መጽሔቶችን ለማበርከት ምን ማለት ይቻላል?
መጠበቂያ ግንብ ግንቦት 1
“የምናፈቅረው ሰው ሲሞት ይህንን ሰው እንደገና ለማየት እንደምንጓጓ የታወቀ ነው፤ በዚህ አይስማሙም? [መልስ እስኪሰጥ ጠብቀው።] ብዙ ሰዎች በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የሚገኘውን የትንሣኤ ተስፋ በማወቃቸው ተጽናንተዋል። [ዮሐንስ 5:28, 29ን አንብብ።] ይህ መጽሔት ትንሣኤ መቼ እንደሚከናወንና ከዚህ ተጠቃሚ የሚሆኑት እነማን እንደሚሆኑ ይገልጻል።”
ንቁ! ግንቦት 2005
“የኃይል ምንጭ ተፈላጊነት በየዓመቱ እየጨመረ ነው። አስፈላጊ የሆነው የኃይል ምንጭ አንድ ቀን ቢቋረጥ ምን እንደሚሆን አስበው ያውቃሉ? [መልስ እስኪሰጥ ጠብቀው።] ይህ መጽሔት ብክለት የማያስከትል የኃይል ምንጭ ለማግኘት እየተደረገ ያለውን የለውጥ ሂደት ይገልጻል። በተጨማሪም የሁሉም ዓይነት የኃይል ምንጮች ፈጣሪ ማን እንደሆነ ይናገራል።” ኢሳይያስ 40:26ን አንብብለት።
መጠበቂያ ግንብ ግንቦት 15
“ድህነት የሌለበት ዓለም ይመጣል ብለው አስበው ያውቃሉ? [መልስ እስኪሰጥ ጠብቀው።] አምላክ የገባልንን ተስፋ ልብ ይበሉ። [ኢሳይያስ 65:21ን አንብብለት።] ይህ መጠበቂያ ግንብ ተስፋው እንዴት እንደሚፈጸም ያብራራል።” ይህ ተስፋ መቼ ይፈጸማል? የሚለውን ጥያቄ ተመልሰህ ስትመጣ እንደምትወያዩበት ንገረው።