የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w98 9/1 ገጽ 22-23
  • ቤቴል በጥሩም በመጥፎም የምትታወቅ ከተማ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ቤቴል በጥሩም በመጥፎም የምትታወቅ ከተማ
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1998
  • ንዑስ ርዕሶች
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ቤቴል የክህደት ማዕከል ሆነች
  • ከሁሉ የተሻለ የሥራ መስክ ይሆንልህ ይሆን?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2001
  • “የአምላክን ቤት” በአድናቆት መመልከት
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1994
  • ራስህን በፈቃደኝነት ልታቀርብ ትችላለህ?
    የመንግሥት አገልግሎታችን—2001
  • ይምጡና ይጎብኙ!
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2010
ለተጨማሪ መረጃ
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1998
w98 9/1 ገጽ 22-23

ቤቴል በጥሩም በመጥፎም የምትታወቅ ከተማ

አንዳንድ ከተሞች በውስጣቸው በተፈጸመ ድርጊት በጥሩ ስም ሲነሱ ሌሎች ደግሞ በመጥፎ ስም ይታወሳሉ። ቤቴል ግን ከሌሎች ለየት ባለ መንገድ በጥሩም በመጥፎም ትታወቃለች። ከተማዋን ቤቴል ብሎ የሰየማት የዕብራውያን አባት የሆነው ያዕቆብ ሲሆን ትርጉሙም “የአምላክ ቤት” ማለት ነው። ሆኖም ከአንድ ሺህ ዓመት በኋላ ነቢዩ ሆሴዕ ይህችን ከተማ “የጉዳት ቤት” በማለት ጠርቷታል። የዚህች ከተማ ጥሩ ስም በመጥፎ የተተካው እንዴት ነው? ከተማዋ ካስመዘገበችው ታሪክስ ምን ልንማር እንችላለን?

ቤቴል ከአምላክ ሕዝቦች ጋር በተያያዘ መንገድ መጠቀስ የጀመረችው በ1943 ከዘአበ አብርሃም ገና በሕይወት ከነበረበት ጊዜ አንስቶ ነው። በዚያን ጊዜ ከተማዋ ሎዛ ተብላ ትጠራ የነበረ ሲሆን ይህንንም መጠሪያ ያወጡላት ከነዓናውያን ናቸው። ከተማዋ ከኢየሩሳሌም በስተ ሰሜን በኩል 17 ኪሎ ሜትር ራቅ ብላ ኮረብታማ በሆነ አገር ላይ የተቆረቆረች ነበረች። አብርሃምና የወንድሙ ልጅ ሎጥ በቤቴል አካባቢ ባሉ ተራሮች ላይ ሆነው በዮርዳኖስ ሸለቆ የሚገኘውን ለም መሬት ቁልቁል ሲመለከቱ በዓይነ ሕሊናህ ተመልከት። አብርሃም በጣም ለተበራከቱት መንጎቻቸው የሚበቃ የግጦሽ መስክ እንደሌለ ለሎጥ በዘዴ ነገረው። “እኛ ወንድማማች ነንና በእኔና በአንተ በእረኞቼና በእረኞችህ መካከል ጠብ እንዳይሆን እለምንሃለሁ። ምድር ሁሉ በፊትህ አይደለችምን? ከእኔ ትለይ ዘንድ እለምንሃለሁ፤ አንተ ግራውን ብትወስድ እኔ ወደ ቀኝ እሄዳለሁ፤ አንተም ቀኙን ብትወስድ እኔ ወደ ግራ እሄዳለሁ።”​—⁠ዘፍጥረት 13:​3-11

አብርሃም መጀመሪያ ለመምረጥ የነበረውን መብት ለማስጠበቅ አልሞከረም። ከዚህ ይልቅ ከእርሱ በዕድሜ የሚያንሰው ሰው የተሻለውን ቦታ እንዲመርጥ ፈቀደለት። አብርሃም ያሳየውን ጥሩ ዝንባሌ እኛም ልንኮርጀው እንችላለን። በራሳችን ተነሳሽነት ረጋ ባለ መንፈስ በመናገርና ከራስ ወዳድነት ነፃ የሆነ ነገር በማድረግ አለመግባባቶች እንዳይባባሱ ማድረግ እንችላለን።​—⁠ሮሜ 12:​18

ከብዙ ዓመታት በኋላ የአብርሃም የልጅ ልጅ ያዕቆብ በሎዛ ሰፍሮ በነበረበት ጊዜ አንድ እንግዳ የሆነ ሕልም ተመለከተ። “መሰላል በምድር ላይ ተተክሎ፣ ራሱም ወደ ሰማይ ደርሶ፣ እነሆም የእግዚአብሔር መላእክት ይወጡበት ይወርዱበት ነበር። እነሆም፣ እግዚአብሔር በላይ ቆሞበት” ተመለከተ። (ዘፍጥረት 28:​11-19፤ ከዮሐንስ 1:​51 ጋር አወዳድር።) ሕልሙ አንድ አስፈላጊ የሆነ ቁም ነገር የሚያስተላልፍ ነበር። ያዕቆብ የተመለከታቸው መላእክት የእርሱን ዘር አስመልክቶ አምላክ የገባውን ቃል ለመፈጸም ያገለግሉታል። ይሖዋ ከመሰላሉ በላይ ከፍ ያለ ቦታ ላይ መሆኑ በዚህ ሥራ ለመላእክቱ አመራር እንደሚሰጣቸው የሚያሳይ ነው።

ይህ የመለኮታዊ ድጋፍ ማረጋገጫ ያዕቆብን በጥልቅ ነካው። ከሕልሙ ሲነቃ ያንን ቦታ ቤቴል ብሎ ጠራው፤ ትርጉሙም “የአምላክ ቤት” ማለት ነው። “ከሰጠኸኝም ሁሉ ለአንተ ከአሥር እጅ አንዱን እሰጥሃለሁ” በማለት ለይሖዋ ተሳለ።a (ዘፍጥረት 28:​20-22) ሁሉንም ነገር ያገኘው ከይሖዋ መሆኑን በመገንዘብ አመስጋኝነቱን ለመግለጽ ሲል በለጋስነት መንፈስ መልሶ ለመስጠት ፈለገ።

መላእክት በዛሬው ጊዜ ያሉ ክርስቲያኖችንም ያገለግላሉ። (መዝሙር 91:​11፤ ዕብራውያን 1:​14) ክርስቲያኖችም ‘ለእግዚአብሔር ብዙ ምስጋና በማቅረብ’ ላገኟቸው በረከቶች ያላቸውን አድናቆት መግለጽ ይችላሉ።​—⁠2 ቆሮንቶስ 9:​11, 12 የ1980 ትርጉም

ከጊዜ በኋላ የያዕቆብ ዝርያዎች አንድ ብሔር ሆኑ። መሪያቸው የነበረው ኢያሱ ከነዓናውያንን ድል ከማድረጉ ከጥቂት ጊዜ በፊት የቤቴልን አረማዊ ንጉሥ ድል አደረገ። (ኢያሱ 12:​16) በመሳፍንት ዘመንም ነቢይቷ ዲቦራ በቤቴል አቅራቢያ ተቀምጣ የይሖዋን ቃል ለሕዝቡ ትናገር ነበር። ሳሙኤልም ለእስራኤል ሕዝብ ፈራጅ ሆኖ ይሠራ በነበረበት ጊዜ አዘውትሮ ወደ ቤቴል ይሄድ ነበር።​—⁠መሳፍንት 4:​4, 5፤ 1 ሳሙኤል 7:​15, 16

ቤቴል የክህደት ማዕከል ሆነች

ይሁን እንጂ የእስራኤል መንግሥት በ997 ከዘአበ ከተከፋፈለ በኋላ ቤቴል ከንጹሕ አምልኮ ጋር የነበራት ግንኙነት ተቋረጠ። ንጉሥ ኢዮርብዓም በቤቴል የጥጃ አምልኮ አቋቋመ። ጥጃው ይሖዋን ይወክላል ተብሎ ይታሰብ ነበር። (1 ነገሥት 12:​25-29) ሆሴዕ ቤቴል እንደምትደመሰስ ትንቢት ሲናገር “ቤትአዌን” ብሎ የጠራት በዚህ ምክንያት ነው፤ ትርጉሙም “የጉዳት ቤት” ማለት ነው።​—⁠ሆሴዕ 10:​5, 8

ምንም እንኳ ቤቴል ከጊዜ በኋላ ተለውጣ መንፈሳዊ ጉዳት የምታስከትል ማዕከል ብትሆንም በዚያን ጊዜም በከተማዋ ውስጥ የደረሱት ክስተቶች ጠቃሚ ትምህርት ያዘሉ ናቸው። (ሮሜ 15:​4) ከነዚህ ትምህርቶች አንዱ በቤቴል ያሉት መሠዊያዎችና ካህናት የሚደርስባቸውን ጥፋት እንዲናገር ከይሁዳ ወደ ቤቴል የተላከውን ስሙ ያልተጠቀሰ ነቢይ የሚመለከት ነው። ይህ ነቢይ ምግብ ሳይበላና ውኃ ሳይጠጣ በስተ ደቡብ ጥቂት ኪሎ ሜትሮች ራቅ ብሎ ወደሚገኘው ወደ ይሁዳ ተመልሶ እንዲሄድ ይሖዋ ነግሮት ነበር። ይህ ነቢይ የእስራኤል ንጉሥ በነበረው በኢዮርብዓም ፊት በድፍረት ትንቢት በመናገር በቤቴል የቆመውን መሠዊያ ረገመ። ይሁን እንጂ ቤቴል በሚኖር በአንድ በዕድሜ በገፋ ነቢይ ቤት ምግብ በመመገብ የአምላክን ትእዛዝ ጣሰ። ለምን? ሽማግሌው ነቢይ መሰሉ የሆነውን ነቢይ በእንግድነት ተቀብሎ እንዲጋብዘው የይሖዋ መልአክ እንዳዘዘው በሃሰት ነገረው። ከይሁዳ የመጣው ነቢይ ታዛዥ አለመሆኑ ሞት አስከተለበት።​—⁠1 ነገሥት 13:​1-25

አንድ የእምነት ባልደረባችን አጠያያቂ የሆነ ነገር እንድንፈጽም ሐሳብ ቢያቀርብልን ምን ማድረግ ይኖርብናል? በቀና መንፈስ የተነገረ ምክርም እንኳን ቢሆን ስህተት ከሆነ አደጋ ላይ ሊጥል እንደሚችል አስታውስ። (ከማቴዎስ 16:​21-23 ጋር አወዳድር።) በጸሎትና ቃሉን በማጥናት አመራር እንዲሰጠን ይሖዋን ከጠየቅን ስሙ ያልተጠቀሰው ነቢይ የፈጸመው ዓይነት አሳዛኝ ስህተት ከመፈጸም እንጠበቃለን።​—⁠ምሳሌ 19:​21፤ 1 ዮሐንስ 4:​1

ከ150 ዓመት አካባቢ በኋላ ነቢዩ አሞጽ በቤቴል ላይ የጥፋት ፍርድ ለማወጅ ወደ ሰሜን ተጉዞ ነበር። አሞጽ ‘ወደ አይሁድ ምድር ሸሽቶ እንዲሄድ’ በትዕቢት የተናገረውን ካህኑን አማዝያን ጨምሮ ያዳምጡት የነበሩትን ተቃዋሚዎቹን አጥብቆ አውግዟቸዋል። እንዲያውም አሞጽ በራሱ በካህኑ ቤተሰቦች ላይ ታላቅ መቅሰፍት እንደሚወርድ በድፍረት ለአማዝያ ተናገረ። (አሞጽ 5:​4-6፤ 7:​10-17) ይሖዋ ትሁት አገልጋዮቹን ደፋር ሊያደርጋቸው እንደሚችል ይህ ምሳሌ ያስታውሰናል።​—⁠1 ቆሮንቶስ 1:​26, 27

ከጊዜ በኋላ ይሁዳን ይገዛ የነበረው ታማኙ ንጉሥ ኢዮስያስ ‘በቤቴል የነበረውን መሠዊያ ሰባበረ፣ የኮረብታውን መስገጃ አመድ አደረገ እንዲሁም የማምለኪያ ዐጸዱን አቃጠለ።’ (2 ነገሥት 23:​15, 16) በዛሬው ጊዜ ያሉት ሽማግሌዎች የአምላክን መመሪያዎች ሙሉ በሙሉ በቅንዓት በመፈጸምና የጉባኤውን ንጽሕና ለመጠበቅ ቀዳሚ በመሆን የዚህን ንጉሥ ምሳሌ ሊኮርጁ ይችላሉ።

በቤቴል ታሪክ የደረሱት እነዚህ ክስተቶች ጻድቅ ወይም ክፉ መሆን፣ ይሖዋን መታዘዝ ወይም አለመታዘዝ ምን ሊያስከትል እንደሚችል ቁልጭ አድርገው ያሳያሉ። ከብዙ ዓመታት ቀደም ብሎ ሙሴ “ዛሬ በፊትህ ሕይወትንና ጥሩነትን፣ ሞትንና ክፋትን አኑሬአለሁ” የሚለውን ምርጫ በእስራኤል ሕዝብ ፊት አስቀምጦ ነበር። (ዘዳግም 30:​15, 16) በቤቴል ታሪክ ላይ ማሰላሰላችን “ከጉዳት ቤት” ጋር ሳይሆን የእውነተኛው አምልኮ ማዕከል ከሆነው “የአምላክ ቤት” ጋር እንድንተባበር ያበረታታናል።

[የግርጌ ማስታወሻ]

a ያዕቆብና አብርሃም ሁለቱም በገዛ ፈቃዳቸው ተነሳስተው አሥራት ሰጥተዋል።

[በገጽ 23 ላይ የሚገኝ ሥዕል]

ኢዮርብዓም የጥጃ አምልኮ ማዕከል አድርጎት በነበረው ቦታ የሚገኘው የቤቴል ፍርስራሽ

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ