ክርስቲያናዊ ሕይወት
የማስተማሪያ መሣሪያዎቻችንን በጥሩ ሁኔታ ተጠቀሙባቸው
ደቀ መዛሙርት ማድረግ ቤት ከመገንባት ጋር ይመሳሰላል። በሥራችን ስኬታማ ለመሆን ያሉንን መሣሪያዎች በጥሩ ሁኔታ የመጠቀም ችሎታ ማዳበር ያስፈልገናል። በተለይ ደግሞ ዋነኛ መሣሪያችን የሆነውን የአምላክን ቃል የመጠቀም ችሎታችንን ማዳበር ያስፈልገናል። (2ጢሞ 2:15) ሰዎችን ደቀ መዛሙርት የማድረግ ግባችን ላይ ለመድረስ ከፈለግን ለማስተማር የምንጠቀምባቸውን ሌሎች ጽሑፎችንና ቪዲዮዎችንም በጥሩ ሁኔታ የመጠቀም ችሎታ ማዳበር ያስፈልገናል።a
በማስተማሪያ መሣሪያዎቻችን በጥሩ ሁኔታ የመጠቀም ችሎታ ማዳበር የምትችለው እንዴት ነው? (1) የመስክ አገልግሎት ቡድን የበላይ ተመልካችህ እንዲረዳህ ጠይቅ፤ (2) ተሞክሮ ካላቸው አስፋፊዎች ወይም አቅኚዎች ጋር አገልግል (3) አዘውትረህ ልምምድ አድርግ። እነዚህን ጽሑፎችና ቪዲዮዎች በጥሩ ሁኔታ የመጠቀም ችሎታ ስታዳብር በአሁኑ ጊዜ እየተካሄደ ባለው መንፈሳዊ የግንባታ ሥራ ላይ በመካፈል የምታገኘው ደስታ እየጨመረ ይሄዳል።
መጽሔቶች
ብሮሹሮች
መጻሕፍት
ትራክቶች
ቪዲዮዎች
መጋበዣዎች
የአድራሻ ካርዶች
a በማስተማሪያ መሣሪያዎቻችን ዝርዝር ውስጥ የማይገኙ የተወሰኑ ጽሑፎች አሉ፤ እነዚህ ጽሑፎች የሚዘጋጁት አንድን የማኅበረሰብ ክፍል ብቻ ግምት ውስጥ በማስገባት ነው። አስፈላጊ በሆነ ጊዜ ሁሉ እነዚህን ጽሑፎች መጠቀም ይቻላል።