የአቀራረብ ናሙናዎች
መጠበቂያ ግንብ ጥር 1
“ሙስና ሊወገድ የማይችል ችግር ሆኗል ቢባል ሁላችንም እንሰማለን። ለዚህ ምክንያቱ ምን ይመስልዎታል? [ሐሳቡን እንዲገልጽ ዕድል ስጠው።] እስቲ ትኩረቴን የሳበ አንድ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅስ ላሳይዎት። [መክብብ 7:20ን አንብብ።] ይህ መጽሔት ለሙስና መፍትሔው ምን እንደሆነ መጽሐፍ ቅዱስ የሚሰጠውን መልስ ይገልጻል። መጽሔቱን ወስደው ጊዜ ሲያገኙ ቢያነቡት ደስ ይለኛል።”
ንቁ! ጥር
“ብዙ ሰዎች ሕይወት የጀመረው በዝግመተ ለውጥ እንደሆነ ይናገራሉ፤ ሌሎች ግን ይህን ሐሳብ ይጠራጠራሉ። እርስዎ ሕይወት የጀመረው እንዴት ነው ብለው ያምናሉ? [ሐሳቡን እንዲገልጽ ዕድል ስጠው።] ለበርካታ አሥርተ ዓመታት የተደረገ ምርምር እንደሚያሳየው ሕይወት ያለው ነገር የሚገኘው ሕይወት ካለው ነገር ብቻ ነው። ይህ ደግሞ መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ከሚገኝ ለመረዳት ቀላል ከሆነ አንድ ሐሳብ ጋር ይስማማል። [መዝሙር 36:9ን አንብብ።] ብዙዎች፣ ሕይወት በጣም ውስብስብና አስደናቂ በመሆኑ በዝግመተ ለውጥ ሊገኝ እንደማይችል ያምናሉ፤ ይህ መጽሔት ሰዎች እዚህ መደምደሚያ ላይ የደረሱበትን ምክንያት ይገልጻል።”