የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w06 3/15 ገጽ 26
  • አዲስ የተሾሙ የበላይ አካሉ አባላት

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • አዲስ የተሾሙ የበላይ አካሉ አባላት
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2006
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • አዲስ የአስተዳደር አካል አባላት
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2000
  • አዲስ የበላይ አካል አባል
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2013
  • አዲስ የበላይ አካል አባል
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2019
  • ታሪካዊ ስብሰባ
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2011
ለተጨማሪ መረጃ
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2006
w06 3/15 ገጽ 26

አዲስ የተሾሙ የበላይ አካሉ አባላት

ረቡዕ፣ ነሐሴ 24, 2005 የዩናይትድ ስቴትስና የካናዳ ቤቴል ቤተሰቦች በማለዳ አምልኮ ላይ አንድ አስደሳች ማስታወቂያ ሰሙ። ከብሩክሊን ወደ እነዚህ ቅርንጫፍ ቢሮዎች በቪዲዮ በሚተላለፈው በዚህ ፕሮግራም ላይ፣ ጄፈሪ ጃክሰንና አንቶኒ ሞሪስ የተባሉ ሁለት ወንድሞች ከመስከረም 1, 2005 ጀምሮ የይሖዋ ምሥክሮች የበላይ አካል አዲስ አባላት ሆነው እንደተሾሙ ተገለጸ።

ወንድም ጃክሰን የአቅኚነት አገልገሎቱን የጀመረው በየካቲት ወር 1971 ሲሆን የተመደበውም የአውስትራሊያ ግዛት በሆነችው የታስማኒያ ደሴት ነበር። ሰኔ 1974 ጀኔትን (ጄኒ) አገባ፤ ከዚያ ብዙም ሳይቆዩ ልዩ አቅኚዎች ሆነው እንዲያገለግሉ ተሾሙ። ከ1979 እስከ 2003 ባሉት ዓመታት ውስጥ የደቡባዊ ፓሲፊክ ደሴቶች በሆኑት በቱቫሉ፣ በሳሞኣ እና በፊጂ ሚስዮናውያን ሆነው አገልግለዋል። እነዚህ ባልና ሚስት በደሴቶቹ በነበሩበት ወቅት መጽሐፍ ቅዱሳዊ ጽሑፎችን በመተርጎሙ ሥራም የጎላ ድርሻ አበርክተዋል። ወንድም ጃክሰን ከ1992 ጀምሮ በሳሞኣ፣ ከ1996 ጀምሮ ደግሞ በፊጂ የቅርንጫፍ ኮሚቴ አባል ሆኖ አገልግሏል። ሚያዝያ 2003 እርሱና ጄኒ የዩናይትድ ስቴትስ ቤቴል ቤተሰብ አባላት በመሆን በትርጉም አገልግሎት ክፍል መሥራት ጀመሩ። ከዚያ ብዙም ሳይቆይ ወንድም ጃክሰን በይሖዋ ምሥክሮች የበላይ አካል ሥር በሚገኘው የትምህርት ኮሚቴ ውስጥ ረዳት ሆኖ ማገልገል ጀመረ።

ወንድም ሞሪስ አቅኚ ሆኖ ማገልገል የጀመረው በ1971 በዩናይትድ ስቴትስ ነው። በዚያው ዓመት፣ ታኅሣሥ ላይ ሱዛንን ያገባ ሲሆን የመጀመሪያ ልጃቸው ጄሲ እስከተወለደበት ጊዜ ድረስ ለአራት ዓመታት ያህል በአቅኚነት አገልግለዋል። ከጊዜ በኋላ ፖል የተባለ ሁለተኛ ልጅ ወለዱ። ወንድም ሞሪስ በ1979 የዘወትር አቅኚ በመሆን እንደገና ወደ ሙሉ ጊዜ አገልግሎት ተመለሰ። ልጆቻቸው ትምህርት ቤት ሲገቡ ባለቤቱም አቅኚ ሆነች። ቤተሰቧ በዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ ወደ ሮዴ ደሴት እንዲሁም ሰሜን ካሮላይና በመሄድ የምሥራቹ ሰባኪዎች ይበልጥ በሚያስፈልጉበት አካባቢ አገልግሏል። በሰሜን ካሮላይና ወንድም ሞሪስ ተተኪ የወረዳ የበላይ ተመልካች ሆኖ ሲያገለግል ልጆቻቸው ደግሞ የዘወትር አቅኚዎች ሆኑ። ጄሲና ፖል 19 ዓመት ሲሞላቸው በየተራ ወደ ዩናይትድ ስቴትስ ቤቴል ተጠሩ። በዚህ መሃል ወንድም ሞሪስ የወረዳ የበላይ የተመልካች ሆኖ ማገልገል ጀመረ። ከዚያም በ2002 እርሱና ሱዛን በቤቴል እንዲያገለግሉ ተጋበዙ፤ አዲሱን ምድባቸውንም በነሐሴ ወር ጀመሩ። ወንድም ሞሪስ መጀመሪያ በፓተርሰን በአገልግሎት ክፍል ከዚያም በይሖዋ ምሥክሮች የበላይ አካል ሥር የአገልግሎት ኮሚቴው ረዳት ሆኖ አገልግሏል።

ከእነዚህ ሁለት አዲስ አባላት በተጨማሪ የበላይ አካሉ ሳሙኤል ኸርድ፣ ስቲቨን ሌት፣ ቴዎዶር ጃራዝ፣ አልበርት ሽሮደር፣ ኬሪ ባርበር፣ ዳንኤል ሲድሊክ፣ ዴቪድ ስፕሌን፣ ጆን ባር፣ ጋይ ፒርስ እና ጌሪት ሎሽ የተባሉትን ወንድሞች ያቀፈ ነው። ሁሉም የበላይ አካሉ አባላት በመንፈስ የተቀቡ ክርስቲያኖች ናቸው።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ