መግቢያ
አምላክ ለአንተ ያስብልሃል?
አደጋ ሲከሰት ወይም ሰዎች ሲሠቃዩና ሲሞቱ ስንመለከት ‘አምላክ ይህን ሁኔታ ያያል? ከነጭራሹስ ግድ ይሰጠዋል?’ ብለን እናስብ ይሆናል። መጽሐፍ ቅዱስ እንዲህ ይላል፦
“የይሖዋ ዓይኖች ጻድቃንን ይመለከታሉና፤ ጆሮዎቹም ምልጃቸውን ይሰማሉ፤ የይሖዋ ፊት ግን ክፉ ነገሮችን በሚያደርጉ ላይ ነው።”—1 ጴጥሮስ 3:12
ይህ የመጠበቂያ ግንብ እትም አምላክ እርዳታ የሚያደርግልን እንዴት እንደሆነና ማንኛውንም ዓይነት መከራ ለማስወገድ በቅርቡ ምን እርምጃ እንደሚወስድ ይገልጻል።