ ሆኖ መሥራት እንደጀመረ ያረጋግጣሉ። ይህም ከዚያ ጊዜ ጀምሮ በነገሮች ሥርዓት መደምደሚያ ውስጥ እንደምንገኝ ያሳያል።

ታዲያ መጠበቂያ ግንብ ያብራራው ነገር ምንድን ነው? ሊብራራ የተፈለገው ዋና ነገር ኢየሱስ በማቴዎስ 24:​34 ላይ “ትውልድ” ለሚለው ቃል የሰጠው ትርጉም ነው። ይህ ጥቅስ “እውነት እላችኋለሁ፣ ይህ ሁሉ እስኪሆን ድረስ ይህ ትውልድ አያልፍም” ይላል። ኢየሱስ “ትውልድ” ሲል የጠቀሰው ቃል በእርሱ ዘመንም ሆነ በእኛ ዘመን ምን ትርጉም አለው?

ኢየሱስ “ትውልድ” የሚለውን ቃል እንደ አይሁድ መሪዎች ወይም እንደ ራሱ ታማኝ ደቀ መዛሙርት ያለውን አንድን አነስተኛና ውስን የሰዎች ቡድን ለማመልከት እንዳልተጠቀመ የሚያረጋግጡ በርካታ ጥቅሶች አሉ። ከዚህ ይልቅ “ትውልድ” የሚለውን ቃል የተጠቀመው እርሱን ያልተቀበሉትን ብዙሐን አይሁዶች ለማውገዝ ነው። ይሁን እንጂ ግለሰቦች ሐዋርያው ጴጥሮስ በጰንጠቆስጤ ቀን በሰጠው ጥብቅ ማሳሰቢያ መሠረት ንስሐ ሊገቡና ‘ከዚያ ጠማማ ትውልድ’ ሊድኑ የቻሉ መሆናቸው ያስደስታል።​— ሥራ 2:​40

ጴጥሮስ ይህን ሲናገር በአንድ በተወሰነ ዕድሜ ላይ የሚገኙ ሰዎችን ወይም የተለየ ርዝመት ያለውን ጊዜ ማመልከቱ ወይም ‘ትውልዱን’ ከአንድ የተወሰነ ጊዜ ጋር ማያያዙ እንዳልነበረ ግልጽ ነው። ሰዎች ኢየሱስ በተወለደበት ዓመት ወይም በ29 እዘአ ከተወለደ ትውልድ መዳን እንደሚኖርባቸው አልተናገረም። ጴጥሮስ የተናገረው የኢየሱስን ትምህርት ለማዳመጥ አጋጣሚ ስላገኙትና ተአምራቱን አይተው ወይም ስለ ተአምራቱ ሰምተው መሲሕነቱን ስላልተቀበሉ በዚያ ዘመን ይኖሩ ስለነበሩ ያላመኑ አይሁዳውያን ነው። እነዚህ አይሁዳውያን አንዳንዶቹ ወጣቶች ሌሎቹ ደግሞ አረጋውያን ሊሆኑ ይችላሉ።

ኢየሱስ ከራሱ ከጴጥሮስና ከሌሎች ሦስት ሐዋርያት ጋር በደብረ ዘይት ተራራ ላይ በነበረበት ጊዜ የተናገረውን “ትውልድ” የሚል ቃል ጴጥሮስ የተረዳው በዚህ ስሜት እንደሆነ ግልጽ ነው። የዚያ ዘመን አይሁዶች፣ ማለትም በአብዛኛው በኢየሱስ ዘመን የነበሩት አይሁዶች ስለ ጦርነት፣ ስለ ምድር መናወጥ፣ ስለ ረሐብና የአይሁድ ሥርዓት ፍጻሜ መቅረቡን ስለሚያረጋግጡ ሌሎች ምልክቶች ይሰማሉ ወይም ያያሉ። እንዲያውም በ70 እዘአ መጨረሻው ከመምጣቱ በፊት ያ ትውልድ አላለፈም።​— ማቴዎስ 24:​3-14, 34

ይሁን እንጂ ሁላችንም የኢየሱስን ቃል በዚህ ዓይነት ትር​ጉሙ ሳንረዳ እንደቆየን የማንክደው ሐቅ ነው። ፍጹም ያል​ሆኑ ሰዎች መጨረሻው የሚመጣበትን ቀን ለይቶ ለማ​ወቅ የመፈለግ ዝንባሌ አላቸው። ሐዋርያት እንኳን “ጌታ ሆይ፣ በዚህ ወራት ለእስራኤል መንግሥትን ትመልሳለህን?” ብለው በመጠየቅ ቁርጥ ያለ ቀን ለማወቅ እንደፈለጉ ታስታውሳላችሁ።​— ሥራ 1:​6፤ ጋደል አድርገን የጻፍነው እኛ ነን።

በዘመናችንም የአምላክ ሕዝቦች በተመሳሳይ በቅን ልቦና ተነሳስተው ከ1914 ጀምሮ በማስላት መጨረሻው የሚሆንበትን ጊዜ ኢየሱስ ስለ “ትውልድ” ከተናገረው ቃል ለማግኘት ሞክረዋል። ለምሳሌ የአንድ ትውልድ ዕድሜ 70 ወይም 80 ዓመት ሊሆን ይችላል፤ ሰዎቹም አንደኛው የዓለም ጦርነትንና የሌሎች ክንውኖችን ሙሉ ትርጉም ለመረዳት በሚችሉበት ዕድሜ ላይ መገኘት ከነበረባቸው መጨረሻው ምን ያህል እንደቀረበ ማስላት ይቻላል ተብሎ ነበር።

ይሁን እንጂ ይህ ዓይነቱ አስተሳሰብ ምንም ያህል በቀና መንፈስ ላይ የተመሠረተ ቢሆንም እንኳ ኢየሱስ በመቀጠል ከሰጠው ምክር ጋር ይስማማልን? ኢየሱስ እንዲህ ብሏል:- “ስለዚያች ቀንና ስለዚያች ሰዓት ግን ከአባት ብቻ በቀር የሰማይ መላእክትም ቢሆኑ ልጅም ቢሆን የሚያውቅ የለም። . . . ጌታችሁ በምን ሰዓት እንዲመጣ አታውቁምና እንግዲህ ንቁ።”​— ማቴዎስ 24:​36-42

ስለዚህ “ይህ ትውልድ” ለሚለው ሐረግ በቅርቡ በመጠበቂያ ግንብ የተሰጠው ማብራሪያ በ1914 ስለተፈጸመው ነገር በነበረን ግንዛቤ ላይ ያመጣው ለውጥ የለም። ነገር ግን ኢየሱስ “ትውልድ” የሚለውን ቃል እንዴት እንደተጠቀመበት ይበልጥ በግልጽ ለመረዳት ችለናል። የኢየሱስ አጠቃቀም ምን ያህል ወደ መጨረሻው እንደቀረብን ከ1914 ተነስተን ለማስላት እንደማያስችለን ተረድተናል።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ