የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • km 1/03 ገጽ 4
  • ንጹሑን ልሳን ለሌሎች አስተምሩ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ንጹሑን ልሳን ለሌሎች አስተምሩ
  • የመንግሥት አገልግሎታችን—2003
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ለሁሉም ሕዝቦች የሚሆን ንጹሕ ልሳን
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1991
  • ‘ንጹሑን ቋንቋ’ አጥርተህ ትናገራለህ?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2008
  • ንጹሑ ልሳን አንድ ያድርጋችሁ
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1991
  • ንጹሑን ልሳን ተናገርና ለዘላለም ኑር!
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1991
ለተጨማሪ መረጃ
የመንግሥት አገልግሎታችን—2003
km 1/03 ገጽ 4

ንጹሑን ልሳን ለሌሎች አስተምሩ

1 የይሖዋ ምሥክሮች ከተለያየ ‘ሕዝብ፣ ነገድ፣ ወገንና ቋንቋ’ የመጡ ቢሆንም አንድነት ያለው ሕዝብ ማለትም እውነተኛ ዓለም አቀፋዊ የወንድማማች ማኅበር ናቸው። (ራእይ 7:9) በጊዜያችን ባለው የተከፋፈለ ዓለም ውስጥ እንዲህ ዓይነት ሕዝብ መኖሩ በጣም የሚያስገርም ነው። ይህ አንድነት ሊገኝ የቻለው እንዴት ነው? “ንጹሕን ልሳን” መናገር በመቻላችን ነው።​—⁠ሶፎ. 3:9

2 አስገራሚ ውጤቶች:- ይህ ንጹሕ ልሳን ምንድን ነው? ይሖዋንና ዓላማዎቹን በተመለከተ በአምላክ ቃል ውስጥ የሚገኘውን እውነት በተለይም ስለ መንግሥቱ የሚናገረውን እውነት በሚገባ መረዳት ነው። ኢየሱስ አስቀድሞ እንደተናገረው ይህ እውነት በሚታየው ምድራዊ የመገናኛ መስመር ማለትም “በታማኝና ልባም ባሪያ” አማካኝነት ለሰዎች የሚዳረስ ሲሆን በዚህ ምክንያት “ከአሕዛብ ቋንቋ ሁሉ” የመጡ ሰዎች እውነተኛውን አምልኮ እየተቀበሉ ነው።​—⁠ማቴ. 24:45፤ ዘካ. 8:23

3 ሰዎች ንጹሑን ልሳን ሲማሩ አኗኗራቸውን ከይሖዋ የሥነ ምግባር ደረጃዎች ጋር ለማስማማት ይገፋፋሉ። ‘በአንድ ልብና በአንድ ሐሳብ የተባበሩ’ መሆንን ይማራሉ። (1 ቆ⁠ሮ. 1:10) በተጨማሪም መለኮታዊ ትምህርት ትክክለኛ ምግባር እንዲኖራቸው በተለይም ምሥራቹን ለሌሎች በሚናገሩበት ጊዜ ጤናማና ሐቀኛ አንደበት እንዲኖራቸው ያደርጋል። (ቲቶ 2:7, 8፤ ዕብ. 13:15) እነዚህ አስደናቂ ለውጦች ለይሖዋ ክብር ያመጣሉ።

4 ለምሳሌ ምሥራቹን የሰማ አንድ ሰው በፊት የነበሩት በርካታ ጥያቄዎች ከመጽሐፍ ቅዱስ ተመለሱለት። በተማረው ነገር ስለተነካ በሳምንት ሁለት ጊዜ ማጥናትና በስብሰባዎች ላይ መገኘት ጀመረ። በመንግሥት አዳራሹ ሲገኝ አብዛኞቹ ተሰብሳቢዎች ከእርሱ የተለየ ዘር የነበራቸው ቢሆንም ሞቅ ባለ ወዳጃዊ መንፈስ ስለተቀበሉት ተገረመ። በአጭር ጊዜ ውስጥ እሱና ሚስቱ በሕይወታቸው ላይ ለውጥ አደረጉና ተጠመቁ። ይህ ሰው ከዚያን ጊዜ አንስቶ አብዛኞቹን የቤተሰቡን አባላት ጨምሮ 40 የሚያህሉ ሰዎች የይሖዋ አገልጋይ እንዲሆኑ ረድቷል። ምንም እንኳ የአካል ጉዳተኛ ቢሆንም በቅርቡ አቅኚ ሆኖ ማገልገል ጀምሯል።

5 ሌሎችን ማስተማር:- በዓለማችን ላይ እየተፈጸሙ ያሉት ክስተቶች በርካታ ቅን ሰዎች አስተሳሰባቸውንና አኗኗራቸውን መለስ ብለው እንዲመረምሩ እያደረጓቸው ነው። እኛም ልክ እንደ ኢየሱስ እንዲህ ዓይነት ሰዎችን የመርዳት ፍላጎት ሊያድርብን ይገባል። ልበ ቅን የሆኑ ሰዎች ንጹሑን ልሳን እንዲማሩ ለመርዳት ውጤታማ ተመላልሶ መጠየቆችና የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቶች ቁልፍ ሚና ይጫወታሉ።

6 ጊዜ የለንም የሚሉ ሰዎችን ለመርዳት ውጤታማ ሆኖ የተገኘው ዘዴ እዚያው በራፋቸው ላይ እንደቆምን አጠር ያለ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት መምራት ነው። (የመንግሥት አገልግሎታችን 5/02 ገጽ 1) ይህን ዘዴ ሞክረኸው ታውቃለህ? ተመላልሶ መጠየቅ ለማድረግ በምትዘጋጅበት ወቅት ከጥር 2002 የመንግሥት አገልግሎታችን አባሪ ላይ ለምታነጋግረው ሰው ተስማሚ የሆነ አንድ አቀራረብ ምረጥ። በዚህ አባሪ ላይ ከሰፈሩት አቀራረቦች ውስጥ አብዛኞቹ አምላክ ከእኛ የሚፈልገው ምንድን ነው? በተባለው ብሮሹር ወይም በእውቀት መጽሐፍ አማካኝነት በቀጥታ ውይይት ለማስጀመር ተብለው የተዘጋጁ ናቸው። መግቢያህን ከተናገርክ በኋላ በአንዱ አንቀጽ ላይ በቀላሉ ውይይት ማድረግ በሚያስችልህ መንገድ አቀራረብህን ተለማመድ። አንብበህ የምታብራራው አንድ ወይም ሁለት ጥቅስ ከአንቀጹ ውስጥ ምረጥና ውይይቱን የምትደመድምበት አንድ ጥያቄ አዘጋጅ። ጥያቄው በሚቀጥለው ቀን ጉብኝትህ ለመሸፈን ወዳሰብከው አንቀጽ በቀላሉ ለመሸጋገር ያስችልሃል።

7 የይሖዋ ሕዝቦች ንጹሑን ልሳን በመማራቸው ብዙ በረከቶችን እያገኙ ነው። እኛም ሌሎች አብረውን ‘የይሖዋን ስም እንዲጠሩና’ ‘አንድ ሆነው እንዲያገለግሉት’ የምንረዳ እንሁን።​—⁠ሶፎ. 3:9

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ