መጽሔቶችን ለማበርከት ምን ማለት ይቻላል?
መጠበቂያ ግንብ ታኅሣሥ 1
“ብዙ ሰዎች አርማጌዶን የሚለውን ቃል ሲሰሙ የሚታያቸው ነገር አሰቃቂ የሆነ የጅምላ ጭፍጨፋ ነው። [በገጽ 3 ላይ ያለውን ሣጥን አሳይ] አርማጌዶን ለእኛ ጥቅም ሲባል ከሚደረጉ ግሩም ዝግጅቶች መካከል አንዱ መሆኑን ቢያውቁ ምን ይሰማዎታል? [መልስ እስኪሰጥ ጠብቀው] ይህ መጽሔት እንዲህ የምንልበትን ምክንያት ያብራራል።” 2 ጴጥሮስ 3:13ን አንብብ።
ንቁ! ታኅሣሥ 2005
“የመጣሁት ወደፊት እያንዳንዱ ሰው የተመቻቸ መኖሪያ ቤት አግኝቶ እንደሚኖር ልነግርዎት ነው። ዛሬ ብዙ ሰዎች ቤት አልባ መሆናቸው የሚያሳዝን አይደለም? [መልስ እስኪሰጥ ጠብቀው። ከዚያም ኢሳይያስ 65:21, 22ን አንብብ] ይህ መጽሔት የቤት እጦት መንስኤ ምን እንደሆነ ይናገራል። በተጨማሪም አምላክ አሁን ባነበብነው ጥቅስ ላይ የሚገኘውን ተስፋ እንዴት እንደሚፈጽመው ያብራራል።”
መጠበቂያ ግንብ ታኅሣሥ 15
“ብዙ ሰዎች የበዓል ሰሞን ሃይማኖታዊ ገጽታው ጠፍቶ የንግድ እንቅስቃሴ የሚጧጧፍበት ጊዜ እየሆነ መምጣቱ ያሳስባቸዋል። ምናልባት ሰዎች በዓል የሚከበርበትን ዓላማ እንደሳቱ ይሰማዎታል? [መልስ እስኪሰጥ ጠብቀው] ይህ መጽሔት በበዓል ወቅት የሚዘወተሩት ልማዶች ከጊዜ ወደ ጊዜ እንዴት ይዘታቸው እየተቀየረ እንደመጣ ይናገራል። በተጨማሪም ለአምላክና ለክርስቶስ እውነተኛ ክብር እንዴት መስጠት እንደምንችል ያስረዳል።” ዮሐንስ 17:3ን አንብብ።