የድረ ገጹን ትራክት ተጠቀሙ
የትራክቱ ርዕስ በአእምሯችን ለሚጉላሉ ጥያቄዎች መልስ ማግኘት የሚቻለው ከየት ነው? የሚል ነው። በትራክቱ የጀርባ ገጽ ላይ ሦስት ጥያቄዎች ይገኛሉ። ሁኔታው አመቺ ከሆነ ግለሰቡ የየትኛውን ጥያቄ መልስ ይበልጥ ማወቅ እንደሚፈልግ ጠይቁት፤ ከዚያም ድረ ገጹ ላይ የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርቶች > የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው በሚለው ሥር መልሱን አሳዩት። በዚሁ ክፍል ላይ ‘የአምላክ መንግሥት ምንድን ነው?’ ወይም ‘የአምላክ መንግሥት ወደፊት ምን ያከናውናል?’ ለሚሉት ጥያቄዎችም መልስ ማግኘት ይችላል።
በአምላክ መንግሥት አገዛዝ ሥር የሚኖረውን አስደሳች ሕይወት በተመለከተ መጽሐፍ ቅዱስ ምን እንደሚናገር ለሰዎች ማሳወቅ እንድንችል የዚህን ትራክት የተወሰኑ ቅጂዎች ምንጊዜም እንያዝ።