የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • wp16 ቁጥር 4 ገጽ 16
  • መጽሐፍ ቅዱስ ምን ያስተምራል?

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • መጽሐፍ ቅዱስ ምን ያስተምራል?
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (ለሕዝብ የሚሰራጭ)—2016
  • ንዑስ ርዕሶች
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ሃይማኖትን የፈጠሩት ሰዎች ናቸው?
  • የአንድ ሃይማኖት አባል መሆን አስፈላጊ ነው?
  • ሃይማኖት
    ንቁ!—2014
  • የአንድ ሃይማኖት አባል መሆን የግድ አስፈላጊ ነው?
    የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው
  • ለደህንነት በሚያበቃ ንጹሕ ሃይማኖት መመላለስ
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1991
  • እውነተኛውን ሃይማኖት ማግኘት የምችለው እንዴት ነው?
    የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው
ለተጨማሪ መረጃ
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (ለሕዝብ የሚሰራጭ)—2016
wp16 ቁጥር 4 ገጽ 16
የአንድ ቤተሰብ አባላት የተለያዩ የአምልኮ ቦታዎችን ሲመለከቱ

መጽሐፍ ቅዱስ ምን ያስተምራል?

ሃይማኖትን የፈጠሩት ሰዎች ናቸው?

አንዳንዶች ምን ይላሉ? አንዳንድ ሰዎች ሃይማኖትን የፈጠሩት የሰው ልጆች እንደሆኑ ይሰማቸዋል፤ ሌሎች ደግሞ አምላክ፣ ሰዎች ወደ እሱ እንዲቀርቡ ለመርዳት በሃይማኖት እንደሚጠቀም ያምናሉ። አንተ ምን ይመስልሃል?

መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል?

“በአምላካችንና በአባታችን ዓይን ንጹሕና ያልረከሰ ሃይማኖት” አለ። (ያዕቆብ 1:27 የግርጌ ማስታወሻ) የንጹሑ ወይም የእውነተኛው ሃይማኖት ምንጭ አምላክ ነው።

መጽሐፍ ቅዱስ የሚያስተምረው ሌላስ ነገር አለ?

  • አንድ ሃይማኖት አምላክን የሚያስደስት እንዲሆን በመጽሐፍ ቅዱስ እውነት ላይ መመሥረት አለበት።—ዮሐንስ 4:23, 24

  • በሰው አስተሳሰብ ላይ የተመሠረቱ ሃይማኖቶች ከንቱ ናቸው።—ማርቆስ 7:7, 8

የአንድ ሃይማኖት አባል መሆን አስፈላጊ ነው?

ምን ትላለህ?

  • አዎ

  • አይደለም

  • እንደ ሁኔታው

መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል?

“እርስ በርስ ለፍቅርና ለመልካም ሥራዎች መነቃቃት እንድንችል አንዳችን ለሌላው ትኩረት እንስጥ፤ . . . መሰብሰባችንን ቸል አንበል።” (ዕብራውያን 10:24, 25) አምላክ፣ ሕዝቦቹ በተደራጀ መልኩ እንዲሰበሰቡ ይፈልጋል።

መጽሐፍ ቅዱስ የሚያስተምረው ሌላስ ነገር አለ?

  • አምላክን በኅብረት የሚያመልኩ ሰዎች በሚያምኑት ነገር ረገድ አንድነት ሊኖራቸው ይገባል።—1 ቆሮንቶስ 1:10, 11

  • በአምላክ ዘንድ ተቀባይነት ያለው ሃይማኖት አባላት ዓለም አቀፍ የወንድማማች ማኅበር አላቸው።—1 ጴጥሮስ 2:17

ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት በይሖዋ ምሥክሮች የተዘጋጀውን ትክክለኛው የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ምንድን ነው? የሚል ርዕስ ያለውን የዚህን መጽሐፍ ምዕራፍ 15 ተመልከት

መጽሐፉ www.jw.org/am ላይም ይገኛል

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ