ክርስቲያናዊ ሕይወት
ለዘላለም በደስታ ኑር! ያሉት ጠቃሚ ገጽታዎች
ለዘላለም በደስታ ኑር! የተባለው መጽሐፍ ላይ ያሉትን ቪዲዮዎችና የአመለካከት ጥያቄዎች ወደሃቸዋል? “አንዳንዶች እንዲህ ይላሉ”፣ “ግብ” እና “ምርምር አድርግ” የሚሉትን ገጽታዎችስ? ደቀ መዛሙርት በማድረጉ ሥራ ስትካፈል ልትጠቀምባቸው የምትችል ምን ሌሎች ገጽታዎች አሉ?—ማቴ 28:19, 20
ሚዲያ፦ ማስጠናት የምትመርጠው በታተመው መጽሐፍ ተጠቅመህ ከሆነ ቪዲዮዎቹንና ሌሎች የሚዲያ ፋይሎችን አንድ ቦታ ላይ ማግኘት የምትችለው እንዴት ነው? በኤሌክትሮኒክ ቅጂው ላይ ከአራቱ ዋና ዋና ክፍሎች አንዱን ምረጥ። ከተዘረዘሩት ምዕራፎች በታች በዚያ ክፍል ሥር የሚገኙ ቪዲዮዎችን ማግኘት የምትችልበት አማራጭ አለ። (ምስል 1ን ተመልከት።)
“ለሕትመት የተቀናበረ” የሚለው አማራጭ፦ የምታጠኑት በኤሌክትሮኒክ መሣሪያ ተጠቅማችሁ ከሆነ በጥናቱ ወቅት አለፍ አለፍ እያልክ “ለሕትመት የተቀናበረ” የሚለውን አማራጭ መጠቀምህ ጠቃሚ ሊሆን ይችላል። ምዕራፉን ከከፈትክ በኋላ በገጹ አናት ላይ የሚገኘውን ሦስት ነጥብ ጠቅ አድርግ፤ ከዚያም “ለሕትመት የተቀናበረ” የሚለውን ምረጥ። ይህ የእይታ ማስተካከያ የሚጠቅምህ እንዴት ነው? እየተወያያችሁበት ያለው ነጥብ ከአጠቃላይ የምዕራፉ ጭብጥ ጋር ያለውን ዝምድና ለማስተዋል ይረዳሃል። ወደ ቀድሞው የእይታ አማራጭ ለመመለስ ሦስት ነጥቡን ጠቅ ካደረግህ በኋላ “ለዲጂታል የተዘጋጀ” የሚለውን ምረጥ።
“ብቃቱን አሟላለሁ?”፦ በመጽሐፉ መጨረሻ ላይ የሚገኙት እነዚህ ሣጥኖች፣ አንድ ሰው ከጉባኤው ጋር ለመስበክና ለመጠመቅ የሚያስፈልጉትን ብቃቶች ይገልጻሉ። (ምስል 2ን ተመልከት።)
ተጨማሪ ሐሳብ፦ አስፈላጊ ስለሆኑ አንዳንድ ርዕሰ ጉዳዮች ተጨማሪ ማብራሪያ ይሰጣል። በኤሌክትሮኒክ ቅጂው ላይ ከእያንዳንዱ ተጨማሪ ሐሳብ በታች ሊንክ አለ፤ ሊንኩን ጠቅ ስታደርገው ምዕራፉ ላይ ወደነበርክበት ቦታ ይመልስሃል። (ምስል 2ን ተመልከት።)
ጥናትህ ለዘላለም በደስታ ኑር! የተባለውን መጽሐፍ ሳይጨርስ ቢጠመቅ እንኳ እስከ መጨረሻው አስጠናው። ከተጠመቀ በኋላም እንኳ ጥናቱን ስትመራ ሰዓቱን፣ ተመላልሶ መጠየቁንና ጥናቱን ሪፖርት ማድረግ ትችላለህ። አንድ አስፋፊ አብሮህ ጥናቱ ላይ ከተገኘና ተሳትፎ ካደረገ እሱም ሰዓቱን ሪፖርት ማድረግ ይችላል