የአቀራረብ ናሙናዎች
መጠበቂያ ግንብ ጥር 1
ዕብራውያን 13:18ን ካነበብክለት በኋላ “ሁሉም ሰው በዚህ የመጽሐፍ ቅዱስ መመሪያ ቢመራ ዓለማችን የተሻለች ቦታ የምትሆን አይመስልዎትም?” ብለህ ጠይቀው። ከዚያም ሐሳቡን እንዲገልጽ ዕድል ስጠው። “መጽሐፍ ቅዱስ በሁሉም ነገር ሐቀኛ እንድንሆን ይመክረናል። የዚህ ወር የመጠበቂያ ግንብ እትም ሐቀኝነት ሁሉንም የሕይወታችንን ዘርፍ እንዴት እንደሚነካ ያብራራል።”
ንቁ! ጥር
“የመጣሁት የዚህን ወር የንቁ! መጽሔት እትም ልሰጥዎት ነው። [ለቤቱ ባለቤት መጽሔቶቹን ስጠው።] በገጽ 2 ላይ የሚገኙትን ጥያቄዎችና ሰዎች የሚሰጧቸውን አንዳንድ የተለመዱ መልሶች ይመልከቱ። እርስዎ ምን ይመስልዎታል? [ሐሳቡን እንዲገልጽ ዕድል ስጠው።] ይህ ርዕስ ስለ ሕይወት ያለንን አመለካከት እንድናሻሽል የሚረዱ አንዳንድ የመጽሐፍ ቅዱስ ምክሮችን ይዟል።”