ክርስቲያናዊ ሕይወት
ስደት ሲደርስባችሁ ደስ ይበላችሁ
ክርስቲያኖች ስደት እንደሚደርስባቸው ይጠብቃሉ። (ዮሐ 15:20) ስደት በተወሰነ መጠን ጭንቀት፣ አንዳንዴም ሥቃይ ሊያስከትል ቢችልም በጽናት ስንቋቋመው ደስታ እናገኛለን።—ማቴ 5:10-12፤ 1ጴጥ 2:19, 20
ምንም ነገር ደስታችሁን እንዲያሳጣችሁ አትፍቀዱ—ስደት የሚለውን ቪዲዮ ተመልከት፤ ከዚያም የሚከተሉትን ጥያቄዎች ለመመለስ ሞክር፦
የሚከተሉት ነገሮች ያላቸውን ጥቅም በተመለከተ ከወንድም ባዤኖቭ ተሞክሮ ምን ትምህርት አግኝተሃል?
መጽሐፍ ቅዱስን በየዕለቱ ማንበብ
ከእምነት ባልንጀሮቻችን ድጋፍ ማግኘትa
አዘውትሮ መጸለይ
የመንግሥቱን መዝሙሮች መዘመር
ስለ እምነታችን መናገር
a ስለታሰሩ ክርስቲያኖች መጸለይ እንችላለን፤ እንዲያውም በጸሎታችን ላይ ስማቸውን መጥቀስ እንችላለን። ይሁንና ወደ እነሱ መላክ የምንፈልገውን የግል ደብዳቤ ቅርንጫፍ ቢሮው ሊያደርስልን አይችልም።