የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w13 11/1 ገጽ 16
  • የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2013
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ወደ ሰማይ እነማን ይሄዳሉ? ለምንስ?
    በምድር ላይ በገነት ለዘላለም መኖር ትችላለህ
  • የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2015
  • ታማኝ ክርስቲያኖች በሙሉ ወደ ሰማይ ይሄዳሉ?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2011
  • ጥሩ ሰዎች ሁሉ ወደ ሰማይ ይሄዳሉ?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2010
ለተጨማሪ መረጃ
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2013
w13 11/1 ገጽ 16
[በገጽ 16 ላይ የሚገኝ ሥዕል]

የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው

ወደ ሰማይ የሚሄዱት እነማን ናቸው? የሚሄዱት ለምንድን ነው?

በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች፣ ሲሞቱ ወደ ሰማይ እንደሚሄዱ ተስፋ ያደርጋሉ። ኢየሱስ፣ ታማኝ ሐዋርያቱ በሰማይ እንደሚኖሩ ተናግሯል። በሰማይ ከአባቱ ጋር እንዲሆኑ ቦታ እንደሚያዘጋጅላቸው ከመሞቱ በፊት ለሐዋርያቱ ቃል ገብቷል።—ዮሐንስ 14:2⁠ን አንብብ።

በምድር ላይ ይኖሩ የነበሩ ሰዎች ከሞት ሲነሱ ወደ ሰማይ የሚሄዱት ለምንድን ነው? እዚያስ ምን ያደርጋሉ? ኢየሱስ፣ በሰማይ ነገሥታት እንደሚሆኑ ለሐዋርያቱ ነግሯቸዋል። ነገሥታት ሆነው ምድርን ያስተዳድራሉ።—ሉቃስ 22:28-30⁠ን እና ራእይ 5:10⁠ን አንብብ።

ጥሩ ሰዎች ሁሉ ወደ ሰማይ ይሄዳሉ?

በብዙ አገሮች በአስተዳደር ሥራ የሚካፈሉት ጥቂት ሰዎች ብቻ ናቸው። ሰዎች ከሞት ተነስተው ወደ ሰማይ የሚሄዱበት ዓላማ ምድርን ለማስተዳደር ስለሆነ እነዚህ ሰዎች ጥቂቶች እንደሚሆኑ ማሰብ እንችላለን። (ሉቃስ 12:32) መጽሐፍ ቅዱስ፣ ከኢየሱስ ጋር የሚገዙት ሰዎች ቁጥራቸው ስንት እንደሚሆን በግልጽ ይናገራል።—ራእይ 14:1⁠ን አንብብ።

ኢየሱስ፣ ለአንዳንድ ተከታዮቹ በሰማይ ቦታ አዘጋጅቶላቸዋል። እነዚህ ሰዎች እዚያ ሄደው ምን እንደሚያደርጉ ታውቃለህ?

ሽልማት የሚያገኙት ግን ወደ ሰማይ የሚሄዱት ብቻ አይደሉም። ኢየሱስ ለሚያስተዳድረው መንግሥት በታማኝነት የሚገዙ ሰዎች፣ ገነት በምትሆነው ምድር ላይ ለዘላለም ይኖራሉ። (ዮሐንስ 3:16) አንዳንዶች ይህ ክፉ ሥርዓት ሲጠፋ በሕይወት ተርፈው ወደዚህች ገነት ይገባሉ። ሌሎች ደግሞ በገነት ውስጥ ትንሣኤ ያገኛሉ።—መዝሙር 37:29⁠ን እና ዮሐንስ 5:28, 29⁠ን አንብብ።

ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት በይሖዋ ምሥክሮች የተዘጋጀውን ትክክለኛው የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ምንድን ነው? የተባለውን መጽሐፍ ምዕራፍ 8 ተመልከት

www.jw.org ከተባለው ድረ ገጽ ላይ ማውረድ ይቻላል

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ