መጽሔቶችን ለማበርከት ምን ማለት ይቻላል?
መጠበቂያ ግንብ ሰኔ 1
“በሰፊው ከሚታወቁ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች መካከል አንዱ ስለ ኖኅና በእሱ ዘመን ተከስቶ ስለነበረው የጥፋት ውኃ የሚናገረው ነው። እርስዎ የጥፋት ውኃው በእርግጥ የተከሰተ ይመስልዎታል? [መልስ እስኪሰጥ ጠብቀው።] የሚገርመው ኢየሱስ ራሱ፣ የጥፋት ውኃውን እንደተፈጸመ እውነተኛ ክንውን አድርጎ ጠቅሶታል። [ሉቃስ 17:26, 27ን አንብብ።] ይህ መጽሔት ስለ ጥፋት ውኃ የሚናገረው የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪክ እውነት ስለ መሆኑ አሳማኝ ምክንያቶችን የሚያቀርብ ከመሆኑም በላይ ከታሪኩ ምን ጠቃሚ ትምህርት እንደምናገኝ ይገልጻል።”
ንቁ! ሰኔ 2008
“በአሁኑ ጊዜ ልጆችን ማሳደግ አስቸጋሪ እየሆነ መጥቷል፤ በተለይ ደግሞ የጉርምስና ዕድሜ ላይ በሚደርሱበትና ድንገተኛ ለውጦችን በሚያሳዩበት ወቅት ሁኔታው ከባድ ይሆናል። ታዲያ ወላጆች አስተማማኝ የሆነ ምክር ከየት ማግኘት የሚችሉ ይመስልዎታል? [መልስ እስኪሰጥ ጠብቀው። ከዚያም ኢሳይያስ 48:17, 18ን አንብብ።] ይህ መጽሔት፣ ወላጆች ነገሮችን በጥበብና በማስተዋል መያዝ የሚችሉት እንዴት እንደሆነ የሚጠቁሙ ወቅታዊ ሐሳቦችን ይዟል።”
መጠበቂያ ግንብ ሰኔ 1
“አምላክ ሁሉንም ሃይማኖቶች የሚቀ በል ይመስልዎታል? [መልስ እስኪሰጥ ጠብቀው።] የጥንቶቹ እስራኤላውያን በዙሪያቸው የነበሩ ሕዝቦች የሚከተሉትን ሃይማኖታዊ ልማድ ሲከተሉ አምላክ ምን እንደተሰማው ማወቅ ትኩረት የሚስብ ነው። [ሕዝቅኤል 6:6ን አንብብ።] ይህ መጽሔት ‘አምላክ ማንኛውንም አምልኮ ይቀበላል?’ ለሚለው ጥያቄ መልስ ይሰጣል።” ገጽ 9 ላይ የሚገኘውን ርዕስ አሳየው።
ንቁ! ሰኔ 2008
“የጉርምስና ዕድሜ በተለይ ለወጣቶችና ለወላጆቻቸው አስቸጋሪ ይሆንባቸዋል ቢባል ሳይስማሙ አይቀርም። ይህን ምክር መከተል አንድ ወላጅ ኃላፊነቱን በሚገባ እንዲወጣ የሚረዳው ይመስልዎታል? [ያዕቆብ 1:19ን አንብብ። ከዚያም መልስ እስኪሰጥ ጠብቀው።] በዚህ መጽሔት ውስጥ ጠቃሚና በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ የተመሠረቱ ሐሳቦችን ያገኛሉ።”