የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • km 10/94 ገጽ 8
  • በጥቅምት መጽሔት ላይ አተኩሩ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • በጥቅምት መጽሔት ላይ አተኩሩ
  • የመንግሥት አገልግሎታችን—1994
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • መጽሔቶችን በማንኛውም አጋጣሚ አበርክቱ
    የመንግሥት አገልግሎታችን—1995
  • የአቀራረብ ናሙናዎች
    የመንግሥት አገልግሎታችን—2014
  • መጽሔቶችን ለማበርከት ምን ማለት ይቻላል?
    የመንግሥት አገልግሎታችን—2009
  • የአቀራረብ ናሙናዎች
    የመንግሥት አገልግሎታችን—2013
ለተጨማሪ መረጃ
የመንግሥት አገልግሎታችን—1994
km 10/94 ገጽ 8

በጥቅምት መጽሔት ላይ አተኩሩ

1 መጠበቂያ ግንብ እና ንቁ! የሚያጽናናና የሚያበረታታ ዘላለማዊ የሆነ ምሥራች ይዘዋል። በመጽሔት ላይ ማተኮር እነሱን በጥንቃቄ ለማንበብ ጊዜ መመደብንና ርዕሰ ትምህርቶቹ በአገልግሎት ክልላችን ውስጥ ያሉትን ሰዎች እንዴት ሊማርኩ አንደሚችሉ ማሰብን ይጠይቃል።

2 በመጀመሪያ በሽፋኑ ላይ ትኩረት ከተሰጠባቸው ርዕሰ ትምህርቶች ጋር ተዋወቅ። ብዙውን ጊዜ በሽፋኑ ላይ የሰፈሩት ሥዕላዊ መግለጫዎች መጽሔቶችን ለማበርከት ያስችላሉ። በአገልግሎት ክልልህ ውስጥ ያሉትን ሰዎች ይማርካሉ የምትላቸውን ርዕሶች ምረጥ። በአካባቢህ ያሉት አብዛኞቹ ሰዎች አንድ ሃይማኖት ያላቸው ሰዎች ናቸውን? በይበልጥ የሚያሳስቧቸው ነገሮች የትኞቹ ናቸው? እነዚህን ሐሳቦች በአእምሮህ በመያዝ ውጤታማ አቀራረብ ልትዘጋጅ ትችላለህ። ከዚህ በታች የሰፈሩትን አቀራረቦች ልብ በል።

3 የጥቅምት 1⁠ን “መጠበቂያ ግንብ ” የምታበረክት ከሆነ “መጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሙ በትክክል ምንድን ነው?” የተባለውን ርዕስ ልትጠቀም ትችላለህ። እንዲህ ትል ይሆናል:-

◼ “በማኅበረሰባችን ውስጥ በየቤቱ ማለት ይቻላል መጽሐፍ ቅዱስን ሊያገኙት ይችላሉ። ብዙዎች አንድ ልዩ ጠቀሜታ ያለው መልእክት እንደያዘ ይሰማቸዋል።” ከዚያም እንዲህ ዓይነት ቀጥተኛ ጥያቄ ልትጠይቅ ትችላለህ:- “መጽሐፍ ቅዱስን በዓይነቱ ብቸኛ የሚያደርገው ምንድን ነው ይላሉ?” ወይም “መጽሐፍ ቅዱስን ቢጠቀሙበት ብዙ ሰዎችን ሊረዳ ይችላል ብለው የሚያስቡት ምንድን ነው?” የምታነጋግረው ሰው ምላሽ ከሰጠ በኋላ እንደሚከተለው ያለ ተገቢ አስተያየት ልትሰጥ ትችላለህ:- “መጽሐፍ ቅዱስ በአምላክ መንፈስ አነሣሽነት ለመጻፉና አስተማማኝ መመሪያ ለመሆኑ አሳማኝ መረጃ አለ። ወደ ዘላለም ሕይወት ሊመራ የሚችል እውቀት ይዟል። [ዮሐንስ 17:3⁠ን አንብብ።] ብዙ ሰዎች ቢያከብሩትም እንዴት እንደሚጠቀሙበት አያውቁም። በዚህ መጠበቂያ ግንብ ውስጥ የሚያገኙት ይህ ርዕስ ስለ ወደፊቱ ጊዜ ያሉዎትን ጥያቄዎች ለመመለስ እርስዎ በግል መጽሐፍ ቅዱስን እንዴት ሊጠቀሙበት እንደሚችሉ ያብራራል። ይህንን ቅጂ ልተውልዎት እፈልጋለሁ። አንብበው ከተደሰቱበት በሚቀጥለው ጊዜ ስመጣ መጠበቂያ ግንብ በቋሚነት ቤትዎ ድረስ እንዴት ሊመጣልዎት እንደሚችል እንነጋገራለን።”

4 የጥቅምት 15 “መጠበቂያ ግንብ ” እትምን በመጠቀም እንዲህ ያለ ቀላል አቀራረብ ትመርጥ ይሆናል:-

◼ “በአብዛኛው ሁሉም ሰው የሚያፈቅረውን ሰው በሞት አጥቷል። ይህ ርዕስ ‘ሙታን በምን ሁኔታ ላይ ይገኛሉ?’ የሚል ጥያቄ ያስነሣል። ስንሞት ምን እንሆናለን ብለው ያስባሉ? [መልስ እንዲሰጥ እድል ስጠው።] መጽሐፍ ቅዱስ ለዚህ ጥያቄ የሚሰጠውን መልስ ማወቅ ከፈለጉ ይህን ቅጂ ለእርስዎ ብተውልዎት ደስ ይለኛል።” የምታነጋግረው ሰው ይበልጥ የሚመርጠው እጥር ምጥን ያለ ጽሑፍ ከሆነ ልትሰጠው እንድትችል እናፈቅራቸው የነበሩ ሙታን ምን ተስፋ አላቸው? የተባለውን ትራክት ያዝ።

5 አንዳንድ ጊዜ በጣም የሚማርኩ ርዕሶች የሚገኙት በመጽሔቱ ሽፋን ላይ ሳይሆን መጽሔቱ ውስጥ ይሆናል። ለምሳሌ ያህል፣ የመስከረም 15 መጠበቂያ ግንብ ስለ ይቅር ባይነት በተለይም በትዳር ጓደኛሞች መካከል ሊኖር ስለሚገባው የይቅር ባይነት መንፈስ የሚናገር ጥሩ የሽፋን ርዕስ ይዟል። ይሁን እንጂ ነጠላ ሰው ወይም ባል የሞተባትን ሴት ብናነጋግርስ? በገጽ 21 ላይ ያለውን “ብቸኝነት ሕይወታችሁን እንዲያጨልመው አትፍቀዱለት” የሚለውን ርዕስ ለሁኔታው እንደሚስማማ በማድረግ አጉላ። መጽሔት ስታበረክት የቤቱ ባለቤት ሥዕሎቹን ማየት በሚችልበት መንገድ መጽሔቱን ግለጠው። በተጨማሪም በተለይ ንቁ! ከያዝክ ሁለት መጽሔቶችን ባንድ ላይ ለማበርከት አታመንታ። አዎንታዊ አመለካከት ይኑርህ፤ በቦርሳህ ውስጥም በቂ መጽሔቶችን ያዝ። የምታነጋግረውን ሰው መጽሔቱን እስክትፈልግ ድረስ እንዳታስጠብቀው በሥርዓታማ መንገድ አስተካክለህ ያዛቸው።

6 ሌላው ቀርቶ መጽሐፍ ቅዱስን ገልጠህ ማወያየት ባትችልም እንኳን በየቤቱ መጽሔቶችን ለማበርከት ተዘጋጅ። በተጨማሪም መጽሔቶቹን ተመላልሶ መጠየቅ ለምታደርግላቸው ወይም መጽሐፍ ቅዱስን ለምታስጠናቸው ሰዎች፣ በቢሮዎች ውስጥ ላሉ፣ ለምታውቃቸው ሰዎችና በመንገድ ላይ በምትመሠክርበት ጊዜ አበርክታቸው። ንግግርህ አጠር ያለ ይሁን፤ በመጽሔቱ ውስጥ ያለውን ነገር ሁሉ ልትንግራቸው አትሞክር። ግብ አውጣ፣ አዎንታዊ አመለካከት ይኑርህ፤ ለውድ መጽሔቶቻችን ከበፊቱ በተሻለ ሁኔታ ሞቅ ያለ ስሜት አሳይ!

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ