የመታሰቢያውን በዓል የሚመለከቱ ማሳሰቢያዎች
ከመታሰቢያው በዓል ዝግጅት ጋር በተያያዘ ሽማግሌዎች የሚከተሉትን ጉዳዮች ትኩረት ሰጥተው ሊያስቡባቸው ይገባል:-
◼ ቂጣውና ወይኑ ፀሐይ ከመጥለቋ በፊት መዞር እንደሌለባቸው አስታውሱ።
◼ ተገቢው ዓይነት ቂጣና ወይን ተዘጋጅቶ መቀመጥ አለበት።—የየካቲት 15, 2003 መጠበቂያ ግንብ ገጽ 14-15ን ተመልከቱ።
◼ ሳህኖችን፣ የወይን ብርጭቆዎችን፣ ለበዓሉ ተስማሚ የሚሆን ጠረጴዛና የጠረጴዛ ልብስ ቀደም ብሎ ወደ አዳራሹ ማምጣትና በቦታው ማስቀመጥ ያስፈልጋል።
◼ የመንግሥት አዳራሹ ወይም ለበዓሉ የምትጠቀሙበት ሌላ የመሰብሰቢያ ቦታ አስቀድሞ በደንብ መጽዳት ይኖርበታል።
◼ አስተናጋጆችም ሆኑ ቂጣውንና ወይኑን የሚያዞሩት ወንድሞች በቅድሚያ ሊመረጡና የሥራ ድርሻቸው ምን እንደሆነ፣ ሥራቸውን በተገቢው መንገድ እንዴት እንደሚያከናውኑ እንዲሁም ሥርዓታማ የሆነ አለባበስና አበጣጠር አስፈላጊ መሆኑ ሊነገራቸው ይገባል።
◼ አቅመ ደካማ በመሆናቸው በበዓሉ ላይ መገኘት የማይችሉ ቅቡዓን ከቂጣውና ከወይኑ መካፈል የሚችሉበት ሁኔታ መመቻቸት ይኖርበታል።
◼ ከአንድ በላይ ጉባኤዎች በመንግሥት አዳራሹ የሚጠቀሙ ከሆነ በመግቢያዎች አካባቢ፣ በመንገዱ ላይ እንዲሁም በመኪና ማቆሚያ ቦታዎች አላስፈላጊ ጭንቅንቅ እንዳይፈጠር በጉባኤዎቹ መካከል ጥሩ ቅንጅት ሊኖር ይገባል።
◼ የመንግሥት አዳራሹን ሳይሆን ሌላ የመሰብሰቢያ ቦታ የምትጠቀሙ ከሆነ ተሰብሳቢዎች በሙሉ ተናጋሪው የሚናገረውን በሚገባ ማዳመጥ እንዲችሉ ተገቢው ዓይነት የድምፅ መሣሪያ ሊኖራችሁ ይገባል።