የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • km 3/03 ገጽ 1
  • ይሖዋ ሊወደስ የሚገባው አምላክ ነው

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ይሖዋ ሊወደስ የሚገባው አምላክ ነው
  • የመንግሥት አገልግሎታችን—2003
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • በስብሰባዎች ላይ መገኘታችን ስለ እኛ ምን ይጠቁማል?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2019
  • “ይህን ለመታሰቢያዬ አድርጉት” የኢየሱስ ሞት መታሰቢያ ሚያዝያ 2 ይከበራል
    የመንግሥት አገልግሎታችን—2007
  • ሌሎች ሰዎች ከቤዛው እንዲጠቀሙ እርዷቸው
    የመንግሥት አገልግሎታችን—2006
  • መልካም ለማድረግ የምትቀኑ ሁኑ!
    የመንግሥት አገልግሎታችን—2003
ለተጨማሪ መረጃ
የመንግሥት አገልግሎታችን—2003
km 3/03 ገጽ 1

ይሖዋ ሊወደስ የሚገባው አምላክ ነው

የጌታ እራት ሚያዝያ 16 ቀን ይከበራል

1 ሚያዝያ 16, 2003 በጉጉት የምንጠባበቀው ዕለት ነው። በዚያን ዕለት ምሽት በዓለም ዙሪያ የይሖዋን ስም ከሚያወድሱ በሚልዮን የሚቆጠሩ የእምነት አጋሮቻችን ጋር በመሆን የኢየሱስን ሞት መታሰቢያ እናከብራለን። ድንቅ ለሆነው የቤዛው ዝግጅት ሁላችንም ይሖዋን ልናወድሰው ይገባል። በዚህ ዝግጅት አማካኝነት ታዛዥ ለሆኑ የሰው ልጆች በሙሉ አስደናቂ በረከቶችን ያጎናጽፋቸዋል። ልክ እንደ መዝሙራዊው እኛም “እግዚአብሔር ታላቅ ነው እጅግም የተመሰገነ ነው” በማለት በሙሉ ልባችን እናወድሰዋለን።​—⁠መዝ. 145:3

2 የመታሰቢያው በዓል ሰሞን በአምላክ ጥሩነትና “በሕይወት እንኖር ዘንድ . . . አንድ ልጁን ወደ ዓለም” በመላክ ባደረገልን ውለታ ላይ የምናሰላስልበት ወቅት ነው። (1 ዮሐ. 4:9, 10) የጌታ እራትን በታዛዥነት ማክበራችን ‘ይሖዋ ርኅሩኅና መሓሪ እንዲሁም ምሕረቱ የበዛ’ መሆኑን እንድናስታውስ ይረዳናል። (መዝ. 145:8) በእርግጥም የቤዛው ዝግጅት ይሖዋ ለመላው የሰው ዘር ያሳየው ከሁሉ የላቀ ፍቅር መግለጫ ነው። (ዮሐ. 3:16) አምላክ ስላሳየን ፍቅርና ኢየሱስ ስለተከተለው የታማኝነት ጎዳና ስናስብ ይሖዋን ለማወደስ እንገፋፋለን። ይሖዋ የዘላለም ሕይወት የምናገኝበትን አጋጣሚ በማመቻቸት ላሳየን ወደር የለሽ ፍቅር ለዘላለም እናወድሰዋለን።​—⁠መዝ. 145:1, 2

3 ሌሎች ይሖዋን እንዲያወድሱ እርዷቸው:- አምላክ ለሰጠን ከሁሉ የላቀ ቤዛዊ ስጦታ ያለን አድናቆት ሌሎችም ከእኛ ጋር ሆነው ይሖዋን እንዲያወድሱ ግብዣ እንድናቀርብላቸው ይገፋፋናል። መዝሙራዊው በመንፈስ ተገፋፍቶ “የበጎነትህን ብዛት በደስታ ያወሳሉ፤ ስለ ጽድቅህም በእልልታ ይዘምራሉ” በማለት ጽፏል። (መዝ. 145:7 አ.መ.ት ) የይሖዋ ምሥክሮች ባለፈው ዓመት ብቻ በዓለም ዙሪያ በስብከቱ ሥራ ከአንድ ቢልዮን ሰዓት በላይ አሳልፈዋል። ይህ ጥረታቸው ምን ውጤት አስገኝቷል? በየሳምንቱ በአማካይ ከ5, 100 የሚበልጡ ሰዎች ራሳቸውን ለይሖዋ መወሰናቸውን በጥምቀት ያሳያሉ። በመታሰቢያው በዓል ላይ የምሥራቹ አስፋፊዎች ሆነው ይሖዋን ማወደስ ያልጀመሩ ከ9 ሚልዮን የሚበልጡ ሰዎችን ጨምሮ 15, 597, 746 የሚያህሉ ተሰብሳቢዎች መገኘታቸው ተጨማሪ ዕድገት ሊኖር እንደሚችል የሚያመለክት ነው! የመንግሥቱ አዋጅ ነጋሪዎች እንደመሆናችን መጠን ምሥራቹን በማወጅ ሰዎች ትኩረታቸውን ወደ ይሖዋ፣ ወደ ልጁና ወደ መንግሥቱ እንዲያደርጉ ለመርዳት የተሰጠንን ልዩ መብት በአድናቆት እንመለከተዋለን።

4 ሌሎች ይሖዋን እንዲያወድሱ ለማበረታታት የምንችልበት አንዱ መንገድ ከእኛ ጋር ሆነው የጌታ እራትን እንዲያከብሩ በመጋበዝ ነው። ልትጋብዛቸው ያሰብከውን እንዲሁም ቀኑንና ሰዓቱን ልታስታውሳቸው የሚገባህን ሰዎች ስም ዝርዝር አውጥተሃል? ለሁሉም የመጋበዣ ወረቀት ሰጥተሃቸዋል? ካልሆነ በቀረህ ጊዜ ውስጥ ለመጋበዝ ጥረት አድርግ። በዓሉ የሚከበርበትን ዓላማ እንዲገነዘቡ እርዳቸው። በበዓሉ ላይ የጋበዝካቸውን ሰዎች ለመቀበል ንቁ ሁን። ባይተዋርነት እንዳይሰማቸው ለማድረግ ከሌሎች ጋር አስተዋውቃቸው እንዲሁም በበዓሉ ላይ ለመገኘት ላደረጉት ጥረት አመስግናቸው።

5 አዳዲሶች በመታሰቢያው በዓል ላይ መገኘታቸው መንፈሳዊ እድገት እንዲያደርጉ ሊያነሳሳቸው ይችላል። ከአሰቃቂ ሁኔታ በኋላ በሚፈጠር ጭንቀት ስለሚሰቃይ ብዙ ሰዎች ባሉበት ቦታ መገኘት የሚያስፈራው አንድ የመጽሐፍ ቅዱስ ተማሪ በመታሰቢያው በዓል ላይ ተገኘ። ከበዓሉ በኋላ ምን እንደተሰማው ሲጠየቅ “የተቀደሰ ምሽት ነበር፤ በበዓሉ ላይ በመገኘቴ ተደስቻለሁ” ብሏል። ከዚያን ጊዜ ወዲህ በስብሰባዎች ላይ መገኘት ጀምሯል።

6 ከመታሰቢያው በዓል በኋላ:- እነዚህ ፍላጎት ያሳዩ ሰዎች የይሖዋ አወዳሾች እንዲሆኑ ለመርዳት ምን ማድረግ ይቻላል? ሽማግሌዎች በመታሰቢያው በዓል ላይ ለተገኙት አዳዲስ ሰዎች ትኩረት በመስጠት ብቃት ያላቸው አስፋፊዎች ብዙም ሳይቆዩ እንዲጎበኟቸውና በበዓሉ ላይ ስለተማሯቸውና ስለተመለከቷቸው አስደሳች ነገሮች እንዲያወያዩአቸው ዝግጅት ያደርጋሉ። አንዳንዶች መጽሐፍ ቅዱስ ለማጥናት ይፈልጉ ይሆናል። በስብሰባዎች ላይ መገኘታቸው የመጽሐፍ ቅዱስ እውቀታቸውን ለማሳደግ ስለሚረዳቸው በሁሉም ሳምንታዊ የጉባኤ ስብሰባዎች ላይ እንዲገኙ ግብዣ ሊቀርብላቸው ይገባል።

7 አዘውትረው በአገልግሎት የማይካፈሉና በስብሰባዎች ላይ የማይገኙ አስፋፊዎች በጉባኤ ስብሰባዎች ላይ እንዲገኙ ለማበረታታት ዝግጅቶች እየተደረጉ ነው። ሽማግሌዎች አንድ አገልግሎት ያቆመ አስፋፊ በድጋሚ በመስክ አገልግሎት መካፈል እንዲጀምር እገዛ እንድታደርግለት ከጠየቁህ በፈቃደኝነት ተባበራቸው። ለወንድሞቻችን እንደዚህ ዓይነት ፍቅራዊ አሳቢነት ማሳየታችን “ጊዜ ካገኘን ዘንድ ለሰው ሁሉ ይልቁንም ለሃይማኖት ቤተ ሰዎች መልካም እናድርግ” ከሚለው የሐዋርያው ጳውሎስ ምክር ጋር እንደምንስማማ ያሳያል።​—⁠ገላ. 6:10

8 ሁላችንም ሚያዝያ 16 በሚከበረው የመታሰቢያው በዓል ላይ ለመገኘት ከፍተኛ ጥረት እናድርግ። ይሖዋን ለማወደስ የሚያስችለን ይህ ልዩ አጋጣሚ ሊያመልጠን አይገባም። አዎን፣ ዛሬም ሆነ ለዘላለም ይሖዋን ለታላላቅ ሥራዎቹ እናወድሰው!​—⁠መዝ. 145:21

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ