የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w17 ጥር ገጽ 32
  • ይህን ያውቁ ኖሯል?

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ይህን ያውቁ ኖሯል?
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2017
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • እሳት የሚሰጠው ጥቅምና የሚያስከትለው ጉዳት
    ንቁ!—2003
  • እሳት! መጠቀም ያለብህ የትኛውን እሳት ማጥፊያ ነው?
    ንቁ!—2001
  • ከሁሉ የላቀው የአምላክ ፍቅር ማረጋገጫ
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2009
  • የአብርሃም እምነት ተፈተነ
    ከመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች ምን ትማራለህ?
ለተጨማሪ መረጃ
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2017
w17 ጥር ገጽ 32
ይስሐቅ እንጨት ተሸክሟል፤ አብርሃም ደግሞ ፍም የያዘ ማሰሮ በእጁ አንጠልጥሏል

ይህን ያውቁ ኖሯል?

በጥንት ጊዜ፣ ሰዎች እሳትን ከቦታ ቦታ የሚያጓጉዙት እንዴት ነበር?

በዘፍጥረት 22:6 ላይ የሚገኘው የመጽሐፍ ቅዱስ ዘገባ፣ አብርሃም መሥዋዕት ለማቅረብ ራቅ ወዳለ ቦታ ስላደረገው ጉዞ ሲናገር እንዲህ ይላል፦ “ለሚቃጠል መባ የሚሆነውን እንጨት ወስዶ ልጁን ይስሐቅን አሸከመው። እሱ ደግሞ እሳቱንና ቢላውን ያዘ፤ ሁለቱም አብረው ሄዱ።”

በጥንት ዘመን ሰዎች እሳት ለማያያዝ ይጠቀሙበት ስለነበረው ዘዴ የሚናገር ዘገባ በቅዱሳን መጻሕፍት ውስጥ አናገኝም። ከላይ ከተጠቀሰው ዘገባ ጋር በተያያዘ አንድ ተንታኝ፣ አብርሃምና ይስሐቅ “ባደረጉት ረጅም ጉዞ ላይ እየነደደ ያለ እሳት ይዘው ተጉዘዋል ብሎ ማሰብ የማይመስል ነገር” እንደሆነ ተናግረዋል። ስለዚህ ይህ ዘገባ እየተናገረ ያለው እሳትን ለማቀጣጠል ስለሚያስፈልጉ ነገሮች ሊሆን ይችላል።

በሌላ በኩል ደግሞ፣ በጥንት ጊዜ እሳት ማያያዝ ቀላል ነገር እንዳልነበረ የሚናገሩም አሉ። በወቅቱ የነበሩት ሰዎች ራሳቸው እሳት ለማቀጣጠል ከመሞከር ይልቅ የሚቻል ከሆነ ከጎረቤቶቻቸው ፍም መውሰድ ይቀላቸዋል። በመሆኑም በርካታ ምሁራን፣ አብርሃም የያዘው ቀደም ባለው ምሽት ካነደዱት እሳት ላይ የወሰደውን የከሰል ፍም የያዘ ዕቃ እንደሆነ ያምናሉ፤ ፍሙን ለመያዝ ደግሞ በሰንሰለት የተንጠለጠለ ማሰሮ ተጠቅሞ ሊሆን ይችላል። (ኢሳ. 30:14) በፍሙ ላይ በቀላሉ የሚቀጣጠል እንጨት በማድረግ በማንኛውም ጊዜ እሳት ማቀጣጠል ይቻላል።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ