የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • wp19 ቁጥር 2 ገጽ 10-11
  • ከከባድ ሕመም ጋር ስትታገል

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ከከባድ ሕመም ጋር ስትታገል
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (ለሕዝብ የሚሰራጭ)—2019
  • ንዑስ ርዕሶች
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • አንዳንዶች ሁኔታውን መቋቋም የቻሉት እንዴት ነው?
  • ሥር የሰደደ በሽታ—መላውን ቤተሰብ የሚነካ ጉዳይ
    ንቁ!—2000
  • ሕመምህን ተቋቁመህ መኖር—እንዴት?
    ንቁ!—2001
  • ቤተሰቦች ሥር የሰደደ በሽታን መቋቋም የሚችሉት እንዴት ነው?
    ንቁ!—2000
  • የቤተሰብ አባል ሲታመም
    ለቤተሰብ ደስታ ቁልፉ ምንድን ነው?
ለተጨማሪ መረጃ
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (ለሕዝብ የሚሰራጭ)—2019
wp19 ቁጥር 2 ገጽ 10-11

ከከባድ ሕመም ጋር ስትታገል

“የሳንባና የአንጀት ካንሰር እንዳለብኝ ሲነገረኝ የሞት ፍርድ የተፈረደብኝ ያህል ሆኖ ተሰምቶኝ ነበር። ከሆስፒታሉ ወደ ቤት ከተመለስኩ በኋላ ግን እንዲህ ብዬ ማሰብ ጀመርኩ፦ ‘እርግጥ ነው፣ ያጋጠመኝ ሁኔታ ፈጽሞ ያልጠበቅኩት ነው፤ ሆኖም ይህን ሁኔታ መቋቋም የምችልበት መላ መፈለግ አለብኝ።’”—ሊንዳ፣ 71 ዓመት

“በግራ በኩል ያሉትን የፊቴን ነርቮች በሚያጠቃ ከባድ ሕመም እሠቃያለሁ። አንዳንዴ ሥቃዩ ኃይለኛ ከመሆኑ የተነሳ በመንፈስ ጭንቀት እዋጣለሁ። ብዙ ጊዜ የብቸኝነት ስሜት የሚሰማኝ ሲሆን ሕይወቴን ለማጥፋት ያሰብኩበት ወቅትም ነበር።”—ኤሊስ፣ 49 ዓመት

በተሽከርካሪ ወንበር የሚንቀሳቀሱ አንድ ታማሚ ሰው በወዳጆቻቸው ተከበው

አንተ ወይም አንድ የቤተሰብህ አባል ለሕይወት አስጊ የሆነ በሽታ እንዳለባችሁ ተነግሮህ የሚያውቅ ከሆነ ሁኔታው ምን ያህል ቅስም እንደሚሰብር መረዳት አይከብድህም። ሕመሙ ከሚያስከትለው ሥቃይ በተጨማሪ ሁኔታው የሚፈጥረውን የስሜት መደቆስ መቋቋም ያስፈልግሃል። ከእያንዳንዱ የሕክምና ቀጠሮ በፊት የሚሰማህ ፍርሃት፣ ሕክምና ማግኘት ወይም ወጪውን መሸፈን አለመቻልህ የሚፈጥረው ውጥረት እንዲሁም ሕክምናው የሚያስከትለው የጎንዮሽ ጉዳት ጭንቀትህን ሊያባብሰው ይችላል። በእርግጥም ከባድ ከሆነ የጤና እክል ጋር ተያይዞ የሚመጣው የስሜት ሥቃይ ከአቅም በላይ ሊሆን ይችላል።

ታዲያ እንዲህ ያለውን አስጨናቂ ሁኔታ መቋቋም የምትችለው እንዴት ነው? ብዙዎች ወደ አምላክ በመጸለይና በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የሚገኙትን አጽናኝ ሐሳቦች በማንበብ ብርታት ማግኘት ችለዋል። በተጨማሪም ቤተሰቦችህና ወዳጆችህ የሚሰጡህ ፍቅራዊ ድጋፍ የብርታት ምንጭ ሊሆንልህ ይችላል።

አንዳንዶች ሁኔታውን መቋቋም የቻሉት እንዴት ነው?

የ58 ዓመቱ ሮበርት እንዲህ የሚል ምክር ሰጥቷል፦ “በአምላክ ላይ እምነት በመጣል በሽታህን ፊት ለፊት ተጋፈጠው፤ አምላክ ሕመምህን መቋቋም እንድትችል ይረዳሃል። ወደ ይሖዋ ጸልይ። ስሜትህን ሁሉ አውጥተህ ንገረው። ለቤተሰብህ ስትል ጠንካራ መሆንና ሁኔታውን በተረጋጋ መንፈስ መወጣት እንድትችል እንዲረዳህ ለምነው።

“ቤተሰቦቼ የሚያደርጉልኝ ስሜታዊ ድጋፍ በእጅጉ ረድቶኛል። በየቀኑ ቢያንስ አንድ ወይም ሁለት ሰው ስልክ ደውሎ ስላለሁበት ሁኔታ ይጠይቀኛል። በተለያየ ቦታ የሚኖሩ ጓደኞቼም ያበረታቱኛል። እነሱ የሚያደርጉልኝ ድጋፍ፣ ብርታት የሚሰጠኝ ሲሆን ይህም ፈጽሞ ተስፋ እንዳልቆርጥ ይረዳኛል።”

የታመመ ጓደኛህን ለመጠየቅ ስትሄድ ሊንዳ የሰጠችውን የሚከተለውን ምክር ልብ ማለትህ ይጠቅምሃል፦ “ታማሚው በተቻለው መጠን እንደ ጤነኛ ሰው ሕይወቱን መምራት ስለሚፈልግ ሁልጊዜ ስለ በሽታው ማውራት ላያስደስተው ይችላል። ስለዚህ ሌላ ጊዜ የምታወሯቸውን ጉዳዮች ለማውራት ሞክር።”

ከከባድ ሕመም ጋር እየታገልንም እንኳ በሕይወታችን ደስተኛ መሆን እንችላለን። አምላክ የሚሰጠን ብርታትና ከመጽሐፍ ቅዱስ የምናገኘው መጽናኛ እንዲሁም አፍቃሪ የሆኑ ቤተሰቦቻችንና ወዳጆቻችን የሚያደርጉልን ድጋፍ ሁኔታውን ተቋቁመን መኖር እንድንችል ይረዳናል።

ሊረዱህ የሚችሉ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች

በአምላክ ታመን።

“ይሖዋን ጠየቅኩት፤ እሱም መለሰልኝ። ከምፈራው ነገር ሁሉ ታደገኝ። ይህ ችግረኛ ተጣራ፤ ይሖዋም ሰማው።”—መዝሙር 34:4, 6

ቀደም ሲል የተጠቀሰችው ሊንዳ እንዲህ ብላለች፦ “‘ሕመሜ እንዲሻለኝ እርዳኝ’ ብዬ አልጸልይም። ሁሌም የምጸልየው ‘ብርታት ስጠኝ፤ ሕመሜን መቋቋም እንድችል እርዳኝ’ እያልኩ ነው።”

ብርታት ለማግኘት የአምላክን ቃል አንብብ።

“ማንኛውም ሰው ‘ታምሜአለሁ’ አይልም።”—ኢሳይያስ 33:24

አምላክ ስለ ወደፊቱ ጊዜ በሰጣቸው ተስፋዎች ላይ ማሰላሰልህ ተስፋህን ያለመልምልሃል፤ ይህም ሕመምህን ለመቋቋም የሚያስችል ብርታት ይሰጥሃል።

የቤተሰቦችህንና የወዳጆችህን እርዳታ ጠይቅ።

“እውነተኛ ወዳጅ ምንጊዜም አፍቃሪ ነው፤ ደግሞም ለመከራ ቀን የተወለደ ወንድም ነው።”—ምሳሌ 17:17

ቀደም ሲል የተጠቀሰችው ኤሊስ እንዲህ የሚል ምክር ሰጥታለች፦ “ራሳችሁን አታግልሉ። ወዳጆቻችሁ የሚያደርጉላችሁን እርዳታ ተቀበሉ። አንዳንድ ጊዜ፣ ብቻችሁን እንደቀራችሁና አምላክም እንኳ ችላ እንዳላችሁ ይሰማችሁ ይሆናል፤ በዚህ ጊዜም ቢሆን ራሳችሁን አታግልሉ።”

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ