የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w05 8/15 ገጽ 8
  • በገሊላ ባሕር ላይ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • በገሊላ ባሕር ላይ
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2005
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • የገሊላው ጀልባ​—መጽሐፍ ቅዱስ የተጻፈበትን ዘመን የሚያስታውሰን ቅርስ
    ንቁ!—2006
  • ኢየሱስ ሊጠብቀን ይችላል
    ከታላቁ አስተማሪ ተማር
  • አንዲት መርከብ በአንድ ደሴት አጠገብ ተሰበረች
    የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች መማሪያ መጽሐፌ
  • ኢየሱስ ማዕበሉን ጸጥ አሰኘው
    ኢየሱስ—መንገድ፣ እውነት፣ ሕይወት
ለተጨማሪ መረጃ
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2005
w05 8/15 ገጽ 8

በገሊላ ባሕር ላይ

በማርቆስ 4:35-41 ላይ ተመዝግቦ የምናገኘው ታሪክ ኢየሱስና ደቀ መዛሙርቱ የገሊላን ባሕር ለማቋረጥ በጀልባ መጓዝ እንደጀመሩ ይናገራል። ጥቅሱ እንዲህ ይላል:- “በዚህ ጊዜ ኀይለኛ ዐውሎ ነፋስ ተነሣ፤ ማዕበሉም ውሃ እስኪሞላት ድረስ ጀልባዋን ያናውጣት ነበር። ኢየሱስ ግን ትራስ ተንተርሶ ከጀልባዋ በስተ ኋላ በኩል ተኝቶ ነበር።”

“ትራስ” ተብሎ የተተረጎመውን የግሪክኛ ቃል በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ተጠቅሶ የምናገኘው እዚህ ቦታ ላይ ብቻ ነው። በመሆኑም እዚህ ላይ የገባውን ቃል ትክክለኛ ትርጉም ምሑራን ሊያውቁት አልቻሉም። አብዛኞቹ መጽሐፍ ቅዱሶች ቃሉን “ትራስ” ብለው ተርጉመውታል። ሆኖም ይህ ትራስ ምን ዓይነት ነበር? ማርቆስ መጀመሪያ በጻፈበት ቋንቋ ትራሱን የጀልባው ክፍል እንደሆነ አድርጎ ገልጾታል። በ1986 በገሊላ ባሕር አጠገብ የተገኘ አንድ ጀልባ ማርቆስ የተጠቀመበትን የግሪክኛ ቃል ለመረዳት የሚያስችል ፍንጭ ሰጥቷል።

ይህ 8 ሜትር ርዝመት ያለው ጀልባ የሚጓዘው በተወጠረ ሸራ አማካኝነት በነፋስ እየተገፋ እንዲሁም በመቅዘፊያ በመጠቀም እንደነበረ በተደረገው ጥናት ማወቅ ተችሏል። ይህ ጀልባ ዓሣ ለማጥመድ የሚያገለግል ሲሆን የኋለኛው ክፍል ሰፊና ከባድ የሆነውን መረብ ለማስቀመጫ የሚሆን ቦታ ነበረው። ይህ ጀልባ በ100 ከክርስቶስ ልደት በፊትና በ70 ከክርስቶስ ልደት በኋላ መካከል ባለው ጊዜ ውስጥ ይሠራበት እንደነበረ እንዲሁም ኢየሱስና ደቀ መዛሙርቱ ይጠቀሙበት የነበረው ዓይነት ሊሆን እንደሚችል ይገመታል። ጀልባውን ለማግኘት በተካሄደው የመሬት ቁፋሮ ድርሻ ያበረከቱት ሼሊ ቫክስማን ዘ ሲ ኦቭ ጋሊሊ ቦት—አን ኤክስትራኦርዲናሪ 2000 ይር ኦልድ ዲስከቨሪ የተባለውን መጽሐፍ ጽፈዋል። እኚህ ሰው ኢየሱስ የተንተራሰበት “ትራስ” የጀልባውን ሚዛን ለመጠበቅ የሚያገለግል በአሸዋ የተሞላ ከረጢት ሊሆን እንደሚችል ገልጸዋል። በጃፋ የሚኖርና በመረብ ዓሣ የማጥመድ ልምድ ያለው አንድ ሰው እንዲህ ብሏል:- “ወጣት በነበርኩበት ጊዜ በሜዲትራኒያን አካባቢ ስንሠራ አሸዋ የያዘ አንድ ወይም ሁለት ከረጢት ሁልጊዜ እንይዝ ነበር። . . . ከረጢቶቹን የምንይዘው ጀልባው ሚዛኑን እንዲጠብቅ ለማድረግ ሲሆን እነዚህ ከረጢቶች በማንፈልጋቸው ጊዜ በጀልባው ኋለኛ ክፍል ይቀመጡ ነበር። አንድ ሰው ቢደክመው ከጀልባው ወለል በታች ባለው ቦታ ላይ የአሸዋ ከረጢቱን እንደ ትራስ በመጠቀም ይተኛ ነበር።”

አብዛኞቹ ምሑራን የማርቆስ ዘገባ፣ ኢየሱስ ጀልባው ሚዛኑን እንዲጠብቅ የሚያደርገውን የአሸዋ ከረጢት ተንተርሶ ከጀልባው ወለል በታች ባለው ቦታ ላይ እንደተኛ የሚገልጽ እንደሆነ ይሰማቸዋል፤ ይህ ቦታ ደግሞ በማዕበል ጊዜ ከአደጋ የተጠበቀ ነው። ሆኖም ኢየሱስ የትኛውንም ዓይነት ትራስ ይጠቀም ዋናው ቁም ነገር ከዚያ በኋላ የተከናወነው ክስተት ነው። ኢየሱስ በአምላክ ኃይልና ድጋፍ አማካኝነት በማዕበል የተናወጠውን ባሕር ጸጥ እንዲል አድርጎታል። ደቀ መዛሙርቱም እንኳ “ነፋሱም ሞገዱም የሚታዘዙለት ይህ ማነው?” በማለት ጠይቀዋል።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ