የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w01 5/15 ገጽ 27
  • የአንባብያን ጥያቄዎች

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የአንባብያን ጥያቄዎች
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2001
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ታላቁ የይሖዋ መንፈሳዊ ቤተ መቅደስ
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1996
  • በይሖዋ መንፈሳዊ ቤተ መቅደስ ውስጥ አምልኮ የማቅረብ መብትህን ከፍ አድርገህ ተመልከተው
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2023
  • ንጉሥ የሚሆነውን መሲሕ ለይቶ ማወቅ
    “መንግሥትህ ትምጣ”
  • ‘ለአሕዛብ ሁሉ የሚሆን የጸሎት ቤት’
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1996
ለተጨማሪ መረጃ
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2001
w01 5/15 ገጽ 27

የአንባብያን ጥያቄዎች

በዳንኤል 9:​24 ላይ እንደተተነበየው “ቅዱሰ ቅዱሳኑ” የተቀባው መቼ ነበር?

ዳንኤል 9:​24-27 ‘አለቃው መሢሕ’ ማለትም ክርስቶስ የሚገለጥበትን ጊዜ በተመለከተ የተነገረ ትንቢት ነው። በመሆኑም በትንቢት የተነገረው ‘የቅዱሰ ቅዱሳኑ’ መቀባት በኢየሩሳሌም የሚገኘው የቤተ መቅደሱ ክፍል የሆነው ቅድስተ ቅዱሳን መቀባቱን አያመለክትም። ከዚህ ይልቅ ‘ቅዱሰ ቅዱሳን’ የሚለው መግለጫ በታላቁ የይሖዋ መንፈሳዊ ቤተ መቅደስ ውስጥ የሚገኘውን የአምላክን ሰማያዊ ማደሪያ ማለትም በሰማይ ያለውን ቅድስተ ቅዱሳን ያመለክታል።a​—⁠ዕብራውያን 8:​1-5፤ 9:​2-10, 23

የአምላክ መንፈሳዊ ቤተ መቅደስ ሥራ የጀመረው መቼ ነው? ኢየሱስ በ29 እዘአ ራሱን ለጥምቀት ሲያቀርብ የሆነውን ነገር ተመልከት። ከዚያን ጊዜ አንስቶ ኢየሱስ በመዝሙር 40:​6-8 ላይ የሚገኙትን ቃላት ፈጽሟል። ከጊዜ በኋላ ሐዋርያው ጳውሎስ ኢየሱስ እንዲህ ሲል ወደ አምላክ መጸለዩን ጠቅሷል:- “መሥዋዕትንና መባን አልወደድህም ሥጋን ግን አዘጋጀህልኝ።” (ዕብራውያን 10:​5) አምላክ ኢየሩሳሌም በሚገኘው ቤተ መቅደስ የእንስሳት መሥዋዕት መቅረቡን እንዲቀጥል ‘አለመውደዱን’ ኢየሱስ አውቋል። ከዚህ ይልቅ ይሖዋ መሥዋዕት አድርጎ የሚያቀርበው ፍጹም ሰብዓዊ አካል ለኢየሱስ አዘጋጅቷል። ኢየሱስ ልባዊ ምኞቱን ሲገልጽ “እነሆ፣ በመጽሐፍ ጥቅልል ስለ እኔ እንደ ተጻፈ፣ አምላኬ ሆይ፣ ፈቃድህን ላደርግ መጥቼአለሁ” በማለት አክሎ ተናግሯል። (ዕብራውያን 10:​7) ይሖዋ የሰጠውስ ምላሽ ምን ነበር? የማቴዎስ ወንጌል እንዲህ ይላል:- “ኢየሱስም ከተጠመቀ በኋላ ወዲያው ከውኃ ወጣ፤ እነሆም፣ ሰማያት ተከፈቱ የእግዚአብሔርም መንፈስ እንደ ርግብ ሲወርድ በእርሱ ላይም ሲመጣ አየ፤ እነሆም፣ ድምፅ ከሰማያት መጥቶ:- በእርሱ ደስ የሚለኝ የምወደው ልጄ ይህ ነው አለ።”​—⁠ማቴዎስ 3:​16, 17

ይሖዋ አምላክ ለመሥዋዕትነት የቀረበውን የኢየሱስን ሥጋ መቀበሉ ቃል በቃል በኢየሩሳሌም ቤተ መቅደስ ይገኝ ከነበረው መሠዊያ የሚበልጥ መሠዊያ ወደ ሕልውና መምጣቱን ያመለክታል። ይህ የአምላክ “ፈቃድ” መሠዊያ ወይም መሥዋዕት ሆኖ የሚቀርበውን የኢየሱስን ሰብዓዊ ሕይወት ለመቀበል የተደረገ ዝግጅት ነበር። (ዕብራውያን 10:​10) ኢየሱስ በመንፈስ ቅዱስ መቀባቱ አምላክ መላውን የመንፈሳዊ ቤተ መቅደሱን ዝግጅት ወደ ሕልውና ማምጣቱን ያሳያል።b ስለዚህ ኢየሱስ በተጠመቀበት ጊዜ በታላቁ መንፈሳዊ ቤተ መቅደስ ዝግጅት ውስጥ የአምላክ ሰማያዊ መኖሪያ ተቀብቷል ወይም ‘ቅድስተ ቅዱሳን’ ሆኖ ተለይቷል።

[የግርጌ ማስታወሻ]

a ስለ አምላክ መንፈሳዊ ቤተ መቅደስ የተለያዩ ገጽታዎች ማብራሪያ ለማግኘት የሐምሌ 1, 1996 መጠበቂያ ግንብ ገጽ 14-19⁠ን ተመልከት።

b ይህ ጉዳይ የዳንኤልን ትንቢት በትኩረት ተከታተል! በተባለው መጽሐፍ በገጽ 194 አንቀጽ 27 ላይ በተዘዋዋሪ መንገድ ተጠቅሷል።

[በገጽ 17 ላይ የሚገኝ ሥዕል]

ኢየሱስ በተጠመቀበት ጊዜ “ቅድስተ ቅዱሳኑ” ተቀብቷል

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ