የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w06 3/15 ገጽ 3
  • ሞት አስከፊው እውነታ!

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ሞት አስከፊው እውነታ!
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2006
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ትልቅ ቦታ የማግኘት ምኞት እንዳያድርብህ ተጠንቀቅ!
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2012
  • አቢሴሎም በኩራት ተነሳስቶ ዓመፀ
    ክርስቲያናዊ ሕይወታችንና አገልግሎታችን​—የስብሰባው አስተዋጽኦ—2022
  • በይሖዋ ሙሉ በሙሉ መታመን የደኅንነት ስሜት እንዲያድርብን ያደርጋል
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2011
  • የነፃነት አምላክ የሆነውን ይሖዋን አገልግሉ
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2012
ለተጨማሪ መረጃ
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2006
w06 3/15 ገጽ 3

ሞት አስከፊው እውነታ!

አርኖልድ ቶይንቢ የተባሉ እንግሊዛዊ ታሪክ ጸሐፊ “የሰው ልጅ ከተወለደበት ቅጽበት አንስቶ በማንኛውም ጊዜ ሊሞት ይችላል፤ አንድ ቀን ይህ ሐቅ እውን መሆኑ አይቀርም” በማለት ጽፈዋል። ሞት የምንወደውን የቤተሰባችንን አባል ወይም የቅርብ ወዳጃችንን ሲነጥቀን ከፍተኛ ሐዘን ይደርስብናል!

ለብዙ ሺህ ዓመታት ይህ አስከፊ እውነታ የሰው ልጆችን ሲያሰቅቅ ኖሯል። የምንወደው ሰው ሲሞትብን የከንቱነት ስሜት ይሰማናል። እገሌ ከገሌ ሳይል ሁሉም ሰው የዚህ ዓይነት ሐዘን ያጋጥመዋል። ከሞት ሊያመልጥ የሚችል ሰው የለም። አንድ የ19ኛው መቶ ዘመን ጸሐፊ “ምንም ያህል የትምህርት ደረጃ ቢኖረን [ስለ ሞት ለሚፈጠሩብን ጥያቄዎች] መልስ ስለማይኖረን ሐዘን ሁላችንንም እንደ ልጆች ያደርገናል። አዋቂ የተባለው ሰው እንኳ ምንም አያውቅም” በማለት ጽፈዋል። ልክ እንደ ሕፃናት ሁኔታዎችን ልንቀይር የማንችል አቅመ ቢስ እንሆናለን። ሀብትም ሆነ ሥልጣን ያጣነውን ሰው ሊመልስልን አይችልም። አዋቂዎችም ሆኑ ምሑራን መልስ የላቸውም። ብርቱውም እንደ ደካማው እንባውን ያፈሳል።

የጥንቷ እስራኤል ንጉሥ የነበረው ዳዊት ልጁ አቤሴሎም በሞተበት ጊዜ ይህን የመሰለ መሪር ሐዘን ደርሶበታል። ንጉሡ የአቤሴሎምን ሞት በሰማበት ጊዜ “ልጄ አቤሴሎም ሆይ! ልጄ አቤሴሎም! በአንተ ፈንታ ምነው እኔ በሞትሁ ኖሮ! አቤሴሎም ሆይ፣ ልጄን፣ ወየው ልጄን!” ብሎ አልቅሷል። (2 ሳሙኤል 18:33) ኃያላን የሆኑት ጠላቶቹን በቁጥጥሩ ሥር ያደረገው ብርቱ ንጉሥ እንኳ ምንም ነገር ለማድረግ ስላልቻለ በልጁ ምትክ ‘የመጨረሻ ጠላት ለሆነው ሞት’ ራሱን ለመስጠት ተመኝቷል።—1 ቆሮንቶስ 15:26

ታዲያ ሞት መፍትሔ ይኖረው ይሆን? ካለው የሞቱ ሰዎች ምን ተስፋ አላቸው? የምንወዳቸውን ሰዎች ዳግመኛ እናያቸው ይሆን? የሚቀጥለው ርዕስ ለእነዚህ ጥያቄዎች ቅዱስ ጽሑፋዊ መልስ ይሰጠናል።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ