የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • km 8/02 ገጽ 8
  • ምሥራቹን በሚስብ መንገድ ማቅረብ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ምሥራቹን በሚስብ መንገድ ማቅረብ
  • የመንግሥት አገልግሎታችን—2002
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ከሌሎች ጋር የሐሳብ ግንኙነት በማድረግ ዋነኛ የሆኑት ይሖዋና ክርስቶስ
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1991
  • በክርስቲያን አገልግሎት የሐሳብ ግንኙነት ማድረግ
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1991
  • በቤተሰብና በጉባኤ ውስጥ የሐሳብ ግንኙነት ማድረግ
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1991
  • ጥሩ የሐሳብ ግንኙነት ለተሳካ ትዳር ቁልፍ ነው
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1999
ለተጨማሪ መረጃ
የመንግሥት አገልግሎታችን—2002
km 8/02 ገጽ 8

ምሥራቹን በሚስብ መንገድ ማቅረብ

1 እንድንሰብክና ደቀ መዛሙርት እንድናደርግ የተሰጠንን ተልዕኮ ለመፈጸም ከሌሎች ጋር ውይይት ማድረግ ይኖርብናል። (ማቴ. 24:14፤ 28:19, 20) ወዳጆች በሆኑ ሰዎች መካከል እንኳን ሐሳብ ለሐሳብ መግባባት አስቸጋሪ ሊሆን ይችላል። ታዲያ ምሥራቹን ከዚህ ቀደም ለማናውቃቸው ሰዎች በቀላሉ ለመንገር ምን ሊረዳን ይችላል?

2 እንደ እንግዳ ሳይሆን እንደ ወዳጅ ሆኖ መቅረብ:- በአገልግሎት ሰዎችን በምናነጋግርበት ጊዜ ራሳችንን በእነርሱ ቦታ ለማስቀመጥ ጥረት እናድርግ። ጊዜው እየከፋ በመምጣቱ አንዳንዶች የማያውቁት ሰው ሲያነጋግራቸው ሊጠራጠሩ አልፎ ተርፎም ሊፈሩ ይችላሉ። ይህም ምሥራቹን ለመንገር የምናደርገውን ጥረት ሊያስተጓጉልብን ይችላል። የምታነጋግራቸው ሰዎች መጀመሪያ ላይ የሚሰማቸውን የፍርሃት ስሜት አስወግደው ዘና ብለው እንዲያዳምጡን ማድረግ የምንችለው እንዴት ነው? ልከኛ የሆነው አለባበሳችንና የሰውነት አያያዛችን ገና ምንም ቃል ሳንናገር ለሰዎች አንድ ዓይነት መልእክት ያስተላልፋል። ሥርዓታማ የሆነው አለባበሳችንና ጨዋነት የተሞላው አቀራረባችን የምናነጋግራቸው ሰዎች ሊያድርባቸው የሚችለውን ፍርሃት ለመቀነስ ይረዳል።​—⁠1 ጢ⁠ሞ. 2:9, 10

3 ምሥራቹን በሚስብ መንገድ ለማቅረብ ዘና ያለና ወዳጃዊ የሆነ አቀራረብ መያዛችንም አስፈላጊ ነው። ይህም ሌሎች እንዲረጋጉና የማዳመጥ ፍላጎት እንዲያድርባቸው ለማድረግ ያስችላል። በዚህ ረገድ ጥሩ ዝግጅት ማድረግ አስፈላጊ ነው። ለመናገር የምንፈልገው ሐሳብ በአእምሯችን ውስጥ ግልጽ ሆኖ ከተቀመጠ እንዳንርበተበት ይረዳናል። እንዲህ ያለው የተረጋጋ መንፈስ ሌሎች መልእክታችንን በጉጉት እንዲያዳምጡ ሊያደርጋቸው ይችላል። አንዲት ሴት ቤቷ መጥታ ስላነጋገረቻት ምሥክር ስትናገር እንዲህ ብላለች። “ፊቷ ላይ የሚታየው ፈገግታ የአእምሮ ሰላም እንዳላት አስገንዝቦኛል። ይህም በጣም ማረከኝ።” ይህ ሴትየዋ ምሥራቹን እንድታዳምጥ መንገድ ከፈተላት።

4 የሚስቡ ባሕርያት:- ለሌሎች ከልብ የምናስብ መሆን ይኖርብናል። (ፊልጵ. 2:4) አሳቢ መሆናችንን ማሳየት የምንችልበት አንዱ መንገድ እኛ ብቻ ተናጋሪ እንዳንሆን በመጠንቀቅ ነው። የሐሳብ ልውውጥ ማዳመጥንም የሚጨምር ነው። የምናነጋግራቸው ሰዎች ሐሳባቸውን እንዲገልጹ ስንጋብዛቸውና የሚናገሩትን በጥሞና ስናዳምጥ ለእነርሱ አሳቢ እንደሆንን ይገነዘባሉ። ስለዚህ አድማጭህ ሲናገር ቶሎ ጨርሶ ተዘጋጅቼ የመጣሁትን ሐሳብ በተናገርኩ በሚል ስሜት አትጣደፍ። ተገቢ በሚሆንበት ጊዜ ሁሉ ከልብ አመስግናቸው፤ እንዲሁም እነርሱ በሰጡት ሐሳብ ላይ የራስህን አስተያየት ለማከል ሞክር። ንግግራቸው በጣም የሚያሳስባቸውን ነገር የሚገልጽ ሆኖ ከተሰማህ የተዘጋጀኸውን ሐሳብ በመቀየር በሚያሳስባቸው ጉዳይ ላይ ትኩረት አድርግ።

5 ልክን ማወቅና ትሕትና ውይይቱ ያለ ችግር እንዲቀጥል ያስችላሉ። (ምሳሌ 11:2፤ ሥራ 20:​18, 19) ኢየሱስ ‘የዋህ በልቡም ትሑት’ ስለነበረ ሰዎች በቀላሉ ይቀርቡት ነበር። (ማቴ. 11:29) በሌላ በኩል ደግሞ ራስን ከፍ ከፍ ማድረግ ሰዎችን ያርቃል። ስለዚህ እውነትን እንደያዝን እርግጠኞች ብንሆንም የግትርነት ባሕርይ በሚንጸባረቅበት መንገድ ላለመናገር መጠንቀቅ ይኖርብናል።

6 ግለሰቡ ከመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ጋር የሚጋጭ ሐሳብ ቢሰነዝርስ? አስተሳሰቡን ማስተካከል ይኖርብናል? በጊዜ ሂደት አስተሳሰቡን እንዲያስተካክል ልንረዳው ብንችልም በመጀመሪያው ውይይታችን ላይ ግን ግለሰቡን ለማስተካከል መሞከር አይኖርብንም። አብዛኛውን ጊዜ ለመቀበል የሚከብዱ የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርቶችን ለግለሰቡ ከመንገራችን በፊት በጋራ በምንስማማባቸው ነጥቦች ላይ ብቻ ማተኮሩ ጠቃሚ ነው። ይህም ትዕግሥተኛና ዘዴኛ መሆንን ይጠይቃል። ጳውሎስ በአርዮስፋጎስ ፍርድ ቤት ለነበሩት ፈራጆች የሰጠው ምሥክርነት ለዚህ ጥሩ ምሳሌ ይሆናል።​—⁠ሥራ 17:18, 22-31

7 ምሥራቹን በሚስብ መንገድ ለማቅረብ ከሁሉም በላይ የሚረዳን ባሕርይ ከራስ ወዳድነት ነጻ የሆነ ፍቅር ነው። እኛም ልክ እንደ ኢየሱስ ‘እረኛ እንደ ሌላቸው በጎች ለተጨነቁትና ለተጣሉት’ ሰዎች አዘኔታ ሊሰማን ይገባል። (ማቴ. 9:36) ይህም ምሥራቹን እንድንነግራቸውና በሕይወት መንገድ ላይ መጓዝ እንዲጀምሩ እንድንረዳቸው ይገፋፋናል። መልእክታችን የፍቅር መልእክት ስለሆነ ምንጊዜም ፍቅራዊ በሆነ መንገድ እናቅርበው። በዚህ መንገድ ሐሳባቸውን በማስተላለፍ ረገድ በአጽናፈ ዓለሙ ውስጥ ተወዳዳሪ የሌላቸውን ይሖዋ አምላክንና ኢየሱስ ክርስቶስን መምሰል እንችላለን።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ