የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w01 11/15 ገጽ 2-4
  • የመዳን ተስፋ ይኖር ይሆን?

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የመዳን ተስፋ ይኖር ይሆን?
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2001
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ‘የመዳን ተስፋችሁ’ ብሩህ ሆኖ እንዲቀጥል አድርጉ!
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2000
  • መዳን በእርግጥ ምን ማለት ነው?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1997
  • መዳን ምንድን ነው?
    የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው
  • ራእይ 21:4—“እንባዎችንም ሁሉ ከዓይኖቻቸው ያብሳል”
    የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶችና ማብራሪያቸው
ለተጨማሪ መረጃ
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2001
w01 11/15 ገጽ 2-4

የመዳን ተስፋ ይኖር ይሆን?

ሃያኛው መቶ ዘመን የሰው ልጅ ከኖረባቸው ዘመናት ሁሉ የከፋ ደም መፋሰስ የታየበት ዘመን ተብሎ ሲጠራ ቆይቷል። በተለይ ደግሞ ካለፉት ጥቂት አሥርተ ዓመታት ወዲህ ወንጀል፣ ጦርነት፣ የጎሳ ብጥብጥ፣ አደገኛ ዕፆችን መውሰድ፣ እምነት አጉዳይነት፣ ጭቆናና ዓመፅ በጣም ተስፋፍተው ይገኛሉ። ከዚህም በተጨማሪ በሽታ፣ እርጅናና ሞት የሚያስከትሉትን ሕመምና ሥቃይ አስብ። በዛሬው ጊዜ በዓለም ላይ ተንሰራፍተው ከሚገኙት ትላልቅ ችግሮች መገላገል የማይናፍቅ ማን አለ? የወደፊቱን ጊዜ ስንመለከት የመዳን ተስፋ ይኖር ይሆን?

ከዛሬ 2, 000 ዓመት ገደማ በፊት ሐዋርያው ዮሐንስ እንዲያይ ተደርጎ የነበረውን ራእይ ልብ በል። እንዲህ ሲል ጽፏል:- “እነሆ፣ የእግዚአብሔር ድንኳን በሰዎች መካከል ነው ከእነርሱም ጋር ያድራል፣ እነርሱም ሕዝቡ ይሆናሉ እግዚአብሔርም እርሱ ራሱ ከእነርሱ ጋር ሆኖ አምላካቸው ይሆናል፤ እንባዎችንም ሁሉ ከዓይኖቻቸው ያብሳል፣ ሞትም ከእንግዲህ ወዲህ አይሆንም፣ ኀዘንም ቢሆን ወይም ጩኸት ወይም ሥቃይ ከእንግዲህ ወዲህ አይሆንም፣ የቀደመው ሥርዓት አልፎአልና።” (ራእይ 21:​3, 4) ነቢዩ ኢሳይያስም በተመሳሳይ እንዲህ ሲል ተንብዮአል:- “ሞትን ለዘላለም ይውጣል፣ ጌታ እግዚአብሔርም ከፊት ሁሉ እንባን ያብሳል፣ የሕዝቡንም ስድብ ከምድር ሁሉ ላይ ያስወግዳል፤ እግዚአብሔር ተናግሮአልና።”​—⁠ኢሳይያስ 25:​8

አምላክ የገባቸው ተስፋዎች ፍጻሜ ምን ማለት እንደሚሆን አስብ! የሰው ዘር ከጭቆናና ከዓመፅ ብሎም መከራና ስቃይ ከሚያስከትሉ ነገሮች በሙሉ ይላቀቃል ወይም ነጻ ይወጣል። እንዲያውም ሕመም፣ የዕድሜ መግፋትም ሆነ ሞት ከሚያስከትሉት ሥቃይ እንገላገላለን! የአምላክ ቃል የሆነው መጽሐፍ ቅዱስ ፍጹም ሁኔታዎች በሰፈኑበት ምድር ላይ ስለሚገኝ የዘላለም ሕይወት ይናገራል። (ሉቃስ 23:​43፤ ዮሐንስ 17:​3) ይህን ተስፋ ለማግኘት የሚመኙ ሁሉ ሊያገኙት ይችላሉ። ‘የአምላክ ፈቃድ ሰዎች ሁሉ እንዲድኑና እውነቱን ወደ ማወቅ እንዲደርሱ ነው።’​—⁠1 ጢሞቴዎስ 2:3, 4

ይሁን እንጂ አምላክ ከገባቸው ተስፋዎች ጥቅም ማግኘት ከፈለግን በመዳናችን ረገድ ኢየሱስ ክርስቶስ የሚጫወተውን ሚና መገንዘብና በእርሱ ላይ እምነት ማሳደር ይኖርብናል። ኢየሱስ ራሱ እንደሚከተለው በማለት ተናግሯል:- “በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዶአልና።” (ዮሐንስ 3:​16) ሐዋርያው ጴጥሮስ፣ ኢየሱስ ክርስቶስ በዚህ ረገድ የሚጫወተውን ወሳኝ ሚና ጎላ አድርጎ ሲገልጽ “መዳንም በሌላ በማንም የለም፤ እንድንበት ዘንድ የሚገባን ለሰዎች የተሰጠ ስም ከሰማይ በታች ሌላ የለምና” በማለት ተናግሯል። (ሥራ 4:​12) ሐዋርያው ጳውሎስና ጓደኛው ሲላስ ከቅን ልቦና ተነሳስቶ ጥያቄ ላቀረበላቸው ሰው “በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ እመን፣ አንተና ቤተ ሰዎችህም ትድናላችሁ” በማለት መልሰውለታል።​—⁠ሥራ 16:​30, 31

አዎን፣ ኢየሱስ ክርስቶስ “የሕይወት መገኛ” ሲሆን መዳን የሚቻለው በእርሱ በኩል ብቻ ነው። (ሥራ 3:​15 አ.መ.ት) ይሁን እንጂ እኛን በማዳን ረገድ አንድ ሰው ይሄን ያህል ቁልፍ ሚና ሊጫወት የሚችለው እንዴት ነው? ኢየሱስ በዚህ ረገድ የሚጫወተውን ሚና በግልጽ መገንዘባችን የመዳን ተስፋችንን ሊያጠነክርልን ይገባል።

[በገጽ 2 ላይ የሚገኝ የሥዕል ምንጭ]

ገጽ 3:- ቦምብ ጣይ አውሮፕላኖች:- USAF photo; ረሃብ ያጠቃቸው ልጆች:- UNITED NATIONS/J. FRAND; በእሳት የሚጋየው የጦር መርከብ:- U.S. Navy photo 

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ