የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w07 1/1 ገጽ 3-4
  • ስኬትን የምትለካው በምንድን ነው?

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ስኬትን የምትለካው በምንድን ነው?
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2007
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • በሕይወት ውስጥ እውነተኛ ስኬት ማግኘት
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2012
  • ስኬታማ መሆን የምትችለው እንዴት ነው?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2007
  • እውነተኛ ስኬት ማግኘት የሚቻለው እንዴት ነው?
    ንቁ!—2014
  • እውነተኛ ስኬት ምንድን ነው?
    ንቁ!—2014
ለተጨማሪ መረጃ
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2007
w07 1/1 ገጽ 3-4

ስኬትን የምትለካው በምንድን ነው?

በዎል ስትሪት የአክሲዮን ነጋዴ የነበረው ጄሲ ሊቨርሞር በአንዳንዶች ዘንድ ከማንም ይበልጥ የተዋጣለት ሰው እንደሆነ ተደርጎ ይታሰብ ነበር። ጄሲ ከንግድ ጋር በተያያዘ ጥሩ ውሳኔዎችን በማድረጉ ይታወቃል። ይህ ችሎታውም ከፍተኛ ሀብት እንዲያከማች አስችሎታል። በመሆኑም በእጅ የተሠሩ ምርጥና ውድ የሆኑ ሙሉ ልብሶች ይለብስ፣ 29 ክፍሎች ባሉት መኖሪያ ቤት ውስጥ ይኖር ነበር። ከዚህም በላይ ጥቁር ሮልስ ሮይስ መኪና የነበረችው ሲሆን የሚንቀሳቀሰውም በሾፌር ነበር።

ዴቪድምa እንዲሁ የተሳካለት ሰው ለመሆን ቆርጦ ነበር። የአንድ ትልቅ ኩባንያ ምክትል ፕሬዚዳንትና ዋና ሥራ አስኪያጅ ሆኖ ይሠራ የነበረው ይህ ሰው በድርጅቱ ውስጥ አሁን ካለው የበለጠ ከፍተኛ ሥልጣን የማግኘት ተስፋ ነበረው። ሀብትና ክብር ቀልቡን ስቦት ነበር። ይሁን እንጂ ከድርጅቱ ለመልቀቅ ውሳኔ አደረገ። “ከእንግዲህ ወዲህ እንዲህ ዓይነት ከፍተኛ ቦታ እንደማይኖረኝ አውቃለሁ” በማለት ተናግሯል። ዴቪድ የተሳሳተ ውሳኔ ያደረገ ይመስልሃል?

ብዙዎች ስኬትን ከሀብት፣ ከታዋቂነት ወይም ከዝና ጋር ያዛምዱታል። ይሁን እንጂ በቁሳዊ የበለጸጉ ሰዎችም የባዶነት ስሜት ሊሰማቸው ብሎም የሕይወት ትርጉምና ዓላማ ሊጠፋባቸው ይችላል። ሊቨርሞር ያጋጠመው ሁኔታም ይኸው ነበር። ሀብታም ቢሆንም እንኳ ሕይወቱ በመከራና በሐዘን የተሞላ ሰው ነበር። የመንፈስ ጭንቀት የነበረበትና በተደጋጋሚ የትዳር መፍረስ ያጋጠመው ሲሆን ከልጆቹም ጋር ጥሩ ግንኙነት አልነበረውም። በመጨረሻም ሊቨርሞር አብዛኛውን ሀብቱን ካጣ በኋላ አንድ ቀን በአንድ ትልቅ ሆቴል ቡና ቤት ውስጥ ቁጭ ብሎ ስለደረሰበት ኪሳራ በማሰብ ይቆጭ ጀመረ። መጠጥ ካዘዘ በኋላ የቆዳ ሽፋን ያለውን ማስታወሻ ደብተሩን አውጥቶ ለባለቤቱ የስንብት ደብዳቤ ጻፈ። ያዘዘውን መጠጥ ከጨረሰ በኋላ በቂ ብርሃን ወደሌለው አንድ ክፍል ውስጥ ገብቶ በሽጉጥ ራሱን ገደለ።

እርግጥ ራሱን ያጠፋበትን ምክንያት በእርግጠኝነት መናገር ባይቻልም ይህ ታሪክ የሚከተለውን የመጽሐፍ ቅዱስ አባባል እውነተኝነት ያረጋግጣል:- “ባለጠጋ ለመሆን የሚፈልጉ . . . ራሳቸውንም በብዙ ሥቃይ ወግተዋል።”—1 ጢሞቴዎስ 6:9, 10

ስኬትን በሀብት፣ በሥልጣን ወይም በዝና የሚለኩ ሰዎች የተሳሳተ መመዘኛ እየተጠቀሙ ይሆን? አንተስ ስኬታማ እንደሆንክ ይሰማሃል? ለምን? እንዲህ ብለህ የመለስከው በምን መመዘኛ ተጠቅመህ ነው? ለስኬት ያለህ አመለካከት የተቀረጸው በምንድን ነው? የሚቀጥለው ርዕስ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች ስኬታማ እንዲሆኑ ያስቻላቸውን አስተማማኝ ምክር ያብራራል። አንተም ስኬታማ ልትሆን የምትችለው እንዴት እንደሆነ እስቲ እንመልከት።

[የግርጌ ማስታወሻ]

a ስሙ ተቀይሯል።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ